የመጽሀፉ ስም፦ ጥሎ ማለፍደራሲ፦ አበራ ለማ እይታ

Ethiopia zare:‘ጥሎ ማለፍ’ን እንዳየሁትየመጽሀፉ ስም፦ ጥሎ ማለፍደራሲ፦ አበራ ለማ እይታ፦ በአቢይ አፈወርቅፍርሃት… ሽብር… ጥርጣሬ!… ዘመኑ የአደጋ ነው። በእያንዳንዱ ህልመኛ ዙሪያየስጋት ደመና አንዣቧል። ማንም ማንንም አያምንም፤ ጠላትና ወዳጅየማይለይበት ጊዜ!… ሁሉም ትላልቁን ወንበር ያልማል። ተጫራቹ ብዙ፤ መድረስየሚችለው ግን ጥቂቱ ነው። ‘ጥሎ ማለፍ’ የሚችለው ብቻ።…ጠላትን ጥሎ ማለፍ!… ወዳጅን ጠልፎ ማለፍ!… ፊት ለፊት ተጋትሮ መጣል!…አቅፎ ደግፎ መጣል!… ነፍስ የረከሰባት ዘመን!… ሞት የነገሰባት አገር!…1969 ዓ.ም – ኢትዮጵያ!ንቁ የፖለቲካ አራማጅ የነበሩት ኢህአፓና መኢሶን በከተማው ትግል በከፍተኛደረጃ ተዳክመዋል። ኢህአፓ ከመሰረቱ ከደርግ ጋራ አልተግባባም። ሁለቱምበማይፈቱ ልዩነቶች ተፋጠው ፍልሚያ ቆሙ። ከዚህም ከዚያም ጎራ ሞት ታወጀ…እልቂት!መኢሶን የደርጉ ወዳጅ ነበር። ተቀናቃኞቹን በደርግ ክንድ ጥሎ ለማለፍ የወሰነ።የታቀፈ። የተሳመ። አብሮ በጋራ ጠላት ላይ የዘመተ፤ በማግስቱ ግን ጠላት ሆነ።ደርግን ጥሎ ማለፍ አልቻለም። ይልቅስ ደርግ ጥሎት ሊያልፍ ተነሳ። እናምእየታደነ ተፈጀ…ሌሎች ወዳጅ የነበሩ ድርጅቶችም ምጥ ውስጥ ናቸው። በጥሎ ማለፍ ጨዋታውምናልባትም የላቀ ስሌት የነበረው ወዝሊግ ህልውናው ጥያቄ ውስጥ ወድቋል።ኢጭአት አደጋ ውስጥ ነው። ማሌሪድ ተስፋ ባይቆርጥም ‘ተራዬ መቼ የሆን?’በሚል ስጋት ተወጥሯል። ደርግ ብቻ የልብ ልብ ተሰምቶታል። ጠላቶቹን በጠላቶቹእያዳከመ፣ እያጠጠና እያበጠ መጥቷል። ሰደድ የተሰኘ ካባውን ለብሶ የቀረ ጠላትያስሳል…ግን ስጋት አለ። አሁንም ጓዶች ይመታሉ። በሰፈሩት ቁና ይሰፈራሉ። ደርገኛበጠላት ይበላል። ደርገኛ በደርግ ይመታል። በጠላት ጥይት ይቀለባል። በወዳጅካራ ይሰየፋል። ሕይወት ትጥማለች። ስልጣን ትጣፍጣለች። ግን ታስፈራለችም…1969 ዓ.ም።በዚህ ታሪካዊ ዘመን ነበር የደራሲ አበራ ለማ ‘ጥሎ ማለፍ’ ትረካዋንየምትጀምረው። መግቢያና ቅጥያዋን ሳትጨምር በ400 ገጾች በ24 ምእራፎችየተዋቀረችው ጥሎ ማለፍ በአንድ የስልጣን ማማ ላይ በነበረ የደርግ ቋሚ ኮሚቴአባል ህይወት ዙሪያ ነው የምታጠነጥነው። ይህ ቱባ ሹም ደግሞ አይነታ ሚናየነበረው እንደመሆኑ የህይወት ውጣ ውረዱን ስንቃኝ እግረ መንገዳችንንም የዛንልዩ ዘመን መራራ የፖለቲካ ህይወት ለመፈተሽ፣ ከስልጣኑ ዙሪያ የተኮለኮሉአይነኬ፣ አይደረሴ ይመስሉ የነበሩትን ገዥዎቻችንን ስብእና ለመቃኘት እድሉንእናገኛለን።