ኪነ-ጥበብ infotainment

‹‹ዳሞ ደስ ይበልኪ ተሠርገወ ደብርኪ››

‹‹ዳሞ ደስ ይበልኪ
ተሠርገወ ደብርኪ››
ትግርኛን ከግእዝ ጋር አስተባብሮ ‹‹ደስ ይበልሽ ደብረዳሞ፤ ተራራሽ አምባሽ አሸበረቀ፤ ተዋበ፤›› እያለ ግጥሙን ያቀረበው አንድ የአካባቢ ነዋሪ ነው፡፡

ጭራ ዋጣውም (ባለማሲንቆው አዝማሪ) በበኩሉ
‹‹አረጋዊ ፀሓዬ
መፅኤአለኹ ናብ መፅብዓዬ››
(አረጋዊ ፀሐዬ ወደስለቴ መጥቻለሁ)
ጭራ (ማሲንቆ) እና ድምፁን ሲያስማማ በዙርያው ያሉት ምዕመናንም እየተቀባበሉ መዘመራቸውን አልተውም፡፡ ይህም የተሰማው፣ የተስተጋባው ጥቅምት 14 ቀን 2004 ዓ.ም. ዓመታዊው የአቡነ አረጋዊ በዓል በተከበረበት ዕለት በጥንታዊውና ታሪካዊው ደብረ ዳሞ ገዳም በተገኘበት ጊዜ ነው፡፡

የዘንድሮው በዓል ለየት ያደረገውና ምእመናኑን፣ ቱሪስቶችን፣ የአካባቢውንም ነዋሪዎች ሁሉ የላቀ ደስታ ያስጎናፀፋቸው ሦስት ዓይነት ግንባታዎች ተከናውነው መመረቃቸው ነው፡፡

በስድስተኛው ክፍለ ዘመን የተቆረቆረው ገዳም በከፍታማ ተራራ ላይ የሚገኝና ዙርያው ገደል በመሆኑ መወጣጫው ከቆዳ በተሠራ ሐብል (ገመድ) በመጠቀም ነው፡፡ ለ14 ክፍለ ዘመን ያህል ወደ መወጣጫው ሀብል (አምባው ስር) ለመድረስ ለምእመናን (ነጋድያን /Pilgrimage)፣ ለጎብኚዎች እጅግ ፈታኝ የነበረውን ወጣ ገባና ተረተር የለወጠ 1.2 ኪሎ ሜትር የሚደርስ በሦስት አቅጣጫ መረማመጃ ደረጃዎች መሠራቱ ነው፡፡ ‹‹መንገዱ እጅግ ፈታኝና አስቸጋሪ ስለነበረ ከርቀት ከመስኩ ላይ ሆነን ነበር ጸሎታችንን ስናደርስ የኖርነው፡፡ አሁን ግን መወጣጫው መሠራቱ ሳንቸገር መድረስ ችለናል›› ያሉን አረጋዊው አቶ ተስፋሚካኤል ተክለሃይማኖት ናቸው፡፡ የእናቶችም አስተያየት ከዚህ የተለየ አልነበረም፡፡

‹‹ሕዳሴ አቡነ አረጋዊ ዘ ደብረ ዳሞ›› በሚል መሪ ቃል እየተንቀሳቀሰ ያለው የአቡነ አረጋዊ ደብረ ዳሞ ገዳም ልማት ኮሚቴ፣ 1.5 ሚሊዮን ብር አካባቢ በሚደርስ ወጪ ካስገነባው የደረጃ መንገድ ሌላ ከአምባው ላይ ያለው ገዳሙ የወንዶች ብቻ በመሆኑ ወደ ላይ መውጣት ለማይፈቀድላቸው ሴቶችና በመወጣጫ ሐብል ወደ ገዳሙ የመውጣት ጉልበት ለሌላቸው ወንዶች ገዳሙ ከሚገኝበት አምባው ስር ፀበል እንዲያገኙ ከገዳሙ የሚወርድ ፀበል የሚጠራቀምበት ታንከር ተሠርቷል፡፡

ምእመናን ከታች ኾነው የገዳሙን ቅዳሴና መንፈሳዊ ትምህርት በሚገባ እንዲከታተሉ የሚያስችልም የድምፅ ማስተላለፊያ (ሳውንድ ሲስተም) ከማስገባቱም ሌላ አምባው ሥር ምዕመናንን ሊያስተናግድ የሚችል ማረፊያ ቦታ ሠርቷል፡፡

ደብረ ዳሞ ገዳም መንፈሳዊ እሴቶቹና ታሪካዊ ቅርሶቹ ተጠብቀው ምእመናን፣ የአገር ውስጥና የውጭ አገር ጎብኚዎች የሚጎርፉበት ኢትዮጵያዊ መስህብ ማድረግ አንደኛው የኮሚቴው ራዕይ መሆኑን የጠቆሙልን አቶ ተወልደ ብርሃን ታደሰ የአቡነ አረጋዊ ደብረ ዳሞ ገዳም ልማት ኮሚቴ ዋና ጸሐፊ ናቸው፡፡

የጥንታዊውና ታሪካዊው ደብረ ዳሞ ገዳም ለኢትዮጵያም ሆነ ለአኅጉሪቱ ያለውን ፋይዳ የሚያንፀባርቅ ምእመናንና ጎብኚዎች የሚማሩበትና የሚያውቁበት ሙዚየም በአምባው ሥር የመሥራት እቅዱን እውን ለማድረግም ኮሚቴው ጥቅምት 12 ቀን 2004 ዓ.ም. የመሠረት ድንጋይ አኑሯል፡፡

ሙዚየሙን ስዊዘርላንዳዊው ሚስተር ኩርት ፕፍስተርና ቤተሰባቸው እስከ 1.2 ሚሊዮን ብር ወጪ በማድረግ ለማሠራት ቃል የገቡ ሲሆን፣ ሥራውን ለማስጀመር 30,000 የአሜሪካ ዶላር መስጠታቸውን ኮሚቴው ይፋ አድርጓል፡፡

በምረቃውና የመሠረት ድንጋይ በተጣለበት ሥነ ሥርዓት ላይ የተገኙት በትግራይ ክልል የምሥራቅ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ገብረ መስቀል ታረቀ ባደረጉት ንግግር፤ ‹‹አቡነ አረጋዊ ደብረ ዳሞ ገዳም ማንነታችን፣ ታሪካችንና የጥንት አባቶቻችን ጥበብ የሚገልጽ፣ ከትውልድ ወደ ትውልድ እየተላለፈ የመጣ ቋሚ መለያ ቅርሳችን ነውና የተሟላ መሠረተ ልማት እንዲያገኝ ማድረግም ያስፈልጋል፤›› ብለዋል፡፡

የገዳሙ ልማት ኮሚቴ የበላይ ጠባቂው ፕሬዝዳንት ግርማ ወልደጊዮርጊስ በተወካያቸው በአቶ ገብረ እግዚብሔር ናይዝጊ የትግራይ ባህልና ቱሪዝም ምክትል ኃላፊ በኩል ባስተላለፉት መልእክት፣ ‹‹ገዳሙ በሥነ ሕንፃ ጥበብ ጥንታዊም እንደመሆኑ መጠን ለአገራችን ቱሪዝም አንዱ ትልቅ መስህብ ስለሆነ አገሩንና ታሪኩን የሚወድ ኢትዮጵያዊ ሁሉ ታሪካዊውን ገዳም በመጎብኘት እንዲማርና እንዲያጠና እንዲሁም ገዳሙ ጥንታዊ ታሪካችንንና ሥልጣኔያችን እየጠበቀ ከትውልድ ወደ ትውልድ እንዲያሸጋገር የበኩሉን ሚና ይጫወት፤›› ብለዋል፡፡

ደብረ ዳሞ ማነው?
ደብረ ዳሞ በሰሜን ኢትዮጵያ፣ ትግራይ በ535 ዓ.ም. የታነፀ ገዳም ነው፡፡ መጠርያ ስሙንም ያገኘው ከአምባው ሲሆን፣ ከባሕር ወለል 2216 ሜትር ከፍታ ላይ ይገኛል፡፡ ደብረ ዳሞ ገዳም እስካሁን ህልውናው የተጠበቀ ከ1400 ዓመት በላይ ዕድሜ አስቆጥሯል፡፡

ሕንፃ ቤተ ክርስቲያኑ የአክሱምን ሥነ ሕንፃ ጥበብ ተከትሎ የተሠራና የዚያን ዘመን አሻራ የያዘ ነው፡፡ ከአዲግራትና እንትጮ ከተሞች መካከል በጉሎ መከዳ ወረዳ የሚገኘው ገዳሙ የመጀመርያው የኢትዮጵያ ገዳምና የምንኩስና ሥርዓት የተጀመረበት ነው፡፡ ዙርያው ገደል የሆነ የጠረጴዛ ቅርጽ ወዳለው አምባ የሚወጣውና የሚወረደው በጠፍር ገመድ እየተንጠለጠሉ ነው፡፡

በአባ ገብረኢየሱስ ኃይሉ ድርሳን እንደተጻፈው፣ ደብረ ዳሞ አንድ ለተራራው መውጫ አንድ ለሰው እግር መርገጫ የሚሆነው ቦታ አይገኝበትም ነበር፡፡ ከዘጠኙ ቅዱሳን አንዱ የሆኑ አቡነ አረጋዊ (አቡነ ዘሚካኤል አረጋዊ) በ6ኛው ምእት ዓመት መጀመርያ የተከሉት ነው፡፡

እሳቸው ከምድራዊ ዓለም ርቀው ከሰው ማኅበር ተለይተው፣ በሕሊናቸው ወደ እግዚአብሔር እንደቀረቡት መጠን፣ እንዲሁም በቦታ ወደ ሰማይ የሚያቀርባቸው መካንን ፈለጉ፡፡ የደብረ ዳሞ ተራራንም አገኙ፡፡ በተራራው እግርጌ አንድ በዓት (ቦታ) አለ፤ እሱም በዓተ ኤሌም ይባላል፡፡ እዚያው ለመጀመርያ ጊዜ መጠጊያን አገኙ፡፡ ነገር ግን እርሳቸው የተመኙት ተራራው ጫፍ ላይ መውጣት ነበር፡፡ ከናታቸው ከእማሆይ አድናግ በጸሎትና በመንፈስ ንቃት የላይ ላዩን ሲያስቡ፣ አቡነ አረጋዊ ምኞታቸው እየጋለ በመሔዱ ወደ ላይ ለመውጣት በሞከሩ ጊዜ አንድ ትልቅ ዘንዶ ርዝመቱ ስድሳ ክንድ የሆነው ጭራቸውን ወደ ታች አወረደላቸው፡፡ እሳቸውም ይህ ነገር በእግዚአብሔር የታዘዘላቸውን መውጫ መሆኑን አመኑና በጽኑ ሃይማኖት አላንድ ስጋት የተዘረጋላቸውን ገመድ መሳይ ይዘው እስከ ደብሩ ጫፍ ወጡ፡፡ እዚያው ከደረሱም በመጀመርያ ከልባቸው የፈለቀ እግዚአብሔርን ማመስገን ሆነና ‹‹ሃሌ ሉያ›› በማለት ለእግዚአብሔር ምስጋናን አቀረቡ፡፡ ደብሩም በሌላ መጥርያው ደብረ ሃሌ ሉያ ተባለ፡፡

