ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ በኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ ላይ ማብራሪያ ሊሰጥ ነው

(ቅዳሜ መጋቢት 2 ቀን 2003 ዓ.ም. March 11, 2011)፦ ሚኒሊክ፣ አስኳልና ሳተናው በተባሉትጋዜጦቹ የሚታወቀውና በአሁኑ ሰዓት በህትመት ስራ ላይ እንዳይሳተፍ የታገደው ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ፤ በተለይለአቶ መለስ ዜናዊ በጻፈው ግልጽ ደብዳቤና በወቅታዊ የኢትዮጵያ ጉዳዮች ዙሪያ በሬዲዮ ውይይት እንደሚያደርግተገለጸ።ከካናዳዋ መናገሻ ኦታዋ በየሳምንቱ ከሚተላለፈው የአማርኛ ስርጭት አዘጋጆች ጋር በቀጥታ ውይይት የሚያደርገውጋዜጠኛ እስክንድር በአረብና ሰሜን አፍሪካ ሀገራት የሚካሄደው ህዝባዊ አመጽ ከኢትዮጵያ የፖለቲካ አንድምታ ጋርበማያያዝ ያለውን ልምድ የሚያካፍል ከመሆኑም በላይ ከአድማጮች የሚቀርቡ ጥያቄዎችንም እንደሚያስተናግድታውቋል።ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ከሁለት ሳምንት በፊት ለአቶ መለስ ዜናዊ ህዝቡ ለውጥና ከስልጣን እንዲወርዱ እንደሚፈልግበላከው ግልጽ ደብዳቤ http://ethiomedia.com/above/2220.html ራሱ ለረጅም ግዜ ከኖረባትና ከተማረባት አሜሪካተሞክሮ ጋር በማጣቀስ ኢትዮጵያ ውስጥ ለምን ለውጥ እንደሚያስለፈልግ አትቷል። “እንዳለመታደል ሆኖ ከአሜሪካመሪዎች በተቃራኒ የኢትዮጵያ መሪዎች ከረዳቶቻቸው እውነተኛ ምክር አያገኙም። በኢትዮጵያ በዚህ አርባ አመትውስጥ ብዙ ነገሮች እንደተለዋወጡ፡ አንዳንድ ነገሮች ግን ፈጽሞ እዚያው ባሉበት እንዳሉ ያስረዳው እስክንደርከነዚህም አንዱ መሪዎች ማወቅ የሚገባቸውን ሳይሆን መስማት የሚፈልጉትን ብቻ ነው አንደሚነገራቸውአስረድቷል።ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ለአቶ መለስ በጻፈው ግልፅ ደብዳቤ ላይ በመቀጠልም ልክ በኮሎኔል መንግስቱ ግዜእንደነበረው፡ “በዚህ የስልጣን ዘመንዎት ስልጣንና ጥቅም አናታቸው ውስጥ የነገሰው ረዳቶችዎ ስለኢትዮጵያ ህዝብየሚነግሩዎት ምክር ‘በፈጣን የምጣኔ ሀብት እድገትና በተረጋጋ ፖለቲካ የፈነደቀ ህዝብ፣ ደስተኛና ተስፋ የሞላበትወጣት እንዲሁም ያለፈለት ገበሬ፤ በሌላ አነጋገርም በመለስ የማይተካ አመራር ስር ሆኖ ወደ እድገት ሊመነጠቅያኮበኮበ ህዝብ” እንደሆነ፡ ነገር ግን እውነታው ያ ሳይሆን፡ ተራው የኢትዮጵያ ህዝብ “ሰማይ በነካ የዋጋ ግሽበትየተቃጠለ፡ ታይቶ በማይታወቅ ሙስና እና ለከት ያጣ ስራ እጥነት፤ በፖለቲካ ጭቆና፣ በመራር የመሬት እጥረትያረረና የተመዘበረ ሕዝብ ነው። በጥቅሉ ሕዝቡ ለውጥ ይፈልጋል።” ሲል ጽፏል።ቀጥሎም፡ አቶ መለስን “ለውጥ ሊያመጡ ይችሉበት የነበረውን ሀያ አመት እምሽክ አድርገው አባከኑት። እነሆ በርስዎአመራር ‘በተግባራዊነት ቦታ ግትርነት ተንሰራፋ። በግልጽነት ቦታ ምስጢራዊነት ስር ሰደደ። በዴሞክራሲ ፈንታጭቆና ጣሪያ ነካ። ከችሎታ ይልቅ ዝምድናና አድርባይነት በልጠዋል፡” ብሎ በመጨረሻም፡ “አቶ መለስ የኢትዮጵያህዝብ በሊቢያና በሰሜን አሜሪካ እንዲሁም በአረቡ ዓለም እየሆነ ባለው ነገር እጅግ በጣም ተስፋው ለምልሟል። በልበሙሉነት ተሞልቷል።” ህዝቡ፤ ነገሮች ፈር ለቀው ሳይሄዱ በፊት (ደም ሳይፋሰስ ማለቱ ነው) ስልጣን እንዲለቁይፈልጋል።” በማለት ለአቶ መለስ ዜናዊ የጻፈውን ግልጽ ደብዳቤ ደምድሟል። በደብዳቤው ዙሪያና በኢትዮጵያመጻኢ እድል ላይ ለመምከር፡ በኦታዋ የኢትዮጵያ ራዲዮ አዘጋጅ፡ ተክለሚካኤል አበበ ጋር ግልጽ ውይይትእንደሚያደርግ ከስፍራው የደረሰን መረጃ ያስረዳል።እስክንድር ነጋ ከሰባት ጊዜ በላይ በእስር ቤት የተጣለና በአሰቃቂ ሁኔታ የተደበደበ ሲሆን፡ ባለቤቱ የሰርካለም አሳታሚባለቤት ወ/ሮ ሰርካለም ፋሲልም፤ በግፍ ከነበረችበት የቃሊቲ እስር ቤት ውስጥ መውለዷ የሚታወስ ነው። እስክንድርነጋ፡ ሕገ-መንግስታዊውን ስርአት በሀይል ለመናድ ተወንጅሎ ከታሰረበት እስርቤት ከተፈታ በኋላ፤ በግሉም በጋዜጣአሳታሚ ድርጅቱ በኩልም ከ150 ሺህ ብር በላይ ቅጣት እንዲከፍል እንደተወሰነበት የሚታወቅ ሲሆን፤ ላለፉት ሁለትአመታት በሚጽፋቸው ጠንካራ ሳምንታዊ ፖለቲካዊ ጽሁፎች ይታወቃል። እስክንድር ነጋ ከወር በፊት አዲስ አበባፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ለሰዓታት ታስሮ የተለቀቀ ሲሆን፡ አሁንም በኢትዮጵያ የቱኒሲያና የግብጽ አይነት አመጽለመቀስቀስ ትጥራለህ በሚል ሰበብ ሊታሰር ይችላል የሚል ስጋት ይንሸራሸራል።በዚሁ በመጭው እሁድ ማርች 13/11 ከሰዓት በኋላ በምስራቅ አሜሪካን ሰዓት አቆጣጠር ከ2 እስከ 3 ሰዓት (SundayMarch 13, 2pm – 3pm) ዝግጅቱን በሚከተለው ድረ ገጽ መከታተል ይችላሉ። http://www.chuo.fm/en/home, CHUO

Advertisements

1 thought on “ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ በኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ ላይ ማብራሪያ ሊሰጥ ነው

Comments are closed.

%d bloggers like this:
search previous next tag category expand menu location phone mail time cart zoom edit close