አሜሪካ ዜጎችዋ ወደ ኤርትራ እንዳይጓዙ አስጠነቀቀች

Flag of Eritrea

አሜሪካ ዜጎችዋ ወደ ኤርትራ እንዳይጓዙ አስጠነቀቀች

march 1/2011

  • ኤርትራ እና ኢትዮጵያ ጦራቸውን፡ወደ ድንበር አስጠጉ
  • አልሸባብ በአካባቢው ጥቃት ለማድረስ መዘጋጀቱን ተገለጸ
ዋሽንግተን: የአሜሪካን ስቴት ዲፓርትመንት ሊደርስ ከሚችል ከአሽባሪዎች ጥቃት እና በኤርትራ እየተካሄደ ባለው የእስርና የማማፈን ሁኔታን የሚያሳይ ሪፖርት ከተምልከተ በኋላ ዘጎቹ ወደ ኤርትራ እንዳይጓዙ አስጠነቀቀ። ዲፓርትመንቱ ባወጣው መግለጫ መሰረት ብዛት ያላቸውና በዜግነት ጥምር አሜሪካን የሆኑ ኤርትራዊያን እየታሰሩ መሆኑንና ምክንያቱ ግልጽ ባልሆነ መንገድ ለረጂም ጊዜያት ወደ ወህኒ እንደሚጣሉ ጭምር ገልጿል።
ማስጠንቀቂያው ጨምሮ እንዳተተውም በዚያች ሀገር ያለው የእስር ሁኔታ በጣም አስከፊ መሆኑንና እስረኞችም መኝታ፣ ምግብ ፣መጸዳጃ ኣና ንጹሕ ውሃ እንኳ እንደማያገኙ ይገልጻል። በተጨማሪም የኤርትራ መንግስት የአሜሪካን እና የኤርትራ ጥምር ዜግነት ያላቸውንም ሆነ ትውልደ አሜሪካውያኑን ሲያስር ለአሜሪካን መንግስት እንድማያሳውቅም ገልጻል።
በታህሳስ ወር በአካባቢው ነዳጅ በመሙላት ላይ የነበሩ አራት የእንግሊዝ መርከብ ሰራተኞችን የጫነች መርከብን የኤርትራ መንግስት ባለስልጣናት ማሰራቸውን ጭምር በመግለጽ አስጠንቅቋል።
በተጨማሪም ወደ ሰፍራው ለመጓዝ የሚፍልጉ የአሜሪካን ዘጎች በአሁን ሰአት በሰፍራው በኤርትራ እና በኢትዮጵያ መንግስት መካከል የነገሰውን ፖለቲካዊ ውጥረት እንዲያጤኑ ጭምር አሳስቧል። ሁለቱም ህገሮች ጦራቸውን፡ወደ ድንበር ማስጠጋታቸውም አያይዞ ገልጿል። ዲፓርትመንቱ በቀጥታ በአሜሪካን ዜጎች ላይ ያነጣጠረ ጥቃት እንደሚደርስ መረጃ ባይደርሰውም ይሁንና አልሸባብ በአካባቢው ጥቃት ለማድረስ መዘጋጀቱን እንደደረሰበት ገልጻል። በመጨረሻም የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስተር ከዋና ከተማው ከአስመራ ውጭ ርቀው ለሚጓዙ ዜጎቹ የአስችኳይ ጊዜ ርዳታ ለመስጠት እንድማይችል በመግለጽ አስጠንቅቋል።

 

Advertisements
%d bloggers like this:
search previous next tag category expand menu location phone mail time cart zoom edit close