የአፄ ካሌብ ልጅ አፄ ገብረ መስቀል የደብሩን ቤተ ክርስቲያን አሠሩ፡፡ የቤተ ክርስቲያኑ ሕንፃም ከአክሱም የመነጨ የሥነ ጥበብ ፍሬ ነውና በቅርጹም ባተናነፁም ያክሱም ትምህርት መሆኑ ጐልቶ ይታያል፡፡ ቤተ ክርስቲያኑን በማሠራት ዕቃዎች ወደ ላይ ለማስወጣት አስፈላጊ ስለሆነ፣ ዓለቱ ላይ በውቅር የመሰላል ደረጃዎች ተጠርቦበት ነበር፡፡ ቤተ ክርስቲያኑ ከተፈጸመ ወዲያ ግን መሰላሉን በአቡነ አረጋዊ ትእዛዝ አፈረሱት፡፡ ቦታውም ወደ ዱሮው ሁናቴው ተመለሰ ይባላል፡፡

ዳሞ የሚለው ስያሜ አቡኑ ‹‹ዳህምሞ›› (አፍርሰው) ካሉት ተነሥቶ የተሰጠ ስያሜ ነው የሚሉ እንዳሉ ሁሉ፤ በሌላ መልኩም ይህ ‹‹ደመመ›› ከሚለው አንቀጽ የዕፁብ የመንክር ነገር መግለጫ ከሆነው ግስ የመጣ ሊሆን ይችላል የሚሉ አሉ፡፡

ደብሩን ለማየት ማናቸውም ሰው ወደ ደብሩ ሲወጣ ርዝመቱ 16 ሜትር ከሆነው ገመድ ተንጠልጥሎ ከላይ ተስቦ ይወጣዋል፡፡ ‹‹የሊፍት›› ፍልስፍና በደብሩ መነኮሳት የታቀደ ይመስላል፡፡ ደብሩ በለማበት ጊዜ ጫፍ ላይ እስከ ስድስት ሺሕ መነኮሳት፣ በግርጌውም እስከ ሁለት ሺሕ መነኮሳይያት የነበሩበት ነው፡፡ እዚያው ጫፍ ወጥቶ ዙርያው ያለውን አገር ለማየት የቻለ ሰው ዕድለኛ ያሰኘዋል፡፡

ደብረ ዳሞ የሥነ ጽሑፍና ሥነ ጥበብ ማዕከል
የኢትዮጵያ ሥነ ጽሑፍ ከድንጋይ ላይ ጽሑፍ ወደ ብራና ጽሑፍ ሽግግር ባደረገበት ዘመነ አክሱም የመጀመርያዎቹ ጽሑፎች ከተጻፉባቸው ቦታዎች አንዱ ደብረ ዳሞ ነው፡፡

በ4ኛው ምእት ዓመት በፍሬምናጦስ ጊዜ የተጀመረው ቅዱሳት መጻሕፍትን ከግሪክና እብራይስጥ ወደ ግእዝ መተርጐሙ የቀጠለውና የተስፋፋው በ5ኛውና በ6ኛው ምእት ዓመት ነው፡፡ በዚህ ጊዜ ኢትዮጵያውያኑ ሊቃውንት ከዘጠኙ ቅዱሳን ጋር በመሆን የመጽሐፍ ቅዱስ ልዩ ልዩ ክፍሎችንና የነገረ መለኮት (ቴኦሎጂ)፣ የሥርዓት መጻሕፍትን ከግሪክና ከሶርያ ቋንቋዎች መልሰዋል፡፡

የኢትዮጵያ ገዳማት የሚተዳደሩበትን ስለሥርዓተ ምንኩስና የሚያወሳው ‹‹ሥርዓት ወትእዛዝ ዘ ጳኩሚስ›› የተተረጐመው በደብረ ዳሞ እንደሆነ ይታመናል፡፡ በደብረ ዳሞ ከሥነ ጽሑፍ ሌላ የቁም ጽሕፈትና የሥዕል ትምህርት የሚሰጥበት ከተለያዩ የአገሪቱ አካባቢዎች የመጡ መነኮሳት ትምህርትና ሥርዓቱን ቀስመው በተለያዩ የኢትዮጵያ ግዛቶች በመዘዋወር አምሳያ ማዕከላትን ለመመሥረት ያስቻላቸው ነው፡፡

በአክሱም አካባቢ ተወስኖ የኖረውን ገዳማዊነት በብዙ የኢትዮጵያ ክፍላተ አገር እንዲስፋፋ መሠረቱን የጣሉት አባ ኢየሱስ ሞዐ (1211-1292) የተማሩት በደብረ ዳሞ ነው፡፡

የተማሩትን መንፈሳዊ ትምህርትና ሥርዓተ ገዳማት ደሴ አካባቢ በሚገኘው ሐይቅ ደሴት ቅዱስ እስጢፋኖስ ቤተ ክርስቲያን በመሔድ ባቋቋሙት የአንድነት ገዳም በማስፋፋት ብዙ ተከታዮችን ማፍራት ችለዋል፡፡

በ13ኛው ምእት ለተቋቋሙት ታላላቅ ገዳማት ምሥረታም መነሻ ሆኗል፡፡ ደብረ ሊባኖስ (ዜጋ መልን) የመሠረቱት አቡነ ተክለ ሃይማኖት፣ በጣና ሐይቅ የሚገኘው ዳጋ እስጢፋኖስን ያቋቋሙት አቡነ ኂሩተ አምላክ፣ የጋስጫ ገዳምን የወጠኑት አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ እና ሌሎችም የተገኙት ደብረ ዳሞ ከወለደው የሐይቅ እስጢፋኖስ የአንድነት ገዳም ነው፡፡

ደብረ ዳሞ በሥነ ጽሑፍ ታሪክ ውስጥ ጉልህ ሚና ተጫውቷል፡፡ በገድለ አቡነ ኢየሱስ ሞዐ እንደተጻፈው የደብረ ዳሞ መነኮሳት በ13ኛው ምእት ላይ ለጽሕፈት ሥራ ትኩረት ሰጥተው ነበር፡፡ አቡነ ኢየሱስ ሞዐ ቁም ጽሕፈት በሚገባ ተምረው አራቱን ወንጌል (ማቴዎስና ማርቆስ፣ ሉቃስና ዮሐንስ) ጽፈው ለገዳሙ ሰጥተዋል፡፡ ይህ ወንጌል በውስጡ ሥዕል ስለነበረው ለዘመኑ ኪነ ጥበብ አንድ መለኪያ ነው፡፡

አናባቢ የሌለው በጥንታዊ ግእዝ የተጻፈ የድንጋይ ላይ ጽሑፍም የተገኘበት ነው፡፡ ‹‹አነ ጸለየከ›› [እኔ ጸለይኩ] የሚለው ጽሑፍም ኢትዮጵያውያን ክርስትናን በተቀበሉበት ጊዜ በቦታው እንደነበሩ አመልካች መሆኑ የታሪክ ምሁራን ጠቁመዋል፡፡

አፄ ገብረ መስቀል፣ ‹‹አክሱምሂ ቤተ መንግሥትነ
ዳሞሂ ቤተ ጸሎትነ›› (አክሱም ቤተ መንግሥታችን ዳሞ የጸሎት ቤታችን) በማለት የተናገሩትም ቤተ ክርስቲያኑ በቅዱስ ያሬድ ማህሌታይ ጥዑመ ዜማ በተመረቀበት ጊዜ ነው፡፡

አቡነ አረጋዊ ከአፄ ገብረ መስቀል ጋር በመኾን በመጀመርያ በጎንደር ዙር አባ (ዙራምባ) ከዚያም በደቡብ ኢትዮጵያ አርባ ምንጭ ብርብር ማርያም ድረስ ማስተማራቸው ይተረካል፡፡

this coming week our special gust mahlet demere with new album , የአበራ ለማ የዲቪዲ ግጥሞች

******
አበራ ለማ ነባር ባለቅኔ፣ ደራሲ፣ ጋዜጠኛና ሐያሲ ነው፡፡ ‹‹ኩል ወይስ ጥላሸት››፣ ‹‹የማለዳ ስንቅ››፣ ‹‹አውጫጭኝ››፣ ‹‹ሽበት››፣ ‹‹መቆያ››፣ ‹‹ሕይወትና ሞት››፣ የማለዳ ስንቅ፣ ሞገደኛው ነውጤ ወዘተ በተሰኙ መጻሕፍቱ የምናውቀው ደራሲ፣ ‹‹እውነትም እኛ . . . ›› በሚል ርእስ አዲስ የግጥም ቪዲዮ መድበል በዲቪዲ ይዞልን ቀርቧል፡፡ 25 ግጥሞች የተካተቱበት መድበሉ ምስልና ድምፅ ተቀናብረው የቀረቡበት የዘመኑ ቴክኖሎጂ ውጤት ነው፡፡ በዲቪዲው ላይ ከቀረቡት ግጥሞች መካከል በጥቂቶቹ ላይ የተሞከረውን ኪናዊ ምልከታ እነሆ! ባለቅኔው ከበደ ሚካኤል፣

‹‹ፈለቀሽ የተገኘሽ ከሹበርት ራስ
ከቤቶቨን ናላ ከሞዛርት መንፈስ›› ብሎ ያወደሳትን ሙዚቃ፣ አበራ ለማ ‹‹እሱን አኑሩልኝ› በሚል ርእስ እንደሚከተለው ዘምሯታል፡፡
‹‹መሰንቆን ጥሩልኝ – ክራርን አምጡልኝ
ዋሽንትን ተውልኝ – እሱን አኑሩልኝ
እሩቅ ነው – መንገዱ
እርብትብት ነው -ሆዱ
ብዙ ነው – ትውልዱ
ጥቂት ነው – ዘመዱ››
እሱን አኑሩልኝ ‹‹መወድስ›› ቅኔ ናት፡፡ መወድሱ የቀረበው ለባህል የሙዚቃ መሣርያዎቻችን ለመሰንቆ፣ ለክራርና ለዋሽንት ነው፡፡

የግጥሙ ሠራዊት አዝማች በሙላት ሦስት ጊዜ ተሰናኝቷል፡፡ በዚህ ግጥም መውድስ የቀረበላቸው የሙዚቃ መሣርያዎችም እያንዳንዳቸው አንድ አንድ አንጓ ተሰይሞላቸው በሦስት አንጓ ይደመጣሉ፡፡ ይህ በሦስት ምድብ የመከፋፈል ዘዬ የግጥሙን ዜማ፣ ምትና ምጣኔ አስተካክሎታል፤ አሳምሮታል፡፡ ግጥምን ከሌሎች የሥነ ጽሑፍ ዘሮች የሚለየው ለይዘት ብቻ ሳይሆን ለቅርጽም መጠበቡ ነው፡፡ ይህ ቅርጻዊ ተመጣጥኖ (ባላንስ)እና ውህደት (ሐርመኒ) ታዲያ ሲነበብ፣ ለዓይን ሲደመጥ፤ ለጆሮ የተስተካከለና የሚጣፍጥ ምስል ወ ድምፅ መከሠቱ እንዲሁ በአጋጣሚ የመጣ ሳይሆን፣ ገጣሚው ለዜማ ካለው ስሱነት (ሴንሲቲቪቲ) የተወለደ መሆኑን ልብ ይሏል፡፡

‹‹የመሰንቆው ጭራ – ያ ጥምር ያ ድምር
እራሱን ዘንግቶ – ሌላን የሚያዘክር
ተናግሮ አናግሮ
ውስጠትን ኮርኩሮ . . .››
የመሰንቆው ጭራ በሰውኛ ዘይቤ እንደ ቅን ጎልማሳ የራሱን ነገር ቸል ብሎ ሌሎችን የሚያዘክር፣ ውስጠትን በስውር ጣቶቹ የሚኮረኩር የእምባ ቋትን የሚፈታና ግምባርን በቁጣ የሚያኮሳትር፣ ተናግሮ የሚያናግር ሆኖ በገጣሚው እይታ ተሥሏል፡፡

