በታላቁ ቤተ መንግሥት እየተገነባ ያለው ቤት ለኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትሮች መሆኑ ተገለጸ

በታላቁ ቤተ መንግሥት እየተገነባ ያለው ቤት ለጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ብቻ ሳይሆን፣ ከእሳቸው ቀጥለው ወደ ሥልጣን ለሚመጡት  የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትሮች እንደሆነ ተገለጸ፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ የቤቱን ፕሮጀክት ሁለት ጊዜ ተቃውመውት እንደነበርም የገለጹት ምንጮች፣ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ፕሮጀክቱን እንዲቀጥል የተስማሙት ቀጣዩ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤቱን ሊገነባ እንደማይችል በመረዳታቸው ነው፡፡ ምክንያቱንም ሲያስረዱ፣ ቀጣዩ ጠቅላይ ሚኒስትር ሥልጣኑን ተጠቅሞ ቤቱን አስገነባ ሊባል ስለሚችል፣ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ቤቱ በእሳቸው የሥልጣን ዘመን እንዲገነባ ስለተስማሙ ነው፡፡

በታላቁ ቤተ መንግሥት የሚገነባው ቤት ከ80 ሚሊዮን ብር በላይ የሚፈጅ ሲሆን፣ በሁለት ዓመት ውስጥ ይጠናቀቃል ተብሎ ይገመታል፡፡

Advertisements
%d bloggers like this:
search previous next tag category expand menu location phone mail time cart zoom edit close