ባን ኪ-ሙን አምባሳደር ሳህለወርቅ ዘውዴን ሾሙ

Reporter የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸሐፊ ባን ኪ-ሙን ኢትዮጵያዊቷን አምባሳደር ሳህለወርቅ ዘውዴን፣ በኬንያ ናይሮቢ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጽሕፈት ቤት ዳይሬክተር ጄነራል ሆነው እንዲያገለግሉ ሾሟቸው፡፡ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽሕፈት ቤት እንዳስታወቀው፣ አምባሳደር ሳህለወርቅ ዘውዴ አዲስ የተቋቋመውን የናይሮቢ ጽሕፈት ቤት የሚመሩት በተባበሩት መንግሥታት ምክትል ዋና ጸሐፊነት (Under-Secretary-General) ማዕርግ ነው፡፡

አምባሳደር ሳህለወርቅ ቀደም ሲል በተባበሩት መንግሥታት ድርጀት ዋና ጸሐፊ ባን ኪ-ሙን የማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ ልዩ መልክተኛ ሆነው ሲያገለግሉ ቆይተዋል፡፡ በዚህም በዋና ጸሐፊው በዚህ ደረጃ በዓለም የተሾሙ ሁለተኛዋ ሴት ያደርጋቸዋል፡፡

ከዚህ ሹመት በፊት አምባሳደር ሳህለወርቅ በፈረንሳይ፣ በጂቡቲና በሴኔጋል የኢትዮጵያ መንግሥት ባለሙሉሥልጣን አምባሳደር፣ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ ጉዳዮች ዳይሬክተር ጄነራል፣ በአፍሪካ ኅብረት፣ በአፍሪካ ኢኮኖሚ ኮሚሽን፣ በምሥራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግሥታት (ኢጋድ) እንዲሁም በዩኔስኮ የኢትዮጵያ ቋሚ መልዕክተኛ ሆነው ማገልገላቸውን ከቃል አቀባይ ጽሕፈት ቤት የወጣው መግለጫ ያመለክታል፡፡

Advertisements
%d bloggers like this:
search previous next tag category expand menu location phone mail time cart zoom edit close