እነ ክራርና ዋሽንትም እንደየብጤታቸውና እንደየባሕርያቸው ተወድሰዋል፡፡
‘ክራር ነኝ! . . .’ ይለኛል – ደም ሥሩን አክርሮ
ስሜቴን ለማክረር – ረቂቅ ኪኑን ጭሮ . . .
ሕይወቴን ሊያወጋኝ – ሕይወቱን አውግቶ
‘ያዝ አርገኝ! . . .’ ይለኛል – ሌሊቱን አንግቶ
ሽሜን አጎፍሮ – ጉብል አሸብቶ . . .››
በተለይ በመጀመርያ የተጠቀሱት ስንኞች እጅግ የሰመሩ የዜማን ረቂቅ ውበት፤ የሙዚቃን ዓለም አቀፋዊነት ገጣሚው ያመላከተባቸው ውብ ገለጻዎች ናቸው፡፡

ገጣሚ የቋጠረውን፤ የታዘበውን የተደመመበትን ፍሬ ነገር በስንኝ ቀምሮ ሲወልድ የሚያስተላልጸው ቁምነገር ተደማጭ ይሆንለት ዘንድ፤ የተለያዩ ዘይቤዎችን ይጠቀማል፡፡ ለዋሽንት ውዳሴ የተሰደሩት ስንኞች በአነጻጻሪ ዘይቤ ተኩለው ጎልተውና ደምቀው እንደሚከተለው ይነበባሉ፡፡

‹‹ክንድ አይሞሌው ዋሽንት – ቀጭኑ ረቂቁ
ትንፋሽ ይለግሳል – ባለትንፋሽ ስንቁ
እንደናት አልቅሶ – እንደ ጅረት ፈሶ
ሰተት ብሎ ገብቶ – እንዳዲስ ፍቅረኛ
ልብን ያማልላል አቅፎት እየተኛ . . .››
በነዚህ ስንኞች ውስጥ የዋሽንት ልብ ሰራቂ ዜማ ቁልጭ ባለ ሁኔታ ተገልጿል፡፡ በተጠቃሎ ‹‹እሱን አኑሩልኝ›› ዜማን በዜማ የሚያወድስ ግጥም ነው፡፡

ሌላው በመድበሉ ውስጥ የተካተተ ፍርሃት የተሰኘ ፖስተራዊ ግጥም ነው፡፡ ገጣሚው ሰበበ ድርሰቱን እንደሚያወጋን ከሆነ የሁለት ሁነቶች ግጭትና በግጭቱ ውስጥ ያለ አንድነት ነው፤ ይህንን ግጥም የወለደው፡፡ ከጦር ሜዳ ሸሽቶ ወደ እናቱ ቤት የሚሔድ አንድ ዋቶአደር እና በመስኮት አሻግረው የሚመለከቱ የፈሩ አዛውንት፡፡ ታዲያ አበራ እነዚሀን ሁነቶች መነሻ አድርጎ የቋጠራቸው ስንኞች በከፊል እንደሚከተለው ይነበባሉ፡፡

‹‹ያ መረቡ ልቤ – ረገበ እምቢ አለ
አንድ ራሱን ማስገር – አቃተው ዋለለ
ፍርሃቴ ስጋቴ – በላዬ ነገሠ
ውስጥ አንጀቴን ምሶ – ቤቴን አጣረሰ››
በነዚህ ስንኞች የወንድነት፣ የወኔ፣ የአልበገር ባይነት መጠቀሻ የሆነው ልብ፣ የረገበ መረብ ሆኖ አንድ ራሱን ማስገር ተስኖት ሲዋልል እናስተውላለን፡፡ ፍርሃት በሰብእና ላይ ነግሦ ቤትን ሲያጣርስ እንታዘባለን፡፡ ቤት በዚህ ዐውደ ንባብ ተምሳሌትነቱ የአንድ ሰው ግላዊ ሕይወት፤ የአንድ ማኅበረሰብ ሕልውና ከፍም ሲል የአንድ አገር እጣ ፈንታ ሆኖ በጥቂት ስንኞች የተወሳሰቡ ሁነቶች የተጣመሩበትና በረቀቀ ሁኔታ የደመቁበት ግጥም መሆኑን ልብ እንላለን፡፡ ‹‹ይሄው ግጥም እንደሚከተለው ይቋጫል . . .
‹‹እናንተም እንደኔው – ፍርሃት ካባዣችሁ
ጠመንዣው ዣንጥላው – ውሻው ለምናችሁ?››
ኤሌጂ (Elegy) [እንጉርጉሮ?] በሞት የተለየን ሰው የምንዘክርበት፣ ሥራዎቹን፣ ምግባሮቹን፣ አኗኗሩንና አስተሳሰቡን በማውሳት ያንን ሰው የምናስታውስበት የሥነ ግጥም ዓይነት ነው፡፡ ‹‹ናጋቲካ ያጋሼኮ›› በተሰኘ ግጥሙ አበራ ለማ የሎሬት ጸጋዬ ገብረ መድኅን ዐቢይ ሥራዎች በመጥቀስ፣ በሥጋ የተለየንን ባለቅኔውን ያናግረዋል፤ ይሞግተዋል፤ ይማጸነዋል፡፡ በእርግጥም ብላቴን ጌታ ጸጋዬ ታላቅ ባለቅኔ ነውና ሌሎችም በርካታ የጥበብ ሰዎችም ስንኝ ቋጥረውለታል፡፡ ወደ አበራ ለማ ከመግባታችን በፊት የደብረ መላእክቱ ባለቅኔ ቦጋለ ዳኘ ‹‹ጠብታ›› በተሰኘ ርእስ በታተመ የግጥም መድበል ውስጥ፤ ‹‹ማስታወሻ ለብላቴን ጌታ ሎሬት›› በሚል ርእስ ባካተቱት ግጥም የቋጠሩትን ስንኝ እነሆ . . .

‹‹ጸጋዬ ወለልቱ ያ ኢልመ ቀዌሳ
ሜ ወለሎ ቡሲ አኩመ ከሌሳ
ማሎ ሀረ ቡሊ ማልቱ ሲጀርጀርሳ
ቦዴ ዴሙወያ ኤኙ ሲአምቢሳ?››
አፋን ኦሮሞን ለማያውቁ ግጥሙ በተዛማጅ ትርጓሜ ሲቀኝ ይህን አንድምታ ይዟል፡፡
‹‹ጸጋዬ ወልደ ቀዌሳ አንተ ባለቅኔ
እስቲ እንደ ትናንቱ ዝረፍልን ቅኔ
ዛሬን እደር እንጂ ምን ያስቸኩልሃል
ኋላ መሄድ መልካም፣ ማንስ ያስቀርሃል?›› እንደማለት ነው፡፡
በተመሳሳይ ሁኔታ አበራ ለማም፣ ሎሬት ጸጋዬ በተወለደበት አካባቢ የሚነገረውን ቋንቋ ኦሮሚፋን ተጠቅሞ ለብላቴን ጌታ ያሟሸውን ሙሾ ርእስ ‹‹ናጋቲካ ያጋሼኮ›› በአማርኛ ‹‹ደህና ሁንልኝ ጋሽዬ›› እያለ ሰይሞታል፡፡

ታዲያ በዚህ እንጉርጉሮ ግጥም እሱም ጋሽዬ ያለውን መንገደኛ ባለቅኔ ሥራዎች በማንሣት ‹‹ምነው ቸኮልክ?›› ይለዋል አበራ፤ የሐዘን፣ የመለማመጥ፣ የመቆጨትና የመማጸን ቅላጼ በዋጠው አንደበቱ፡፡
‹‹ኧረ ሞረሽ በሉ – ኧረ በልግን ጥሩ
የከርሞ ሰው ጠፋ – እናት ዓለም ጠፋ
መች እንዲህ ነበረ – ውላችን ቃላችን
ሽልማት ሆነ እንዴ – ላንተ መጮሃችን?
ሽልማት ሆነ እንዴ – ከል መልበሳችን?
ሽልማት ሆነ እንዴ – ቱቢት ስፌታችን
የቀለሙ ቀንዲል – ፈሰህ ማንባታችን?››
በተለይም ብላቴን ጌታ ሎሬት ጸጋዬ ለአገሩ ለወገኑ ያለው ፍቅር የተገለጸባቸው ስንኞች እጅግ በጣም ገላጭና ባለቅኔውን በእርግጥም እንድናስታውሰው የሚያደርጉ ኃያል ተግታዎች ናቸው፡፡

‹‹ሁሉም እኩል ለሱ – ኦሮሞው አማራ
ትግሬና ሻንቂላ – ሲዳሞ ጊሚራ
አኝዋኩ ወይጦው – ቅማንቱ አፋሩ
ሁሉም ለብላቴን – ያንድ እናት ልጆች
ለሱም ወንድሞቹ – ያውም መንትዮች››
ይህ ግጥም የተነበበት ቅላጼ ከግጥሙ ንባብ ጋር ተያይዞ የቀረበው ምስልና ሙዚቃ ተደራሲን ወደ ጥልቅ ሐዘን የሚከት፣ የቁዛሜውን፣ የመለየቱን ድባብ የሚፈጥር፣ ድንቅ ቅንጅት መሆኑም ሌላው ጠንካራ ጎኑ ነው፡፡

የመድበሉ መጠርያ የሆነውና ሌላው ዓቢይ ግጥም ‹‹እውነትም እኛ ልዩ ነን›› የተሰኘው ነው፡፡ ግጥም ካለው የቁጥብነት ባሕርይ አኳያ የግጥም ርእሶች እጥር ምጥን ቢሉ በአንድ ቃል ቢቋጠሩ ይመረጣል፡፡ አንዳንዴ ግን ገጣምያን ሆን ብለው ለመልእከታቸው ማስተላለፊያ ለጭብጣቸው ማጉሊያ ይሆናቸው ዘንድ እንዲህ ዓይነቱን ሐረጋዊ ርእስም ያወጣሉ፡፡ እውነትም ልዩ ነን በእርግጥም ቀልብን የሚይዝ የማንበብ ወይም የመድረስ ጉጉትን የሚያጭር ርእስ ነው፡፡ በተለይ እንደ ኢትዮጵያዊ ዓይነት ኩሩ ሕዝብ እውነትም እኛ ልዩ ነን የሚል መፈክር ሲያጋጥመው የለመደውን ለማንበብ መቋመጡ እሙን ነው፡፡

በታሪክ ለ 27 ጊዜያት በወራሪዎች ተደፍረን፣ ጠላትን አይቀጡ ቅጣት ቀጥተንና አሳፍረን የመለስን ብቸኛ አፍሪካውያን፣ እውነትም እኛ ልዩ ነን፡፡ አሁን በሥልጣኔ የቀደሙ ሕዝቦች በዋሻና በገደል እርቃናቸውን እየኖሩ፣ ፀሐይና ጨረቃን በሚያመልኩበት ወቅት፣ ሕንፃ ቤተ ክርስቲያን ገንብተን እግዚአብሔርን ስናመልክ የኖርን ሃይማኖተኛ ሕዝቦች እውነትም እኛ ልዩ ነን፡፡ ከዘመናት በፊት የአክሱምን ሐውልት አንጸን ለዘመናዊ ሕንፃ ግንባታ ፈር ቀዳጅ የሆን የቀደምት ሥልጣኔ ባለቤቶች እውነትም እኛ ልዩ ነን፡፡ እንግዳ ተቀባይ ትሁትና ወዘተረፈ . . . እውነትም እኛ ልዩ ነን፡፡

