ታላቁ ግድብና የዓባይ ትኩሳት እና የዲሞክራሲያዊ ሂደት በኢትዮጵያ

ኢትዮጵያ ከውኃ 45ሺሕ ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ኃይል የማግኘት ተስፋ እንዳላት ቢነግርም፣ በአሁኑ ጊዜ ከ12 የኃይል ማመንጫ ጣቢያዎች እያመነጨችው ያለችው ሁለት ሺሕ ሜጋ ዋት ብቻ ነው፡፡ይህንን ሁኔታ በእጅጉ ለመለወጥ የተነሳው የኢትዮጵያ መንግሥት በሚቀጥሉት አምስት ዓመታት ውስጥ ስምንት ሺሕ ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ኃይል ለማመንጨት አቅዷል፡፡ በአሁኑ ጊዜ በግልገል ጊቤ ሦስት የኃይድሮ ኤሌክትሪክ ኃይል ግንባታ እያካሄደ ሲሆን፣ ከዚህ ፕሮጀክት 1,870 ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ኃይል ይጠበቃል፡፡

በትናንትናው ዕለት በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ከሱዳን ድንበር ከ20 እስከ 40 ኪሎ ሜትር ውስጥ ሊገነባ የታሰበው “ታላቁ የሚሊኒየም ግድብ” የመሠረት ቁፋሮ ከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናት በተገኙበት ተከናውኗል፡፡ ይህ ከ70 ቢሊዮን እስከ 80 ቢሊዮን ብር ይወጣበት የተባለው ፕሮጀክት 5,250 ሜጋ ዋት እንደሚያመነጭ ታውቋል፡፡ ግድቡ ከ62 ቢሊዮን ሜትር ኩብ በላይ ውኃ ወይም የጣና ሐይቅን እጥፍ ይይዛል ተብሏል፡፡

“በታላቁ የሚሊኒየም ግድብ የደኀንነት ጥያቄ አያሰጋንም፤” ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ፣ ኢትዮጵያ በዓባይ ላይ ግድብ እንዳትሠራ እንቅፋት ናቸው ያሉዋቹውን አንዳንድ የአካባቢ ተቆርቋሪዎችንና የግብፅ ፖለቲከኞችን “ጽንፈኞች” ሲሉ ወርፈዋቸዋል፡፡ በምድራችን ላይ የትም ቦታ ግድቦች ይሠሩ ቢባል ኢትዮጵያ ቀዳሚዋ ተመራጭ ናት ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ የአገሪቱ የኤሌክሪክት ኢንቬስትመንት በአካባቢ ጥበቃም ሆነ በማኀበራዊ ኃላፊነት ላይ መመስረት አለበት ብለዋል፡፡

በዚህ መንግሥት ዘመን በዓባይ ተፋሰስ ላይ የተጀመሩት የኤሌክትሪክ ኃይል ፕሮጀክቶች ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ውጥረት ውስጥ ያሉትን የግብፅ ባለሥልጣናትን ጭምር እያሳሰቡ መሆኑ ቢነገርም፣ ኢትዮጵያ ግን በእነዚህ ፕሮጀክቶች ምክንያት ግብፅና ሱዳን ተጎጂዎች ሳይሆኑ ተጠቃሚ መሆቸውን እየገለጸች ነው፡፡ በተለይ ግብፅ ከጥንት ጀምሮ በኢትዮጵያ ላይ የምታራምደው ፖሊሲዋና በዓባይ ላይ ፍትሐዊ ተጠቃሚነት እንዳይኖር ትሸርበዋለች የሚባለው ሴራም በብዙዎች አዕምሮ ውስጥ ይመላለሳል፡፡ መንግሥት ዓባይ ላይ ሰፊ ፕሮጀክቶችን ማቀድ ከጀመረ ወዲህ የዓባይ ፖለቲካ ትኩሳት ጨምሯል፡፡