ታሪካዊ ልቦለድ ከሌሎች የስነ ጽሁፍ ስራዎች ሁሉ የተለየ ባህሪ አለው።ምናልባትም ፈታኝነቱ ከሁሉ ሳይልቅ አይቀርም። ደራሲው አንድም፤ እንደ አንድታሪክ መዝጋቢ ታሪኩ እንዳይዛባ ከፍተኛ ምርምርና ጥናት ማድረግ አለበት። እንደልብ ወለድነቱ ደግሞ እያዋዛና ልብ እየሰቀለ አንባቢውን በምናብ ይዞ መንጎድይጠበቅበታል። የታሪክ ጸሀፊ እውነቱን መቅረጽ እስከቻለ ድረስ ለትረካ ውበት ብዙላይጨነቅ ይችላል። የልብ ወለድ ደራሲ ደግሞ የጥንካሬው አንዱ ገጽ የቋንቋውውበቱና የአንባቢውን ቀልብ የመግዛት ጉልበቱ ነውና የፈጠራቸውን ባህሪያትለታሪኩ በሚመቸው መልኩ የመቅረጽ፣ ትረካውንም ያምርልኛል ባለው ቦይየማፍሰስ ነጻነት አለው።የታሪካዊ ልቦለድ ጸሀፊ ግን በነዚህ ሁለት ዘርፎች አጣብቂኝ ውስጥ ሆኖ ስለሚጽፍነጻነቱ ግድብ ነው። ከእውነተኛው የታሪክ ፍሰት መጣረስ አይቻለውምና ገጸባህሪያቱን እንዳሻው የመቃኘት መብቱ ውስን ነው። ለዚህም ነው ታሪካዊ ልቦለድለመጻፍ የሰከነ አእምሮና በልምድ የተባ ብእር የግድ ነው የሚባለው።ከዚህ አኳያ የጥሎ ማለፍ ደራሲ ተሳክቶለታል ባይ ነኝ። ጊዜ ወስዶ ለመጽሐፉአስኳል የሆኑ እውነቶች ላይ በቂ ምርምር ማድረጉ በግልጽ ይታያል። በጊዜውወሳኝ የሆኑ ውሳኔዎች የተላለፉባቸውን ስብሰባዎች ቃለ ጉባኤዎችን ጨምሮየተለያዩ ሰነዶችን ተጠቅሟል። ምናልባትም በወቅቱ እውቅ ጋዜጠኛ የነበረ መሆኑመረጃዎችን በማሰባሰብ ሂደቱ ላይ አይነተኛ እገዛ እንዳደረገለት መገመት ይቻላል።በሌላ ጎኑ ደግሞ ‘ጥሎ ማለፍ’ ከአንድ ስሙር የፈጠራ ስራ የሚጠበቁትንመስፈርቶች ማሟላት የቻለች ስራ ሆና ቀርባለች። ገጸ ባህሪያቱ በወጉ ስለተሳሉባመሩበት ሁሉ አብረናቸው እንተማለን። አካሄድ አነጋገራቸው፣ አለባበስአስተሳሰባቸው ሳይቀር ፍንትው ብሎ ይታየናል። ሴራው በአግባቡ ስለተዋቀረታሪኩ ከምእራፍ ምእራፍ ተሰናስሎ ነው የሚወርደው። የዋናውን ገጸ ባህሪመጨረሻ በታሪክ የምናውቀው ቢሆንም እንኳን ሁሉን ረስተን በእለት ተእለትውሎው ምን ይገጥመው ይሆን እያልን ልባችን ይሰቀላል። ለዚህ ደግሞ ደራሲውበበርካታ የፈጠራ ስራዎቹ ብእሩን የሞረደ ልምድ ጠገብ ብእረኛ መሆኑ ሳይረዳውአልቀረም።‘ጥሎ ማለፍ’ ጥቂት ሰዎችን በስማቸው ከመጥራቷ ውጭ ለብዙዎቹ የሽፋን ስምሰጥታቸዋለች። ይሁንና ገጸ ባህሪያቱ ስእላዊ ሆነው ስለቀረቡልን ማን ማን እንደሆነለመለየት አንቸገርም። የአብዮቱን ታሪክ ዘመንተኞች ሆነው በመኖር ያስተዋሉብቻ ሳይሆኑ ሂደቱን በታሪክ የሚከታተሉ ወጣት አንባቢያን ሳይቀሩ የበኩላቸውንግንዛቤ ማሳደር እንዲችሉ ሆነው ቀርበዋል።