የአበራ ለማ ብርእም እውነትም እኛ ልዩ ነንን ሲከትብ የተቆጣ ያመረረ ይመስላል
‹‹ላለመስማማት ተዋደን
ላለመዋደድ ተስማምተን
ላለመኗኗር ተቧድነን
ላለመፋቀር ተቃቅፈን
ላለመጋባት ተጫጭተን
ይሄው ዞረን ዞረን እዚያው ነን!››
ላለመስማማት መዋደድ፣ ላለመኗኗር መቧደን፣ ላለመፋቀር መተቃቀፍና ላለመጋባት መተጫጨት በአያዎ (ፓራዶክስ) ዘይቤ የተሰናኙ የግጥሙን አጠቃላይ መልእክት የቋጠሩ ምርጥ ስንኞች ናቸው፡፡
‹‹አጀብ ዘመናችንን ቸብችበን
በኪሳራችን ቶጅረን
የመጠላለፍ ጽዋችንን
ተራበተራ ጨልጠን
ይሄው ሃቻምናና ተነበርንበት
እዚያው ዞረን ዞረን ግጥም አልንበት››
ይህ እንግዲህ የጠነከረ ሒስ፣ የመረረ ግሳጼ፣ ያልተድበሰበሰ ተቃውሞ ነው፡፡ ሐምሌ 23 ቀን 2000 ዓ.ም. በዳግም አርትኦት የተጻፈው እውነትም እኛ ሁለንተናዊ ጭብጥ ይዞ የተነሣ፣ በትንሽ ቀለበት ሲስተዋል በአንድ ንኡስ ቤተሰብ፣ የጓደኝነት ማኅበር፣ የሙያ ክበብ ወዘተ. ውስጥ ሊከናወን የሚችልን ተገቢ ያልሆነ የመጠላለፍ አባዜ ከፍም ሲል በአንድ ማኅበረሰብ ወይም አገር ውስጥ የሚታዘቡትን ዓይነት የማን አለብኝነትና የእኔ ብቻ ልግነን ባይነት ብልግና የማልቀስ፣ በእያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ላይ የተሰነዘረ ተግሳጽ ነው፡፡ (የሚሰማ ቢኖር እንዲሉ)

ታዲያ ገጣሚው ትዝብቱን የሚያጋራን እያዋዛም ነው፡፡ እየመጸተም . . .
‹‹እንግዲህ ማን አለ እንደኛ
ዞሮ ዞሮ ተነበረበት የተኛ
ማተብ ጠባቂ ሐቀኛ
ብርቅም አይዶለን እኛ?››
ይህ ጽሑፍ በሎስ አንጀለስ (አሜሪካ) ነዋሪ የኾኑት አቶ ዓለማየሁ ታዬ በእማኝ ዘጋቢነት (Eye Reporter) ያቀረቡት ነው፡፡

***********

Dj essatu from Chicago

Legendary is not enough to describe one of my biggest heroes “Maritu Legesse” a.k.a “Ye Bati Nigest” Queen of Bati. I don’t think she’s a mere Queen of Bati, in my opinion she’s the undisputed Queen of Bahil in all the four Ethiopian modes.Her unique voice, custom fitted to the Ethiopian modes is delivered straight to the listener’s ears in such a way that it makes one fall head over heels in love with our music.

Words can’t express how i felt when i saw her coming out of Ledet in Atlanta, I froze there, I think time has stopped moving. I was out of breath, her aura and charisma are so powerful, I mean this is Maritu the Bahil Music Royalty. She saw me and  i was like someone who got struck by a lighting. She noticed my camera and the huge EF 70-200 Lens attached to it, so she looked at me and asked when are you going to take my picture with your camera? I was speechless and stun, you know that feeling you have when you meet someone you admired and loved so much much, yup that feeling that makes you feel like a little kid. Suddenly, I found myself walking up to her, hugging and kissing her. I don’t know if she realized what she means to this poor music fan’s soul, I hope she felt it. I don’t usually trust people with my camera, but in this case the first individual I saw, I immediately handed my camera and I asked him can you please take our picture? I learned that she doesn’t have any shows in ATL 2011. She only came to support and encourage her fellow Bahil artists. Later on that night, like an excited kid I was showing my photo with Mari to Eyayu Bele, Kuribachew W. Mariam and other Bahil artists whom all related to me that “Yeah she stopped by my show earlier and showed me some love, how gracious of her”. Maritu already in a class of her own, but this act here puts her in a higher class. Her voice is such an iconic and synonymous with Deep Roots culture that I believe she was born to sing the four scales: Tizita, Bati, Ambassel & AnchihoyeMaritu was given the title of Ye Bati Nigest because her voice took the listener to Bati – the ‘melting pot’ of Ethiopian people & music. Bati is sang by millions, but Maritu’s version remains the Greatest version ever. Maritu Legesse’s voice, unlike many other Ethiopian singers who exclusively use equal tempered tuning, evokes the ancestral tuning heritage of the washint, masinko and kereto. Maritu’s untempered voice is a living reminder of a fast disappearing art form. Her voice unlike other Ethiopian modern musicians who used the modern equal temper tuning for their voice, her voice is tuned to the natural Ethiopian tuning and  it remains original to the core of Deep Ethiopian Roots.

Her Last album produced by Abiyou Solomon was a masterpiece that displayed the above traits. Legendary Masinko player Setngne Atenaw accompanied her, to the producer’s credit, the masinko was given a much more prominent role than the normally ubiquitous and offensive synthesizer, dancing around, behind, with and ahead of her voice, sometimes callings and sometimes responding, in general dancing with her in a delighful way. Neway Debebe sang the background vocals, now this is a high respect when an artist in Neway’s caliber sings a backup vocals for another artist. Maritu is a national treasure, she’s to Ethiopian Bahil music what Tilahun Gesesse is to vocalist, Getachew Mekuria to the saxophone, Muluken Melesse to ballads, Deregie Mekonen to producing, Setengne Atenaw to Maskino, Kuribachew W. Mariam to dancing, Selam Seyoum to the Guitar Mahmoud Ahmed and Aster Aweke as our musical ambassadors worldwide, and of course Teddy Afro to modern music these days.

In summary, Meeting Maritu Legesse was the high light of ATL 2011 for me. I forgot about all the heat and humidity in that city. As i type this I’m still happy and even more happy to share my unforgettable expiernce with you guys.  

የቃኘው ጦር ሙዚየም ተከፈተ

• ፔንታጎን የጠፋውን የቃኘው የልዩ ጀግንነት ሽልማት ተካ

ከስድሳ ዓመት በፊት በተቀሰቀሰው የኮርያ ጦርነት ሳቢያ በተባበሩት መንግሥታት ጥላ ሥር የዘመተውን የኢትዮጵያን ቃኘው ሻለቃ ገጽታ የሚያሳይ የጦር ሙዚየም ባለፈው ቅዳሜ ተከፈተ፡፡

ቃኘው ሻለቃ ያኔ ለጀግንነቱ የተሸለመውንና ከ50 ዓመት በፊት የጠፋበት የልዩ ጀግንነት ሽልማቱን የአሜሪካ መከላከያ መሥርያ ቤት ፔንታጎን ምትኩን አበርክቷል፡፡

በአፍንጮ በር ፓርክ የሚገኘውን ቃኘው ሙዚየም የመሠረተው የኢትዮጵያ ኮርያ ዘማቾች ማኅበር (ኢኮዘማ) ሲሆን፣ ሙዚየሙ በጦርነቱ የተሳተፈውን ቃኘው ሻለቃ ከዓለማቀፉ ሠራዊት ጋር የነበረውን የኃይል አሰላለፍ፣ የጦርነቱን ገጽታ አመልካች የሆኑ ታሪካዊ ቅርሶች፣ ዘማቾች በወቅቱ የተጠቀሙባቸው ቀላልና ከባድ መሣርያዎች፣ እንዲሁም አልባሳት ተካትቶበታል፡፡ ቃኘው ሻለቃ በ1943 ዓ.ም. ከአዲስ አበባ ወደ ሩቅ ምሥራቋ ኮርያ ከከተተበት ጊዜ አንሥቶ የተነሡ ልዩ ልዩ ፎቶግራፎችም የሙዚየሙ አካል ናቸው፡፡ የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት መንግሥት ጦር ኃይሎች ጠቅላይ አዛዥ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴና የክብር ዘበኛ አዛዦች የነበሩት እነ ጄኔራል ሙሉጌታ ቡሊ፣ ጄኔራል መንግሥቱ ነዋይ ፎቶግራፋቸው ከሚታዩት መካከል ይገኙበታል፡፡

የኢትዮጵያ ነፃነትና ክብር ያስጠበቁ ጥንታውያን ጀግኖች የሚያሳዩ ሥነ ጥበባዊ ውጤቶችም አሉበት፡፡

ቃኘው ሙዚየም በተመረቀ በማግሥቱ ግንቦት 28 ቀን 2003 ዓ.ም. በአፍንጮ በር ፓርክ በቆመው ሐውልት ፊት ለፊት፣ 60ኛ ዓመቱ በታላቅ ሥነ ሥርዓት ሲከበር፣ የኢትዮጵያ ቃኘው ሻለቃ ላደረገው ተጋድሎና ለተጎናጸፈው ስኬት በወቅቱ የተሸለመውና ከግማሽ ምእት ዓመት በፊት የጠፋበት ሽልማት ዳግም የአሜሪካ መከላከያ መሥርያ ቤት ፔንታጎን በአምባሳደሩ አማካይነት አበርክቷል፡፡

የአሜሪካ አምባሳደር ዶናልድ ቡዝ፣ በዘመኑ ኮርያ በዘመተው የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት መንግሥት ሰንደቅ ዓላማ ላይ ልዩ ሽልማቱን አጥልቀዋል፡፡ በ1953 በነበረው ግርግር የጠፋው ሽልማቱ፣ በ1943 ዓ.ም. ወደ ሩቅ ምሥራቅ ኮርያ የዘመተው የኢትዮጵያ ቃኘው ሻለቃ እንደ አንድ ወጥ ወታደራዊ ተቋም ባካሔዳቸው ከፍተኛ ውጊያዎች ሰንደቅ ዓላማው በአሜሪካና በኮርያ መንግሥታት ሽልማቶች መጌጡን መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡

በተያያዘ ዜናም፣ ኮርያ ሪፐብሊክ ዘንድሮ 2 ሺሕ 400 ኢትዮጵያውያን የኮርያ ዘማቾችና ቤተሰቦቻቸውን እንደምትጋብዝ አስታውቃለች፡፡ የኮርያ ጦርነት መቀስቀስ 60ኛ ዓመት አጋጣሚ የኮርያ ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት ሊ ሚዮንግ ባክ ባስተላለፉት መልእክት ላይ እ.ኤ.አ. ከ1975 ጀምሮ ‹‹ኮርያን እንደገና ማየት›› በተሰኘው ፕሮግራም መሠረት፣ የኢትዮጵያ ኮርያ ዘማቾችን በየዓመቱ መጋበዝ መጀመሩን አስታውሰው፣ ዘንድሮ 2,400 የኮሪያ ዘማቾችና የዘማች ቤተሰቦች ወደ አገራችን እንጋብዛለን ብለዋል፡፡

ፕሬዚዳንቱ በዚሁ መልእክታቸው ለኢትዮጵያውያኑ የቃኘው ሻለቃ አባላት፣ ‹‹ሊገለጥ የሚያስቸግር የጦርነትን ሰቆቃ ለተቋቋመው ጀግንነታችሁ ሰላም እንላለን፡፡ ነፃነታችንና ህልውናችንን የተፈታተነውን ጥቃት በጽናት ስለመመከታችሁ ክብር ለናንተ ይሁን እንላለን፡፡ ለዘለዓለም እውነተኛዎቹ ጀግኖቻችን እንደሆናችሁ የምትኖሩ ሲሆን፣ እኛም እናንተን ሁሌም ለማኩራት የሚቻለንን ሁሉ ከማድረግ የማንቆጠብ መሆናችንን እንገልጻለን፤›› ብለዋል፡፡

