በእንግሊዝ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን የተቃውሞ ሰልፍ ወጡ።

በሰላም ድጋፍነህ

በጭቆናና አፈና ውስጥ የሚኖር ህዝብን በኑሮ ውድነት በማሽቆጥቆጥ ላይ የሚገኘውን የኢትዮጵያ መንግስት በመቃዎም በእንግሊዝ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን የተቃውሞ ሰልፍ ወጡ።

ኢትዮጵያውያኑ “የመለስ አገዛዝ ያብቃ፤ የእንግሊዝ ፓርላማ የኢትዮጵያ ሕዝብን እንጂ ሰው በላና አምባግነኑን የመለስን አስተዳድር መደገፉን ያቁም፤ ትናንት ቤናሊና የግብጹ ሙባርክ፡ ዛሬ  ጋዳፊ ነገ ደግሞ መለስ….” የሚሉ እና ሌሎች መፈክሮችን ይዘው አደባባይ ወጥተዋል።

ክንፈ የተባሉ አንድ ሰልፈኛ  “ለሃያ አመት ያህል የብሄር ልዩነትን በመካከላችን በመፍጠር ሲገድልና ሲያቆስለን የቆየውን መንግስት ለማስወገድ ጊዜው አሁን ነው።ባሁን ሰአት በሃገራችን የእስልምና ሃይማኖት ተከታዮችን ተገን በማድረግ ህዝቡን ማናከሱ  ሊመጣበት ያለውን ተቃውሞ ለማዳፈን ታስቦ ነው፤ ኢትዮጵያውያን አንድ ሆነን ልንዋጋው ይገባል።” በማለት ገልጸዋል።

ሰልፈኞቹ ለፓርላማው የእንግሊዝ መንግስት ለመለስ ዜናዊ መንግስት የሚሰጠውን እርዳታ ያቆም ዘንድ እና የኢትዮጵያውያንን ምርጫ ያከብር ዘንድ ጠይቅዋል።

Advertisements
%d bloggers like this:
search previous next tag category expand menu location phone mail time cart zoom edit close