የታክሲ ሹፌር በላስቬጋስ ተገደለ

 

የ30አመት ወጣት የሆነው እና ከትውልድ ሃገሩ ከመጣ ዘጠኝ ወራትን ያስቆጠርው ወጣት ተስፋዬ ኪሞ አርዜ በዘራፊዎች መገደሉ ተገለጸ ። የላስቨጋስ ሜትሮ ፖሊስ እንደገለሰው ወጣቱ የተገደለው አርብ እለት ማለዳ 9፡30 6300 ብሎክ ኦፍ ህይ ሴራ የተባለ ጎዳና ላይ መገደሉን የገለጸ ሲሆን ስራውን ከጀመረ 5 ሳምንታትን ያስቆጠረው ይህ ወጣት በስራው ላይ ሳለ ተሳፋሪዎቹን ወይንም  ተጠርጣሪዎችን ወደ ቤታቸው አድርሶ ሊመለስ ሲል እራሳቸው ተሳፋሪዎቹ ዘርፈው ገድለው እንደጣሉት ገልጸዋል።ሟች ተስፋዬ ከሃገሩ እና ከቤተሰቡ ተለይቶ ወደ ምድረ አሜሪካ ከመጣ ዘጠኝ ወራትን ከማስቆጠሩም በላይ ለረጂም ወራት ስራ ሳይኖረው ተቀምጦ የነበረ ሲሆን ስራውን በጀመረ በአጭር ጊዜያት ውስጥ ህይወቱን ማጣቱ በላስቬጋስ ያሉ ኢትዮጵያኖችን አሳዝኖአል አስቆጥቶአልም ይህ በእንዲህ እንዳለ የወጣቱን አስከሬን ወደ አገር ቤት ለመላክ በላስቬጋስ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኮሙኒቲ የተለያዩ የገንዘብ ማሰባሰብ ዝግጅት ላይ ሰለሆነ ማንኛውም ኢትዮጵያዊ የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣ ጥሪውን አስተላልፎአል !!

 

Advertisements

1 thought on “የታክሲ ሹፌር በላስቬጋስ ተገደለ

Comments are closed.

%d bloggers like this:
search previous next tag category expand menu location phone mail time cart zoom edit close