በታሪኩ ሂደት ተመስጠን ሳናውቀው ራሳችንን ከነዚያ ሰማይ ጥግ ከነበሩ ሹማምንትመሀል እናገኘዋለን። አስገራሚ ባህሪያቸውንም እንታዘባለን። የፖለቲካአክሮባታቸው ልክ ይደንቀናል። ያንዳንዶቹን ጭካኔ፣ የሌሎቹን መሰሪነት፣ያንዳንዶቹንም የዋህነት እንታዘባለን።በመጸሀፉ ላይ የቀረቡልንን ስሞች ለገሰና እንዳለ፤ ሸዋንዳኝና ሽመልስ ወይንምብርሃነ መስቀልና ፍቅሬ (ወ.ዘ.ተ) እያልን በምናውቃቸው ስሞች ለመተካትአይገደንም። ይቺ ይቺን ለአንባቢያን ልተዋትና ዋናውን ገጸ ባህሪ ዳኛቸው ወረደንብቻ በዚህች ጽሁፍ ላይ በትክክለኛ ስሙ ልጠቅሰው ወደድኩ። ታምራት ፈረደብዬ።ዳኛቸው ወረደ (ታምራት ፈረደ) በስልጣን ማማ ላይ የተፈናጠጠ፣ ሻለቃ(ኮሎኔል)መንግስቱን ከምንም ነገር በላይ የሚያፈቅር ወጣት አብዮተኛ ነበር። በአለቃውከልክ በላይ የሚመካ! የስልጣን ጉጉትና በራስ መተማመን የነበረው! በወቅቱላመነበት ነገር ከልቡ የሚደክም። ደስታን ከልቡ የሚሻ፣ መቀለድ መዝፈን፣መጨፈር የሚወድ። ልቡ ለሴት ልጅ ውበት የምትቀልጥ።…በወቅቱ የደርግ ቋሚ ኮሚቴ አባልና ሌሎች ተደራራቢ የስራ ሀላፊነቶች የተሰጡትሰው ስለነበር አንባቢ የዳኛቸውን አይን ተውሶ፣ የዳኛቸውን ጆሮ ወርሶ ከሀገሪቱ ቱባቱባ መሪዎች ጋራ በወጉ የመተዋወቅ እድል ያገኛል። የሊቀመንበሩን ሴረኛነት፣የስጦታውን መሰሪነትና ጭካኔ፣ የእነ እንደሻውን ጭፍንነት… የወዝ ሊጎቹንየሸዋቀናና የነሽመላሽ የፖለቲካ አክሮባት፣ የነ ወልደየስ ልምጥምጥነት… አረስንቱ!?…ዳኛቸው ለሊቀመንበሩ ካለው ፍቅርና ለስልጣን ካለው ጥማት የተነሳ እጁን ብዙስህተቶች ውስጥ ይከታል። ሲጸጸት የምናየው ግን እጅግ ከመሸ ነው… ደራሲውዳኛቸውን ዋና ገጸ ባህሪ አድርጎ መጠቀሙ ያለምክንያት አይደለም። አንድምየነበረበት ቦታ የአገሪቱን መሪዎች ማንነትና ድርጊት በወጉ እንድናይ እድልስለሚሰጠን ይመስላል። የሰደድ፣ የወዝሊግና የማሌሪድ ሰዎችን ሚና እንድንፈትሽረድቶናል። በተለይም የጥሎ ማለፍ ትንቅንቁ፣ የርስ በርስ ሽኩቻውና የአገርንመጻኢ እጣ የሚቃኙ ውሳኔዎች እንዴትና ለምን እንደተላለፉ ለመታዘብአስችሎናል። እያዘንን… እየተቆጨን… እየተናደድን! ሁለትም የዳኛቸው የህይወትውጣ ውረድ ለየት ያለ ነውና ቀልብ ጠልፎ እስከመጨረሻው ገጽ በጉጉትሊያስኳትነን የሚችል በመሆኑ በተለይ የተመረጠ ይመስላል።በህይወቱ የመጀመሪያ ምእራፍ አብረነው ከደርግ ጽህፈት ቤት-ዘመቻ መምሪያ፤ከሊቀመንበሩ ጀምሮ በየቁንጮ ቁንጮ ሹማምንቱ ቢሮ እየገባን ምስጢርእንቃርማለን። በወቅቱ እሱም በተግባሩ እንደመሰሎቹ ደርገኞች ነበርና ስህተቶቹንእየታዘብን ነው የምንዘልቀው።