ኢትዮጵያ የመጀመርያዋና ብቸኛዋ አፍሪካዊት ወደ ደቡብ ኮሪያ ምድር 6037 እግረኛ ሠራዊት ያዘመተች ስትሆን፣ በጦርነቱ የተሰዉ 122፣ የቆሰሉ ደግሞ 536 ወታደሮች ናቸው፡፡ አንድም ወታደር አልተማረከባትም፡፡

የመታሰቢያ በዓሉ በተከበረበት አጋጣሚ ከቃኘው ሻለቃ ጋር አብረው በዐውደ ግንባሩ የተሳተፉ፣ ሁለት የኔዘርላንድስ አረጋውያን መኰንኖች የ87 ዓመቱ ኪስ ሞሻገን እና የ83 ዓመቱ ኮሎኔል ሸሩደር በሥነ ሥርዓቱ ተገኝተው በሐውልቱ ሥር አበባ አስቀምጠዋል፡፡ ኔዘርላንድስ እንደ ኢትዮጵያ ሁሉ አንድም ወታደር እንዳልተማረከባትም ተነግሯል፡፡

ኢትዮጵያውያኑ የኮርያ ዘማቾች ከነሜዳሊያቸው ተንቆጥቁጠው በታዩበት፣ የተሰውት አርበኞች ቤተሰቦችም በተገኙበት አከባበር ላይ አምባሳደሮችና የተለያዩ አገሮች ወታደራዊ አታሼዎች ታዳሚዎች ነበሩ፡፡

ከፍተኛ ሹማምንቱ በ1998 ዓ.ም. በተተከለው ሐውልት ጉንጉን አበባ ሲያስቀምጡ፣ በተሰውት ጀግኖች መታሰቢያ ትክል ድንጊያ ላይ ደግሞቤተሰቦቻቸው የአበባ ቀንበጥ አኑረዋል፡፡

የአሜሪካ፣ የኔዘርላንድስና የሌሎች ኤምባሲዎች ወታደራዊ አታሼዎች ከመኰንናዊ ልብሳቸው ጋር እንደተገኙት ሁሉ፣ የኢትዮጵያ መከላከያ ኃይል መኰንኖች ተገኝተው ቢሆን ኖሮ ምንኛ ባደመቀው ነበር፡፡

ከጣይቱ ሆቴል እስከ ጃዝ አምባ

በኢትዮጵያ የመጀመርያው ሆቴል በፊት እቴጌ ቆይቶም ጣይቱ ሆቴል የተባለውና የእንጦጦ ማርያም ቤተክርስቲያን ምረቃ የሚያያዙበት ታሪክ አላቸው፡፡

ጳውሎስ ኞኞ ‹‹አጤ ምኒልክ›› በሚለው መጽሐፉ፣ የመጀመርያ ስለሆነው ሆቴል አጀማመርና በዚያ ጊዜ ኅብረተሰቡ ሆቴልን ለመልመድና በሆቴል ለመመገብ ያሳየውን እንቢተኝነት አስፍሯል፡፡

እቴጌ ጣይቱ  እንዲያ በልመናና በብሉልኝ ልምምጥ ዛሬ እንዲሁ በተአምር ተነሥተው አሁን ያለውን የሆቴሉን ሁኔታ ቢያዩ ከመገረም በላይ እንደሚሆንባቸው መገመቱ ለምን አያስብልም፡፡

በተለይ ባለፈው ሳምንት በጣይቱ ሆቴል የሚከፈተውን የጃዝ አምባን ክለብ በጭራሽ አያስቡትም ይሆናል፡፡

የጃዝ ክለቡ የአፍሪካ ጃዝ ሙዚቃ ትምህርት ቤት አካል ሲሆን፣ ለሙዚቃ አፍቃሪው በሳምንቱ ቀናት ሁሉ መድረክ ላይ በባንድ የሚቀርቡ ሙዚቃዎችን ለማስደመጥና እንደ ምግቡ ሁሉ የሙዚቃውንም ማዕድ ለማቋደስ ተሰናድቷል፡፡

ክለቡ በጣይቱ ሆቴል ቦታ ውስጥ ተሰጥቶታል፡፡ 150 ያህል ሰዎችንም የመያዝ አቅም አለው፡፡ ቦታው የዱሮ መልኩን በማይለቅ መልኩ የታደሰ ሲሆን፣ የምንጣፍ ቀለም፣ የወንበሮቹ አቀማመጥ፣ መድረኩ፣ አዲሱ ባር ሁሉ ተመልካቹ የዱሮውን ጊዜ እንዲያስታውስ ለማድረግ እንዲችሉ የታሰበባቸው ይመስላሉ፡፡

ጣይቱ ሆቴል በ1898 ዓ.ም. ሲቋቋም አጀማመሩም የእንጦጦ ማርያም ቤተክርስቲያንን ሊመርቅ የመጣው ሕዝብ ምግብና ማረፊያ ስለታጣለት ለዚያ የሚሆነው መላ ሲፈለግ ነበር፡፡ አጤ ምኒልክ የሌሎችን አገሮች ልምድ ሲያጠያይቁ ሆቴል ስለሚባለው ሐሳብ ይሰማሉ፡፡ በ1898 ዓ.ም. የመጀመርያው ሆቴል ‹‹ሆቴል›› በሚል ስያሜ ሥራውን ጀመረ ያም የአሁኑ ጣይቱ ሆቴል ነው፡፡

‹‹በዛን ጊዜ ወጥቶ መብላትም ሆነ ከፍሎ መብላት ነውር ስለነበር ሆቴሉን የሚጠቀምበት ሰው ጠፋ፡፡ በዚህም ምክንያት አጤ ምኒልክ የመጀመርያው የሆቴል ተገልጋይ ሆኑ፡፡  በመጀመርያው ቀን አጤ ምኒልክ መኳንንቱን የጋበዟቸው ሲሆን፣ ያወጡትም  30 ብር ነበር፡፡ እንዲህም እያለ መኳንንቱ ምኒልክን እየጋበዙ ምኒልክም መኳንንቱን እየጋበዙ የሆቴልን ምሥረታ ሀ ብለው ጀመሩት፡፡›› በማለት ጳውሎስ ኞኞ የሆቴሉን አጀማመር ከትቧል፡፡

ከዓመታት በኋላ የሆቴሉ አካባቢና ፒያሳ ሰው የሚውልበት ሥፍራ ሆነ፡፡ በተለይም በአምስቱ ዓመታት የጣሊያን ወረራ ጊዜ የተለያዩ ሆቴሎችና ክለቦች መምጣት ሲጀምሩ በተለምዶ እንደሚታወቀውም ፒያሳ የጆሊዎች መዋያ ሆነ፡፡

በተለይም በ1960ዎቹ የነበሩት ክለቦች እነውቤ በረሀ፣ በዚያን ጊዜ ለነበሩት አርቲስቶች፣ ደራሲዎች፣ ስፖርተኞችና ጥበበኞች ሁሉ መገናኛ ነበር፡፡

ነጋ አስፍሃ፣ የጃዝ አምባ አስተዳዳሪ፣ ፒያሳ አካባቢ ተወልዶ ማደጉ በዚያን ጊዜ የነበረውን ሞቅታና ድምቀት፣ ጭፈራና ዳንኪራ፣ የአራዳዎች መናኸሪያ በነበረችው ፒያሳ እየከመኮመ፣ በትዝታው እየነጎደ እንዲኖር አስችሎታል፡፡

በዚያን ጊዜ የነበሩትም ታዋቂ አርቲስቶች እንደነ ባህታ ገብረ ሕይወት፣ ዓለማየሁ እሸቴና ጌታቸው ካሳ በውርርድ ከዛ ቦታ አይታጡም ነበር ይባላል፡፡ አቶ ነጋም  ያኔ የነበረውን ሁኔታ እንደዚህ ገልጾታል፡፡

‹‹እነዚህ ሙዚቀኞች የሙዚቃ ችሎታቸውን ያሻሻሉት ፒያሳ አካባቢ በነበሩት ቤቶች ነው  እነ ሲምቢሮ ቬነስ የሚባሉ ክለቦችም ነበሩ፡፡ እንደዛም ሆኖ ግን ጣይቱ ሆቴል ታዋቂና ስመጥር ሆቴል ነበር፡፡››

የጃዝ አምባ ክለብም ፒያሳ አካባቢ በመጀመርያው ጣይቱ ሆቴል ውስጥ መጀመሩ ፒያሳ የነበራትን ድምቀት ለመመለስ እንዲያስችልና የጥንቱን የሙዚቃና የአሁኑን ሙዚቃ በጃዝ ለማሳየት ነውም ብሏል፡፡

ቦታውን ለማደስ አራት ወራት ያህል የፈጀበት ሲሆን፣ ውስጡንም በዱሮዎቹና በአሁኖቹ ሙዚቀኞች ፎቶ አካቶ አስጊጦታል፡፡ ከእነዚህም ውስጥ ግርማ በየነ፣ ጌታቸው ካሳ፣ አስቴር አወቀ፣ አበጋዝ ሺዎታና ሔኖክ ተመስገን ይገኙበታል፡፡

‹‹በዚህ ክለብ ዱሮ የነበረውን ስሜት ለተመልካቹ ማምጣት እንፈልጋለን፤›› ብሏል፡፡

ክለቡ ሲከፈት የሳምንቱን ቀናት ሁሉ ክፍት ይሆናል፡፡ ዘሪቱ፣ ሙኒት እና ዮርግ የመሳሰሉት ድምፃውያን እንዲሁም የባህል ባንዱ ኢትዮ ከለር፣ የ60ዎቹን ሙዚቃ የሚጫወቱት ኤክስፕረስ ባንድ፣ ጃዝ እና ጃዝን ከሌሎች ሙዚቃዎች ጋር እያቀላቀሉ የሚጫወቱት ኧርባን ቫይብስ፣ አዲስ አኩስቲክ ፕሮጀክት፣ ትሪዮሎጂ እና ጃዝማሪስ እንዲሁም በአር ኤንድ ቢ የሙዚቃ ስልት የሚታወቀው ኬኒ አለን ከ251 ባንድ ጋር ለሰኔ ወር ከተደለደሉት ውስጥ ናቸው፡፡

ምንም እንኳን ቦታው የጃዝ ሙዚቃና ሙዚቀኞች ጐልተው የሚታዩበት ነው ቢባልም፣ አዘጋጆቹ እንደሚናገሩት ሌሎች የሙዚቃ ዓይነቶችም ይደመጡበታል፡፡ ‹‹እስካሁን ድረስ ሁሉም ባንዶች ቦታውን አይተው ወደውታል፡፡ የክለቡም ባለድርሻ አካላትም ሙዚቀኞች ስለሆኑ ክለቡ ውስጥ ይጫወታሉ፡፡ ስለዚህ ሰባት ቀን መሆኑ ይከብዳል ብለን አናስብም፤›› ይላሉ፡፡

አቶ ነጋ እንደሚገልጸው ጐላ ብሎ የሚታይ፣ መልሶ የመገንባት ሥራ እንደተከናወነ ከሚታዩትም ውስጥ ለየት ባለ በሥነ ሕንፃዊ ውበት የተሠራው እናት ሕንፃ፣ አዲስ የተሠሩት ካፍቴሪያዎች፣ ታድሰው አገልግሎት ላይ የዋሉት የዱሮ ሲኒማ ቤቶች ይጠቀሳሉ፡፡

