50 በርሜል አዲሱ ባለ አንድ ብር ሣንቲም ከኢትዮጵያ ሲወጣ ተያዘ

ANO: 50 በርሜል ሙሉ አዲሱ የኢትዮጵያ ባለ አንድ ብር ሣንቲም በኮንትሮባንድ ከኢትዮጵያ ሊወጣ ሲል በኢትዮጵያና ኬንያ ፖሊሶች ትብብር ድንበር ላይ በቁጥጥር ሥር መዋሉን ምንጮች አስታወቁ፡፡

በኢትዮጵያና ኬንያ ድንበር ላይ በቁጥጥር ሥር የዋለው 50 በርሜል ሙሉ ባለ አንድ ብር ሣንቲም በቁጥጥር ሥር የዋለው በኢትዮጵያዊያን እና ኬንያዊያን ትብብር ነው። በአሁኑ ጊዜ በበርሜል የታሸጉት ባለ አንድ ብር የኢትዮጵያ ሣንቲሞች ወደ ኢትዮጵያ እንዲመለሱ ተደርጎ በፌዴራል ፖሊስ እና በብሔራዊ ባንክ ሥር እንደሚገኝ ለማወቅ ተችሏል፡፡

አዲሱ ባለ አንድ ብር ሣንቲም የመሐል መደቡ ላይ በቅይጥነት የተሰራበት መዳብ ትንንሽ የሞተር ጥርሶች (ጊር) ሊሰራበት ስለሚችል በቅርቡም መኖሪያቸውን ኢትዮጵያ ያደረጉ ቻይናዎች በድብቅ በሻንጣዎቻቸው አከማችተው ይዘው ሊወጡ ሲሉ በቁጥጥር ሥር ውለው ነበር። “ምናልባትም በቅርቡ መንግስት አዲሱ ባለ አንድ ብር ሣንቲምን በመሰብሰብ ሥራ ላይ እንዳይውል ሊያደርግ ይችላል” ሲሉ ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ምንጭ ለሪፖርተራችን ተናግረዋል።

አንድ ብር የወረቀት ገንዘብን ለማተም የሚወጣውን ወጪ ከገንዘቡ የመገበያያ ዋጋ (ዕሴት) እጅግ እንዲቀንስ ታስቦ የተዘጋጀው ባለ አንድ ብር ሣንቲም ገና ሳይቆይ ከገንዘቡ ዋጋ ይልቅ ሣንቲሙ የተሰራበት ብረትና መዳብ ዋጋው ልቆ በመገኘቱ ለሌላ የፋብሪካ ሥራ ጥቅም ላይ ለማዋል የሚሯሯጡ ግለሰቦችና ቡድኖች በዝተዋል፡፡

የአንድ ብር ሳንቲም ከሀገር ሲያሰውጡ ነበር የተባሉ ተጠርጣሪዎች ጉዳይ በቅርቡ በኮልፌ- ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በቅርቡ መታየት ይጀምራል ብለውናል-ምንጮች

Advertisements
%d bloggers like this:
search previous next tag category expand menu location phone mail time cart zoom edit close