መስከረም 27/1972ዓ.ም. ግን የዳኛቸው ህይወት ዳግም ላይታደስ ይቀየራል።ሰማይ ጥግ የከረመው ሰው ታች ወርዶ ሲከሰከስ እናየዋለን። ያውም በሚያስደንቅድራማ!።አ..ቤ..ት.. ከ..ዚ..ያ… በኋላ?! ህይወት ምንኛ ወጥመድ ናት!? የሰው ልጅ ምን ያህልፈተና ያልፋል? ያውም አገር ምድሩ የረገደለት፣ ‘ማን አክሎኝ’ ሲል የኖረ ህልመኛሰው ፈተና። ደግሞ የአቻ ወዳጆቹ ባፍታ ተኖ መጥፋት!።እየዋለ እያደረ ስለ ዳኛቸው ያለን ስሜት እየተቀየረ መሄዱ የግድ ነው። ሰው ሰውእየሸተተን ይመጣል። እናዝንለት ሁሉ እንጀምራለን። የጭንቀቱ ልክ ይረብሻል።የጣ ፈንታው ነገር ስሜት ሰቅዞ ይይዛል… በዚያ ላይ የሁለቱ ፍቅረኞቹ ነገር አለ።ምናልባትም የመጸሀፉን የማራኪነት ደረጃ አንድ እርከን የሰቀሉ ሁለት ቆነጃጅትሴቶች። ሁለት የመጭ ህይወታቸውን ስኬት ሲያልሙ ውለው የሚያድሩ ውቦች።እንከን የለሽ ሆነው ያልቀረቡ፣ በርግጥ የምናውቃቸው ያህል ሆነው የተሳሉ፣ ሩቅአሳቢ ቅርብ አዳሪ ሴቶች። ስንዱና ፍቅርተ።መጽሀፉ የቀረበው በሁለት አይነት የአተራረክ ስልት ነው። በሁሉን አወቅናበአንደኛ መደብ (እኔ) የትረካ ስልት። የመጀመሪያዎቹን አስራ አራት ምእራፎችየሚተርክልን ደራሲው ነው። የመጨረሻዎቹን አስር ምእራፎች ደግሞ ፍቅርተ።ፍቅርተ ልዩ ሴት ነች። ራስ ወዳድነቷ ልክ የለውም። ትረካዋ ደግሞ ውብ ነው፤በዚያ ላይ በእሷ እይታ መተረክ የምንጀምረው በታሪኩ ጡዘት ላይ በመሆኑንባባችንን ለማቋረጥ ጭራሽ የማይታሰብ ይሆንብናል። ፍቅርተ የጥንካሬዋን ልክታሳየናለች፤ ድክመቷንም ትነግረናለች። የዳኛቸውን የህይወት ዑደት ቁልጭአድርጋ ታስፈትሸናለች። በትዝታ የኋሊት መልሳ በአቢዮቱ የመጀመሪያ አመታትላይ ስለነበረው ዳኛቸውም ትነግረናለች።በኔ እምነት ጥሎ ማለፍ በወጉ ተበራይቶ የቀረበ ስራ ነው። ቋንቋው ውብና ቀላል፤ታሪኩ ተአማኒ፤ ባህሪያቱ የሚታዩና የሚዳሰሱ ናቸው። እንከን ማውጣት ግድካልተባለ በቀር ይህ ነው የሚባል ጉድለት አላገኘሁበትም። አንዳንዴ በታሪኩ ዑደትእየተንሳፈፍን ከገጽ ገጽ ስንተም የደረስንበትን ዘመን እስከመዘንጋት የምንደርስበትአጋጣሚ ከመኖሩ በቀር።www.ethiopiazare.com

Advertisements
%d bloggers like this:
search previous next tag category expand menu location phone mail time cart zoom edit close