አዘጋጆቹ የክለቡ መከፈት ቦሌ አካባቢን ብቻ አማራጭ ላደረጉ የሙዚቃ ወዳጆች ፊታቸውን ወደ ፒያሳ መለስ እንዲያደርጉ ያስችላቸዋል ብለው ያምናሉ፡፡

‹‹የእኛ ዓላማ በጥሩ ሙዚቃ ተዝናንተው እንዲሔዱና ከዚያም በላይ የዱሮውን ጊዜ አስታውሰው፣ የአሁኑንም አይተው አዲስ ልምድ ይዘው እንዲሔዱ ለማድረግ ነው፡፡››

የቦታውን ታሪካዊ ዳራ ትልቅነት ለማሳየት ፒያሳን እንደገና ወደ ቀድሞ የሙዚቃ መንደርነቱ መመለስ የጃዝ አምባ ዋና ዓላማ ሲሆን፣ ከዚህ በተጨማሪም ቦታውን የጥበብ ማዕከል የማድረግም ዕቅድ አላቸው፡፡

‹‹ይኼ ቦታ ለንግድ ተብሎ ብቻ የተቋቋመ ቦታ አይደለም፡፡›› የሚሉት የክለቡ ኃላፊዎች፣ ለተለያዩ የጥበባዊ ውጤቶች ለግጥም፣ አዲስ መጽሐፍ ሲመረቅ ወይም አዲስ ሲዲ ሲወጣ፣ አዳዲስ ለሚመጡ አርቲስቶች ያገለግላል ብለውም ያምናሉ፡፡

በየወሩ አዳዲስ ፕሮግራሞች የሚወጡ ሲሆን፣ ከዚህም በተጨማሪ ታዋቂዎቹ የዱሮ ዘፋኞችም በዚህ ቦታ ላይ እንዲዘፍኑ ጥርጊያው ተመቻችቷል፡፡

ክለቡ ለኢትዮጵያውያን ሙዚቀኞች ብቻ የተተወ ሳይሆን፣ ከአውሮፓ፣ ከአሜሪካ እንዲሁም ከሌሎች አፍሪካ አገሮች የሚመጡ አርቲስቶች መታደሚያም ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

‹‹ከሙዚቃ በተጨማሪ የጃዝ ሴሚናሮች እና ወርክሾፖች ይኖራሉ፡፡ ታዋቂ ዘፋኞችን ማስመጣት እንፈልጋለን፡፡ ማንኛውም ሰው መጥቶ ፒያሳ አካባቢ ተዝናንቶ በሙዚቃችን የማይረሳ ጊዜ አሳልፎ እንዲሔድ እንፈልጋለን፤›› በማለት ነጋ ገለጻውን ያጠቃልላል፡፡

አርቲስቶቹን ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር ያገናኘው መድረክ ተነቀፈ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ሥነ ጥበባት ምክክር መድረክ አመቻች ጊዜያዊ ኮሚቶ ግንቦት 29 ቀን 2003 ዓ.ም. ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊን ከርቲስቶች ጋር ለመጀመርያ ጊዜ ለማገናኘት ያዘጋጀው መድረክ በአርቲስቶቹ ተነቀፈ፡፡ አርቲስቶቹ የመድረኩን አዘጋጅ ኮሚቴ የነቀፉበትን ምክንያት ያነጋገርናቸው አራት አርቲስቶች እንደሚከተለው ገልጸውታል፡፡

‹‹ይሄ ነው ወይ ሚዜሽ አየንልሽ››
ይሔ ስብሰባ 1,500 አካባቢ የሥነ ጥበብ ባለሙያዎች የተገኙበት ነበር፡፡ ነገር ግን በስብሰባው የኢትዮጵያን ሥነ ጥበብ የወከሉት እነዚህ ናቸው ወይ? በዚህ ደረጃስ ላይ ነው ወይ? የሚገኙት የሚል ግምት ያሰጠ ነው፡፡ በጣም የሚያሳፍር ነው አንገቴን ደፍቼ እና አቀርቅሬ ነው የወጣሁት፡፡

የብዙዎቹ ጥያቄዎች ይዘት የአገሪቷን ሥልጣኔ፣ ባህልና ኢኮኖሚ ያገናዘበ አይደለም፡፡ ወደ አንድ ያደላ እና እኛ ብቻ እንጠቀም የሚል ይዘት አለው፡፡ የተጠየቁትን ጥያቄዎች ማየት ይቻላል፤ እንዴት ነው ያለ ቀረጥ የሚገባው? ቀረጥ ይቀነስ የሚሉ ናቸው፡፡ ነገር ግን አገሬን እወዳለሁ፣ የሕዝቡን ኑሮ እቀይራለሁ ከሚሉ መነሣቱ በጣም የሚገርም ነው፡፡

ከተነሡት ጥያቄዎች ትንሽ ሻል የሚለው ሠርፀ ፍሬ ስብሐት ያነሣው ጥያቄ  ነው፡፡ የሥነ ጥበብ ትምህርትን ከትንሹ ክፍል ጀምሮ ማስተማር ላይ ስለሚያተኩር መሠረታዊ ነው፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩም በአግባቡ የመለሱት ይኼንኑ ነው፡፡ ሌላው ከመሠረተ ልማት ጋር በተያያዘ የሲኒማ ቤቶች እጥረት ጋር ተያይዞ የተነሣው ጥያቄ ሁሉም ጉዳይ ለምን ወደ መንግሥት ይወረወራል የሚል አስተሳሰብ እንዳነሣ አድርጎኛል፡፡

አካዴሚክ የሆኑና በሰል ያሉ ጥያቄዎች መነሣት ይችሉ ነበር፡፡ ለምሳሌ ኢትዮጵያ የብዙ ብሔር ብሔረሰቦች አገር ነች፡፡ የሥልጣኔ መነሻ ነች፡፡ ማኅበረሰቧ በባህል እሴቶች የበለፀገ ነው፡፡ ነገር ግን ፊልሙ ሲታይ በሆሊውድ ተጽዕኖ ሥር ነው፡፡ እንዲሁም ቴአትራችን የግሪክ ቴአትር የሚመስል ነው፡፡ ኢትዮጵያዊ ቀለም ያለው ሥነ ጥበብ እንዲፈጠር ምን ማድረግ እንችላለን የሚለው ጥያቄ መነሣት ነበረበት፡፡ ነገር ግን ‹‹ይሄ ነው ወይ ሚዜሽ አየንልሽ›› ያስባለ ነበር፡፡

ምንም እንኳን ከሃያ ዓመት በኋላ የተፈጠረ ትልቅ መድረክ ቢጨናገፍም በራሱ መጀመሩ ጥሩ ነው፡፡ የመንግሥትን አቋም አውቀንበታል፡፡ መገናኘቱም ጥሩ ነው፡፡ ነገር ግን ተርበናል፤ ተጠምተናል ብለን የጀመርነው ቴአትር በመጨረሻ ላይ በወርቅ እስክርቢቶ ሽልማት መጠናቀቁ ከማስገረም በላይ ነው፡፡
(አርቲስት ኪሮስ ኃይለ ሥላሴ)


‹‹ከቴአትሩ እስከ ሽልማቱ አርቲስቶቹን አይወክልም››

ተስፋ አስቆራጭ እና አሳዛኝ ጉዳይ የነበረው የጥያቄዎቹ ይዘትና አቀራረብ ነበር፡፡ ለአንድ ሀገር መሪ መጠየቅ የነበረባቸው ጥያቄዎች እንዴት ነው የሚቀርቡት የሚለው የታወቀ አልመሰለኝም፡፡ ስብሰባው ላይ የተደረገው ከቴአትሩ እስከ ሽልማቱ ድረስ አርቲስቶቹን አይወክልም፡፡ ማድረግ የነበረብን ምን ያህል አርቲስቶች ትውልድ መቅረጽ እንደሚችሉና እርሳቸውም በኛ ላይ ኩራት እንዲያድርባቸው ማድረግ ነበረብን፡፡ ሁሉም ጥያቄዎች አንድ ዓይነት ነበሩ እያል ሳይሆን፣ ብዙዎቹ ግን የቃላት ድግግሞሽ ነበረባቸው፤ ከዚያም በተጨማሪ ብዙ መነሣት የነበረባቸው አንገብጋቢ ጥያቄዎች መነሣት አልቻሉም፡፡

ይሄንን ስል ግን ኮሚቴው ይሄንን የምክክር መድረክ መፍጠሩን ትልቅ ነገር መሆኑን ማሳወቅ እፈልጋለሁ፡፡ በጣም ትልቁና ከባዱ ነገር የነበረው እርሳቸውን ማግኘት ነበር፡፡ እርሳቸውን ካገኘናቸው በኋላ ግን ምን ማድረግ እንዳለብን የታሰበ አልመሰለኝም፡፡

ሌላው ደግሞ አብዛኛው የቀረቡት ጥያቄዎች ሁሉንም ሙያዎች ያማከለ አልነበረም፡፡ አርቲስቶች ሆነን ያለንን ነገር በትክክል መግለጽ አልቻልንም፡፡ ይሄም ከምንሠራው ጋር ይቃረናል፡፡ ለቀጣይ ስብሰባዎች ግን መማርያ ነው ብዬ አስባለሁ፡፡
(የፊልም ባለሙያ ዮናስ ብርሃነ መዋ)

‹‹ሙያችንን ማንፀባረቅና ስለሙያችን መታገል የሚችል እንመድባለን››
ለረዥም ዓመታት በሦስቱም መንግሥታት ተጠቂ የነበረው ሙዚቃው ነው፡፡ ለሙዚቃው ላይ ምንም ትኩረት አልተሰጠውም፡፡ ነገር ግን ሕዝብንም መንግሥትንም በሬዲዮውም፣ በቴሌቪዥኑም በሌሎችም መድረኮች እያገለገለ ያለው ሙዚቃው ነው፡፡

ለረዥም ዓመታት ጠቅላይ ሚኒስትሩን ማነጋገር አለብን ስንል እነዚህን ችግራችንን እንዲያውቁልን ነው፡፡ መድረኩ የተቋቋመው የምንችለውን እንፈታለን፤ ግን የመንግሥት ድጋፍ ያስፈልገናል የሚለውን ነገር ለመጠየቅ ነው፡፡ አደራጅ ኮሚቴው ሲመሠረት ዋነኛው ከኢትዮጵያ ሙዚቀኞች ማኅበር የተወከለ ነው፡፡ ስለዚህ ሙዚቃን ወክሎ ተፈላጊውን ውጤት ያመጣል ብለን ነበር [ሠርፀ ፍሬ ስብሐት] የላክነው ከዚያ በኋላ ምንም መረጃ ሳይሰጠን መጨረሻ ላይ መድረኩ ተዘጋጀ፡፡ የማቀርበውን ጥያቄ ባለፈው ዓርብ አስገምግሚያለሁ፤ በዚያን ጊዜ የተባልኩት 10ኛ ተራ ቁጥር ይሰጠሃል ነበር፡፡ መጀመርያውኑ 10ኛ መባሉንም አልተቀበልኩም፡፡ የኮፒ ራይት መብት የሁላችንም ስለሆነ እርሱ ላይ እናተኩር በመባሉ፡፡ እስከመጨረሻው ደቂቃ ድረስ ከአሁን አሁን እጠራለሁ ብዬ ጠብቄ ነበር፡፡ በኋላ ሳጣራ የተሰጠኝ የመጨረሻው ሁለተኛ እሱም ሆኖ ተሰጥቶኝ ባቀርብ ኖሮ ምንም አልነበረም፡፡

