የኢትዮጵያ ሰራዊት ከአልሸባብ ታጣቂዎች ጋር ተጋጨ።

ሁለት የኬንያ ወታደሮች እና 6 ሲቪል ዜጎች ቆሰሉ

ዝግጅት በ አቢ ገብረሃና- ABBY G.Minda

ናይሮቢ፡ የኢትዮጵያ ስራዊት የሶማሊያ  የሽግግር መንግስትን ለመደገፍ በሚያድርግው ጥረት  ከአልሸባብ ታጣቂዎች ጋር ግጭት ውስጥ ገባ።

ባለፉት ሁለት ሳምንታት ውስጥ በለድ ሃዋ በመባል በምትጠራው  የሶማሊያ፣ኬኒያ እና ኢትዮጵያ አዋሳኝ የድንበር ከትማ አቅራቢያ ከአልሸባብ ታጣቂዎች ጋር ከፍተኛ ውጊያ ውስጥ መግባቱ ታውቋል። የ NTVዘገባን ይመልከቱ:

ውጊያው የተቀሰቅሰው ከ2009 ዓ.ም ጀምሮ ኢትዮጵያ ውስጥ ስልጠና ሲስጣቸው ቆይተው ሰልጠናችውን ያጠናቅቁ  የሶማሊያ  የሽግግር መንግስት ወታድሮችን የኢትዮጵያ ስራዊት ወደ ሶማሊያ አጅቦ ለማስገባት በሚሞክርበት ጊዜ መሆኑ ታዉቃል።

በለድ ሃዋ ድንበር  አቅራቢያ ከትሞ የነበረው የኢትዮጵያ ሰራዊት  የሶማሊ ሚሊሺያ ጦር ከአልሸባብ የገጠመውን ውጊያ መቋቋም ተስኖት ሲያፈግፈግ ድጋፍ ለምስጠት በሚል የኢትዮጵያ ሰራዊት ውጊያውን ተቀላቅሏል።

የኢትዮጵያ ሰራዊት በከባድ መሳሪያ የታገዘ ከፍተኛ ውጊያ ማድረጉ የታውቀ ሲሆን፤ውጊያው የኬንያዋ ማንድራ ከተማ ድርስ ዘልቆ ሁለት የኬንያ ወታደሮች እና 6 ሲቪል ዜጎች  መጎዳታቸው ታውቃል። ሪፖርቱ ጨምሮ እንደገለጸውም የኬንያ ጉምሩክ ሰራተኞች እና ነዋሪዎች ተኩሱ ለ3 ቀናት ቀንና ለሊቱን ሙሉ መካሄዱን እና ስጋት ላይ መውደቃቸውንም አሳውቀዋል።

ከውጊያው ጋር ተያይዞ ከ300 በላይ የሚሆኑ ሶማሊያውያን እካባቢያቸውን ለቀው መሰደዳችውም ታውቋል። 2000 የሚሆኑት የሶማሊያ  የሽግግር መንግስት ወታደሮች እና የኢትዮጵያ ስራዊት አሁንም ድረስ ሱፍቱ በመባል የምትጠራው ከተማ መስፈሩ ታውቋል። ኬንያ የራሱዋን ስራዊት ውደ ስፍራው ለመላክ መዘጋጀቷም ታውቋል።

ከዚህ ጋር ተያይዞም ኢትዮጵያና ኬንያ ወንጀለኞችንና የጦር መሳሪያ ለመቆጣጠር  በሚል በቅርብ ያደረጉትን ስምምነት ተከትሎ 110 የሚደርሱ ታጣቂዎችን በጋራ ማሰራችውን  የኬንያው  ዘ ደይሊ ዘግቧል። እስሩ 45 ከባድ መሳሪዎችና ቦምብ የታጠቁ ታጣቂዎችን ያካተተ ሲሆን ፤ቀሪዎቹ ግን ኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን የመብት ረገጣና አፈና ሸሽተው በኬንያ በስደት ላይ የሚግኙ የኦሮሞ ተወላጆች ላይ ያነጣጠረ መሆኑም ታውቃል።

ምንም እንኳ የኢትዮጵያ መንግስት የኦነግን መዋቅርና ሕልውና አጥፍቻለሁ እያለ ቢደሰኩርም ከ1973 ዓ.ም  ጀምሮ በትጥቅ ትግል ላይ ያለው ኦነግ ዛሬም ድረስ በትጥቅ ትግሉ ውስጥ ያለ መሆኑ ይታወቃል።

Advertisements
%d bloggers like this:
search previous next tag category expand menu location phone mail time cart zoom edit close