በእርግጥም እንደ ጠቅላይ ሚንስትሩ አባባል ከሆነ የኢትዮጵያ እድገት በአስር እጥፍ ከማድጉ ወድሗላ እንደማይል ልንገነዘብ እንችላለን ነገር ግን የወሬ ቱባ የሚያውቁት የወያኔው ጠ/ሚኒስትር በየአመቱ የሚያመጡት አዳዲስ ወሬዎች ህዝቡን ለተወሰነ ቀናት አስፈንድቆ ንፋስ እንዳበነነው ገለባ ብን ብሎ የሚጠፋ ሃሳብ መሆኑን ማንም ልብ ያለው ሰው ሊገነዘበው ይችላል እንደምሳሌ ያህል ለመጥቀስ ባለፉት አምስት እና ስድስት አመታቶች የኢትዮጵያን የግብርና ልማተ ግባት ለማፋጠን እና ለማሳደግ የሚያስችለን ወሃ በማቆር ጉድጓድ በመቆፈር ነው በማለት የገጠሩን ህዝብ በከፍተኛ ደረጃ ለውሃ ወለድ በሽታ፣ለወባ በሽታ እና እንደዚሁም አካባቢን ለአየር ብክለት ዳርገው የተሟላ ህክምና በሌሉባቸው ቦታዎች አያሌ ገበሬዎች ለህልፈተ ሞት ዳርገዋቸዋል ይህ ጥናት የጎደለው አሰራራቸው ተጀምሮ ከጥቅሙ ጉዳቱ ሲያመዝን እንደተቛረጠ ማንም ያውቀዋል ከዚያም በመቀጠል በቅርቡ የሚልኒየሙ ታላቁ መርሃ ግብራቸው የነበረው የትራንስፎርሜሽን እቅድ እያሉ የቃላት ጨዋታ የሚያውቁት የወያኔው ጠቅላይ ሚኒስትር የኢትዮጵያን ህዝብ በቃላት ማፍዘዛቸው ዛሬ እንዳዲስ ያልተለመደ ተግባር ቢሆንም የትራንስፎርሜሽን እቅድ ተግባሩ ምንም ሳይከናወን ሚሊኒየም ከተጀመረ ሶስት አመታት ተቆጥሮ አንዳችም ነገር በሃገሪቱ ላይ ለውጥ ሳይመጣ የኑሮ ወድነት ወይም ግሽበት እያየለ መምጣቱ ይህ የእነሱ የሚሊኒየሙ የትራንስፎርሜሽን ትልቁ እቅዳቸው እና የእድገት ተግባራቸው መሆኑን በገሃድ አሳይተዋል ይህ በእንዲህ እንዳለ ደግሞ በአሁን ሰአት ጎልቶ የሚታየው የአባይ ተፋሰስ ውሃን በመገደብ ግድብ እንሰራለን እያሉ የኢትዮጵያን ህዝብ ከአለበት ሃሳባዊ የመንግስት ለውጥ እይታ አይኑን እንዲያነሳ ለማድረግ የተጠቀሙበት ትልቅ ዘዴ እንደሆነ ለመገመት አያዳግትም ምክንያቱም በአፍሪካ እና በአረብ አገሮች የተቀሰቀስው አመጽ አብዛኞቹን  የኣለም መንግስታት ክፉኛ ፍራጫ ውስት  የከተት እና ሁኔታው ስራቸውን ያደናገረ እና ያደናቀፋቸው መሆኑን ጠንቅቀው ስለተረዱት ይህንን ሁኔታ በእነሱ እንዳይደርስ ለማክሸፍ ከተጠቀሙበት ዘዴ አንዱ የሆነው የአቶ መለስ ዜናዊ ቅናዊ ልብ መስለው ለስልጣን ማስረዘሚያ የተጠቀሙበት ሃሳባዊ ሰይጣን እንጂ በእውነቱ ይህንን ካደረጉ እማ እሳቸው በሃገሪቱ ላይ ትልቅ ሃውልት ሊቆምላቸው በተገባ ነበር ግን ምን እና እንዴት ከየት እና በየት የሚሉተን ሃተታዊ መስፈርቶች በስነ ስራት ለመመለስ አንገታቸውን ቀና አድርገው የነጻ ሚዲያንም በግንባራቸው አይተው የማያውቁት አባ በመለስ ዘናዊ የተደበቀው እፍረታቸው እንዳይወጣባቸው ስለሆነ ይህንን እንደ ህልም እንጀራ እንቆጥረዋለን የምንቆጥረውም ይህ ሃሳባቸው ከፍጻሜ እስካልደረሰ ድረስ ማንም እማኝነትን ለመስጠት የሚያስችል ነገር ማውራት አይችልም እና ነው ለምን ብትሉ በወረቀት ላይ ግድብ ሊሰራ ነው ተብሎ ማስፈር ተሰርቶ ተጠናቀቀ ማለት አይደለም ። በውሸት ቱባ ቱባ ወሬ የሚያለብሱን የአቶ መለስ ወሬ ስለማያልቅ ዛሬ እኛነታችንን ለማወቅ በደፈናው ሳይሆን ባለፉት ሃያ አመታት ምን በለው አለፉ ብለን ማለት ይገባናል እንደምሳሌ ያህል መጥቀስ ካስፈለገም በግንቦት ወር 1993 አመተ ምህረት ወያኔ ከጫካ ቅማሉን አራግፎ ወደ አዲስ አበባ በገባበት ወቅት አቶ መለስም የሰይጣን ቁራጭ የመሰለ ፊታቸውን በቴሌቪዥን መስኮት አውጥተው ዳግም ኢትዮጵያ ወደ ጦርነት ላትመለስ በዚያው የጦርነት አውድማው እንዳለቀ ፈስመው ተናግረው ነበር ነገር ግን ከአንድም ሁለት ሶስት ጦርነቶችን በሃያ አመታት ውስጥ ሲያደርጉ በሃገራችን አንድም የጥይት ጩኸት አይሰማም ያሉት አያ ዜናዊ በእየእለቱ በአጋዚ ጦሮቻቸው የደሃውን ልጅ መድፋት ከተያያዙት ሰንበትበት ብለዋል ለማንኛውም ይህንን ሁሉ ሃተታ ወደ ሗላ ሄጄ እንድቃና ያደረገኝ የእሳቸው በየጊዜው የሚፈጥሩት ወሸት ነውና እባካችሁ ንቃተ ህሊናቸሁን ከእሳቸው ምላስ ቀድማችሁ ተጓዙ ለማለት ነው ።

Advertisements
%d bloggers like this:
search previous next tag category expand menu location phone mail time cart zoom edit close