በማኅበር የምንወስደው አቋም ይኖራል፡፡ በሚቀጥለው ሳምንት ውስጥ የሚመለከታቸውን የሙዚቃ ባለሙያዎች እንሰብስብና ጠቅላይ ሚኒስትሩን ካነጋገርንበት ላይ የተገኘው ምን ምን እንደሆነ እንገነዘብና ወደፊት ምን መሆን አለበት በሚለው ላይ ሐሳብ ከወሰድን በኋላ አቋም እንይዛለን፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በጋራ መድረክ ይቋቋም ባሉት ላይ በጣም የምንደግፈው ነው፡፡ ነገር ግን ሙያችንን ማንፀባረቅ የሚችል፣ ስለሙያችን መታገል የሚችል ሰው እዚያ ላይ እንመድባለን እንጂ እንዲህ የምንለቀው አይደለም፡፡

በመጀመርያ ደረጃ ጠቅላይ ሚኒስትሩ የተጠየቁት አብዛኞቹ ጥያቄዎች እሳቸውን ይመጥናሉ ብዬ አልገምትም፡፡ እርስ በርሳችን ማኅበራት በመጠናከር መመለስና መፍታት የምንችለውን ነገር ለርሳቸው ወርውረናል፡፡ ያም ሆነ ይህ ግን እሳቸው የሰጡን ትልቁ ዕድል በጋራ ሆነን መሥራት እንችላለን ማለታቸው ትልቅ ድል ነው፡፡
ሙያችንን ከፍ ለማድረግም ሆነ ለመጣልም የሚችለው የያንዳንዳችን ጥንካሬ ነው፡፡ ስለዚህ ተናጠላዊ የሆነውም ሆነ የሙያ ማኅበራት ከዚህ በበለጠ በዕውቀት ላይ መሠረት አድርጎ መጠናከር አለበት እላለሁ፡፡
(ዳዊት ይፍሩ፣ የኢትዮጵያ ሙዚቀኞች ማኅበር ፕሬዚዳንት)


‹‹ሥነ ጥበቡ ሲጠፋ እንደ ገበሬ ምርት አይታይም››

‹‹እኛ ቅር ብሎናል፤ ተነገደብን ነው የምንለው፤ ጀማሪዎቹ እኛ ነበርን፡፡ ክብደት ያለው ጥያቄ ለመጠየቅ እንጂ የግለሰብ ፍላጎትን ለመጠየቅ አይደለም፡፡ እኔ ራሴ አፍሬያለሁ፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትራችን ሳይታዘቡ የቀሩ አይመስለኝም፡፡ ያደረግነውና የጠየቅነው ነገር እርስ በርሱ ይጋጫል፡፡ ምንም የለንም፣ ባዶ ነን፤ እየተዘረፍን ነው፤ እያልን የወርቅ ስጦታ ስንሰጥ ይጋጫል፡፡

ሲጀመር በስብሰባው ላይ እንድንገኝ አልተፈለገም፡፡ ከውጭ ሰው ሰምተን በግድ ሔደናል ማለት እንችላለን፡፡ ወረቀቱን የላኩልን ስንጠይቅ ነው፡፡ በጣም የተጎዳው በሙዚቃው ዘርፍ ያለው ነው፡፡

ስንት ጊዜ ስለፊልም ስለካሜራ እንደተወራ ሰምተናል፡፡ አንድም ሰው ስለሙዚቃ ያነሣ የለም፡፡ መሠረታዊ ጥያቄ አዘጋጅተን ነበር፡፡ ዕድሉን አልሰጡንም እንጂ፡፡

ከዚህ ሁሉ ድካም በኋላ እንደዚህ ዓይነት የሁሉ መድረክ በሞኖፖል መያዝ አግባብ አይደለም፡፡ የአንድ ሰውና ባልደረቦቹ ብቻ እንዲመስል የተደረገው ሆን ተብሎ  ነው፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ እያንዳንዱን ነገር ያውቃሉ፤ የታዋቂዎቹን ፊት ስላላዩ አዝነው የወጡ ይመስለኛል፡፡ አድልዎ የተደረገው ከአዳራሹ ወንበር ጀምሮ ነው፡፡ ሲያስቀምጡ የነበረው ጥያቄ ይጠይቁ የነበሩት ናቸው፡፡ በርግጥ ጥያቄ ተጠይቋል ነው ወይ? የኔ ነጥብ ነው፡፡

ሥነ ጥበቡ ሲጠፋ እንደ ገበሬ ምርት አይታይም፡፡ አንድ ነገር አብቅለኸው ሲጠፋ ዝናብ ካልዘነበ ታየዋለህ፡፡ ሌላ መንገድ ትፈልጋለህ፡፡ ሥነ ጥበብ ግን አይታይም፤ ትውልድ ይጠይቃል፡፡ የሚያንሰራራው ብዙ ነገር ከጠፋ በኋላ ይሆናል፡፡ ሙዚቃ እንደሌላው ሁሉ በየደረጃው ትምህርት መሰጠት እንዳለበት አምናለሁ፡፡ አንድ አቅጣጫ ብቻ ይዘህ ከተማርህ አስቸጋሪ ነው፡፡ በየቢሮው ስንሔድ የሚያስቸግሩን ትምህርቱ ላይ ችግር ያለባቸው ናቸው፡፡ ነፃ ሆኖ በዕውቀት ያደገ ለኅብረተሰቡ ጠንቅ አይሆንም፤ አያስቸግርም፡፡ ከመሠረቱ ማደግ ያስፈልጋልና ስለሙዚቃ ትምህርት ትኩረት እንዲሰጥ መጠየቅ ፈልጌ ነበር፡፡ እድሉን አላገኘሁም እንጂ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ እንዲያነጋግሩን ሀ ብለን የጀመርነው እኛ ነን፡፡ እነዚህ ሁሉ ሰዎች ከየት እንደመጡ አላውቅም፡፡ ጩኸቴን ቀሙኝ ዓይነት ነገር ነው፡፡ ሁልጊዜ እነዚያ ሰዎች የሚፈልጉት ዝግጅት በኖረበት ቦታ ሁሉ ነገር መቆጣጠር ነው፡፡ ለሌላው ዕድል መሰጠት አለበት፡፡

በአንድ በኩል ምንም አለመጠየቄ ደስ ብሎኛል በነዚያ መካከል እንኳን አልተሳተፍኩ ብያለሁ፡፡ ምክንያቱም ማፈሪያ መሆን ነውና፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሌላ ዕድል ይሰጡናል ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ፡፡
(አርቲስት ሐመልማል አባተ)

ሪፖርተር በሰኔ 1 ቀን 2003 እትሙ የተለያዩ የሥነ ጥበቡ ቤተሰቦችን ቅሬታ ከጊዜያዊ ኮሚቴው ምላሽ ጋር መዘገባችን ይታወሳል፡፡ የምክክር መድረኩ ሰብሳቢ አቶ ቶማስ ጌታቸው፣ ከሙዚቀኞች አቶ ዳዊት ይፍሩ በሰዓት እጥረት ምክንያት ሳይጠይቁ መቅረታቸውን፣ የቀረቡት ጥያቄዎችም ምናልባት የቀረቡበት መንገድ ሊያዛባው ቢችልም፣ ከዚህም በተጨማሪ ቀጥተኛ መልስ የሚጠብቁ ሰዎች ያንን መልስ ስላላገኙ ትንሽ ያዘኑ ይመስለኛል ማለታቸውንም መዘገባችን ይታወሳል፡፡

አርቲስት ፋንቱ ማንዶዬ፡ “ጠዋት ተነስቼ ጠላ ነበር የምጠጣሁ”


(አውራምባ ታይምስ)ጳውሎስ ኞኞ ይሰራበት በነበረው አዲስ ዘመን ጋዜጣ የ‹‹አንድ ጥያቄ አለኝ›› አምድ የካቲት 1964 ዓ.ም. እትም ላይ ‹‹እስካሁን ድረስ በኢትዮጵያ በብዛት የሌለው ስም የቱ ነው?›› የሚል ጥያቄ ቀርቦለት፣ ‹‹ኞኞ ነው›› ሲል መልሷል። የተጠየቅከው አንተ ብትሆን ደግሞ ‹‹ማንዶዬ›› የምትል ይመስለኛል።
አዎ፣ ማንዶዬ የተለመደ ስም አይደለም። አባቴ የደቡብ ሰው ነው፤ የወላይታ። የስሙ አቻ የአማርኛ ቃል ‹‹ማንን ተክቼ›› እንደ ማለት ነው። አንተን የሚያስታውስ ‹‹እሁድ የእቁብ ጠላ›› የሚለውን ኮሜዲያዊ የሙዚቃ ስራን አይዘነጋም። የዘፈኑ የዜማና የግጥም ደራሲ ንጉሱ ረታ ይባላል። በወቅቱ ጠጪ ስለነበርኩ፣ ይመለከተኝ ስለነበር ለእኔ ሲሰጠኝ ደስ ብሎኝ ተጫወትኩት።
በርካታ ጣሳ ጠላ ትጠጣ እንደነበር ሰምቻለሁ።
ምን ያህል ትጠጣ ነበር?
ኦው! ጠዋት ተነስቼ ጠላ ነበር የምጠጣው። [ይጠጣ የነበረው ዶሮ ማነቂያ ውስጥ በሚገኘው ሾፌር ሰፈር ነበር።]
ጠዋት ከ40 በላይ ብርጭቆ ትጠጣ ነበር አሉ

ያኔ በብርጭቆ አይለካም እንጂ ከዚያ በላይ ጠጣ ነበር። ጠላ የምንጠጣው ጠዋት ጠዋት ብቻ ነበር። ከዚያ በኋላ ወደ ካቲካላ፤ ጠጅ እንቀጥላለን። እስከ ምሽት ድረስ መጠጣት ነበር። [በወቅቱ
የሁለት ጣሳ ጠላ ዋጋ ስሙኒ ነበር።]
ከ60 ዓመት የሕይወት ተሞክሮህ አንፃር ስታየው፣ ‹‹ባልፈጠር ያመልጠኝ ነበር›› የምትለው ነገር ምንድን ነው?
መጠጥ ካቆምኩ 24 ዓመት ደፍኖኛል።
በፊት ብሞት መጠጥ ገደለው እንጂ እግዚአብሔር ገደለው አይባልም ነበር። ኖሬ ይህን በማየቴ ደስ ይለኛል። በመኖሬ ብዙ የሰው ፍቅር አግኝቻለሁ። ባልፈጠር ይህ የሕዝብ ፍቅር ከየት ይገኝ ነበር?
ከሰውነትህ አካላት መካከል ቢቀነስም አይጎዳኝ የምትለው አለ?
ሁሉም የሰውነት አካላት ጠቃሚ ናቸው። ኧረ! ይቀነስ የምለው የለም።
የፊት ገፅታህ ቁጡ ያስመስልሀል። ዝምታህም የሚያስጨንቅ አይነት ነው ልበል?
ብዙዎች እንደዚያ ይሉኛል። ከመናገር ይበልጥ ማዳመጥ ደስ ይለኛል። ብዙ ክርክር አልችልም። የማውቀውን ነገር እንኳን ‹‹አይደለም›› ቢሉኝ ከምከራከር ይልቅ አምኜ ብለያይ ብዬ ስለማምን
እተወዋለሁ። ዝም እና ኮስተር በማለቴ ብዙ ሰዎች የምጫወት አይመስላቸውም። ድሮ ድሮ ጠጅ ቤት ውስጥ ዝም ስለምል ተደባዳቢ መስላቸው ነበር። አንድ ሽማግሌ ከቀረቡኝ በኋላ፣ ‹‹ለፀብ የተዘጋጀህ እንጂ ተጨዋች ሰው አትመስለኝም›› ሲሉ ተዋውቄያቸው ለብዙ ዘመን ጓደኛ ሆነናል።
የ‹‹እኔ›› የምትለው መልካም ነገር ምንድን ነው?
በጎ ነገሮችን ለመስራት እሞክራለሁ። በጓደኞቼ ላይ አንዳንድ ችግሮች ሲመጡ በአቅሜ መተባበር እፈልጋለሁ። ሜሪ ጆይ የተራድኦ ድርጅት ውስጥ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት እሰጣለሁ። የቀይ መስቀል
አባል ነኝ። ይህን መሰል በሆኑ በጎ ሥራዎች ላይ ብካፈል ደስተኛ ነኝ።
የመኖሪያ አካባቢ በድርቅና በመሰል ችግሮች ሳቢያ ‹‹ለኑሮ አመቺ አይደለም›› ሲባል
ሰፈራ ይደረጋል። የሙያ ሰፈራ ቢኖር ወደ ምን መስፈር ትፈልጋለህ?
ወደ ሌላ ሙያ ብዘዋወር መስራት የምችል
አይመስለኝም። እንደገና ልጅ ብሆን ግን
እግር ኳስ ተጨዋች ብሆን ደስ ይለኛል።
ከሰራኸው ቲያትር ውስጥ እንደው ቢቻልና
በተመሳሳይ ሰዓት ‹‹ተዋናይ ሆኜ ብትሰራው፣
ተመልካች ሆኜ ባየው›› ብሎ ያስመኘህ አለ?
በ1964 ዓ.ም ‹‹ጤና ያጣ ፍቅር›› የሚል
ሙዚቃዊ ድራማ ሰርተን ሲጠናቀቅ
የነበረው ጭብጨባ በጣም ከፍተኛ ነበር።
ተመልካችም ሆኜ የማየው ቢሆን እሱን
መርጥ ነበር። ሌላው ቀርቶ በፊልም
ተቀርጾ እንኳን ባየው ደስ ይለኝ ነበር፤
ግን አልተደረገም።
ምላሽ ባለማግኘትህ ብቻ አምነህ የተቀበልከው
ነገር አለ?
አለ። እሱም በመስሪያ ቤታችን (በአዲስ
አበባ ቲያትርና ባህል አዳራሽ) ያለውን
የሠራተኛ ደረጃ አመዳደብ ነው። አንድ
ጊዜ ኤክስፐርት ያደርጉሀል፣ ሲፈልጉ
ተዋናይ ያደርጉሀል። እናም ሳላምንባቸው
ብዙዎቹን ነገሮች ተቀብያለሁ። ‹‹ለምን?››
ብትለኝ እነሱ ማሟላት አለብህ የሚሉኝን
የትምህርት ሰርተፍኬት ስለማላሟላ ነው።
እኔ ትምህርት ያቆምኩት 7ኛ እና 8ኛ
ክፍል ላይ ስለሆነ ያሉኝን መቀበል ነው።
በችሎታ /በሙያ ፈትነው ኤክስፐርት፣
ተዋናይ ስድስት ተብዬ ነበር። እንደገና
በቢ.ፒ.አር ተራ ተዋናይ ተብዬ ወደ
ታች ስወርድ በዚህ ምክንያት ጡረታ
ወጥቻለሁ። [ጡረታ 1,067 ብር ያገኛል]
ባለፈው ሰኞ የጥበብ ‹‹ባለሙያዎች››
ከጠ/ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ጋር ባደረጋችሁት
ስብሰባ ላይ አንተ የተሳተፍክበት ተውኔት
አቅርባችኋል። ‹‹ልቤን የጭብጨባ ቡፌ
አጥግቦት ሆዴ ባዶ መሆኑን እያወቅኩ
ይኸው እስከዛሬ ዘለቅኩ›› የሚል የጥበብ
ሰዎች ኑሯችሁ አሳዛኝ መሆኑን የሚገልፅ ቃለ
ተውኔት ከአፍህ ወጥቷል። ይህ መሰል ነገር
ተደጋግሞ ይነሳል። እናንተ የሙያው ፀባይ
ታዋቂ ያደርጋችኋል፣ ጭብጨባ ይቸራችኋል።
አንድ የሕክምና ዶክተር፣ አካውንታንት፣ ሥራ
አስኪያጅ አይጨበጨብላቸውም እንጂ ትልቅ
ነገር ይከውናሉ። የእናንተ ታዲያ ምን ስለሆነ
ነው ተደጋግሞ የሚነሳው?
የቴሌቪዥን ድራማ፣ ፊልም እና ሌሎች
የጥበብ ውጤቶችን ስንሰራ የሚከፈለን
ገንዘብ አነስተኛ ነው። ይህ እንዲሆን
ያደረገው ደግሞ የቅጂ መብት በአግባቡ
አለመከበር ነው። በእኛ ሥራ ምንም
ነገር ሳይሰሩ ትልቅ ሀብታም የሆኑ
ሰዎች አሉ። አሁን በህይወት የሌለ
አረብ አገር ይኖር የነበረ አንድ ጓደኛችን፣
‹‹የሚገርማችሁ የእናንተ ድራማ
ሲተላለፍ እዚያ እሸጥ ነበር። ገንዘቡ
የቤት ኪራይ ለመክፈል ይረዳኝ ነበር››
ብሎኛል። እሱ ግልፅ ስለሆነ ነገረን እንጂ
ብዙዎች ተጠቃሚ የሆኑ አሉ። ይህ
ደግሞ ተገቢውን ህይወት እንዳንመራ
አድርጎናል እንጂ፣ ‹‹እኛ ከሌላው ህዝብ
የተለየን ነን›› ማለት አይደለም።
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን
ፓትርያርክ ሙሉ መጠሪያ ስማቸውን
ታውቀዋለህ?
[እየሳቀ] አታስቸግረኝ … በእውነት
ጥራ ብትለኝ አልችለውም። [እንደምንም
ሞክረው ብዬው ዝግ እያለ ቀጠለ] ብፁዕ
አቡነ ጳውሎስ ፓትሪያርክ አክሱም
ወይጨጌ እንደዚህ የሚል አለበት እና
አዎ እንደዚያ ነው …·ረ ይጠፋኛል።
[ለማንኛውም ፋንቱ እኔ ልሞክር…
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ቀዳማዊ
ፓትርያርክ፣ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት
ዘኢትዮጵያ፣ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም፣
ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት፣
የዓለም አቢያተ ክርስቲያናት ምክር ቤት
ፕሬዝዳንት፣ የዓለም ሃይማኖቶች ምክር
ቤት ለሰላም የክብር ፕሬዝዳንት፣… ኦው!
ፋንቱ የቀረ ካለ ተባበረኝ፤ እንሞላዋለን፣
ስለ ትብብርህ አመሰግናለሁ።

Mulatu Astatke: The godfather of Ethiopian jazz


(BBC) Mulatu Astatke, the godfather of Ethiopian jazz music, is often flying around the world performing sell-out shows so I was lucky to find him at his home in Addis Ababa surrounded by art, conjuring up magic on his vibraphone – which looks like a giant xylophone.

He described the recipe for Ethio-jazz which he first cooked up 42 years ago while studying music in the United States.

“Most of our Ethiopian music is based on five notes [pentatonic]. What I did was fuse the five tones with 12 tones. For many years I’ve been experimenting and the more I do that the more complex it gets,” Mr Mulatu told the BBC.

“I remember one teacher at Berklee College in Boston telling us to always be ourselves and that was always on my mind. I used to do a lot of analyzing of the music of Duke Ellington, Count Basie, Miles Davis and John Coltrane and I saw how great they were and what they had contributed to the world of music.

“So my aim was always to be like them and create something to give to my country and give to the world.”

Heading to Glastonbury

Instead of simply copying the jazz greats, Mr Mulatu set about researching the music of Ethiopia and constantly added a generous pinch of this to his musical cooking pot.

Mulatu Astatke
“There are tribes in the south called the Derashe. They are surrounded by people who play five tone music but they have created a diminished 12-tone scale,” Mr Mulatu said.

“Diminished scales are very important in jazz music especially for improvising. We learn how Charlie Parker came up with diminished scales as well as [the French classical composer] Claude Debussy and Bach. But always on my mind is the question of who were first with the scale, these people or the Derashe tribe?”

Ethio-jazz is on a roll in Addis Ababa.

A new jazz club opened last week, new Ethio-jazz bands are forming and now there are several music colleges. It is also on the rise on the world stage.

Mr Mulatu is due to play at the UK’s famous Glastonbury festival next week.

‘Scientific music’

At Mekane Yesus Jazz Music School in Addis Ababa, students study Mr Mulatu’s music and are even examined on it as part of the curriculum.

Young musicians like Robera Mekonnen look up to Mulatu Astatke In a corridor of tiny practice rooms there were saxophonists, pianists, guitar players and some students with Ethiopian traditional instruments getting ready for the exams.

Two floors up the fire escape and the Blue Note band was cooking up a storm.

The seven-piece band was playing original Ethio-jazz songs – the unmistakable five tone scales, keeping a heavy hint of Ethiopia in the music.

“As a musician, I love all types of music but I love Ethio-jazz music most because it describes me very well – better than other jazz music,” said the band’s 20-year-old bassist, Robera Mekonnen.

“I’m influenced by the legendary musicians of Ethiopia who have brought about a change by mixing jazz with Ethiopian music. One of them is Mulatu Astatke, a man who is special because he loves his native music and has developed it scientifically.”

Over the years, Mr Mulatu has brought musicians from across Ethiopia into the studio.

For one session, Derashe musicians turned up with their six-inch long bamboo flutes, others carried giant vuvuzela-style pipes up to four metres long. When mixed with his own band, the result was an extraordinary hypnotic sound.

Fishing for instruments

Among the stalls of the bustling Addis Merkato market, I found other Ethiopian instruments which Mr Mulatu has fused into his Ethio-jazz music.

Hanging from the ceiling of one shop were dozens of the one-stringed violin-like instruments known as masinko which are played with a bow.

Mulatu Astatke is trying to use the traditional krar in modern music It was like fishing for instruments in the roof of the house as the shopkeeper used a pole to bring down a krar – a five- or six-stringed Ethiopian harp.

To hear them played well, I visited Yod Abyssinia, a cultural centre where the mostly Ethiopian audience is treated to traditional music, dance and food.

Here the music is played in its pure form but Mr Mulatu is on a mission to develop the instruments so the players are not restricted.

“I have a very high respect for our cultural instruments. I have tried to develop the krar. I changed it from six to eight strings and managed to play for the first time songs like Guantanamera, Mercy Mercy and Summertime.

“For 3,000 years we couldn’t play anything except five-tone music on the krar. My aim is to develop one with 12 strings,” Mr Mulatu said.

I wondered if there was not also an argument for leaving the instruments in their purest form.

“Some believe that but I don’t. Look, why do you think most young people go to the guitar?” asked Mr Mulatu.

“It is because the traditional instruments limit them – they cannot do what they want to do. On the guitar, they can experiment. If I can develop the krar so it can do what the guitar does, they will be playing their own instruments and they can also contribute to the world different sounds.

“When you have been kept to five-tone music all your life and you start playing 12-tone music you can do miracles. So it develops the instrument and the mind.”♥

Advertisements

Thank you for leaving us a comment on the post and Thank you for subscribing.

Please log in using one of these methods to post your comment:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this:
search previous next tag category expand menu location phone mail time cart zoom edit close