Search

AFRO ADDIS

An Inspiring Voice against Despots!

Date

April 10, 2011

የኢሕአዴግ ስብሰባና የተቃውሞ ሰልፍ በሚኒያፖሊስ

ZHabesha

ከዚህ በታች የተጠናቀረውን፡የጽሁፍ፡ሪፖርታዥ ያቀረበልንን፡የዘሃበሻ፡ዋና፡አዘጋጅ፡ሄኖክ፡አለማየሁን፡እናመሰግናለን፡

12:30AM

መንገዶች ሁሉ ወደ ዳውንታውን ሚኒያፖሊስ ያመራሉ…. እኔም ወደዛው እየነዳሁ ነው።
“መጽሐፍ ቅዱስ የሚሰበከው ሃገር ሲኖር ነው” ሃይማኖት እና ፖለቲካ የተለያዩ ናቸው ለሚሉት ም ዕመናን ያስተላለፉት መልዕክት
11:30AM
የሚኒሶታው ቅዱስ ዑራኤል ቤተክርስቲያን ቆሞስ አባ ገ/ሚካኤል ሰው ዛሬ ሰልፍ እንዲወጣ ቢጠይቁም እርሳቸው ግን በሰልፉ ላይ እንደማይገኙ አስታውቀዋል። እርሳቸው የማይገኙት የቤተክርስቲያኑ ኮሚቴ ስለከለካላቸው መሆኑም ታውቋል። የኮሚቴውን አባል በስልክ አነጋግሬው “እኛ ወደ ሰልፉ እንሄዳለን። ወደ ሴናተሮች ጋር የምንሄድ ቢሆን ኖሮ አባም ይመጡ ነበር። እኛ የምንሄደው ለመጮህ ስለሆነ ይህ ለአባ አይሆንም” ብለዋል። ይህ በ እንዲህ እንዳለም ከኢቫንጀሊካል ቸርችም የተለያዩ ፓስተሮች እንደሚገኙ ሲበጠቅ ስማቸውን እስካሁን አልደረሰንም። Continue reading “የኢሕአዴግ ስብሰባና የተቃውሞ ሰልፍ በሚኒያፖሊስ”

Advertisements

በኢትዮጵያ የኑሮ ውድነት እና የነዳጅ ዋጋ እያየለ መጥቶአል

    • በዘላለም ገብሬ
      በኢትዮጵያ የነዳጅ ዋጋ ከጊዜ ወደ ጊዜ እያሻቀበ እየመጣ መሆኑን ከአካባቢው የተጘኘ መረጃ ያመለክታል  በዛሬ እለት በደረሰን መረጃ መሰረት የአገሪቱ የዋጋ ግሽበት እና የኑሮ ዉድነት እየባሰበት እንጂ ምንም ቀነሰ ተብሎ የሚወራለት እንዳለሆነ ምንጮቻችን ገልጸዋል ይህ በእንዲህ እንዳለ በትራንስፖርትና መገናና ባለስልጣን የሚከናወን ማናቸውም የትራንስፖርት ችግሮችን የመቅረፍ ሁኔታ ባይታይም በከተማይቱ የሚገኙት የግል የትራንስፖርት ድርጅቶች በስራ መግቢያና መውጫ ሰአታት የዋጋ ጭማሪ በማሳየት ህዝቡን ለስቃይ እየዳረጉት እንደሆነ ተገልጾልናል Continue reading “በኢትዮጵያ የኑሮ ውድነት እና የነዳጅ ዋጋ እያየለ መጥቶአል”

የሚሌኒየም ቦንድ ገበያው ደርቷል ወያኔ በአጭር ጊዜ በቦንድ ግዢ ከበርቴ እንደሚሆን ተጠቆመ

በዓባይ ወንዝ ላይ ለሚገነባው የሚሌኒየም ግድብ የሚያስፈልገውን ወጪ ለመሸፈን የተጀመረው የሚሌኒየም ቦንድ ሽያጭ በአገር ውስጥና በውጭ ያሉ ኢትዮጵያውያን ትኩረት እየሳበ ሲሆን፣ ግዢውን ለመፈጸም በርካታ ሰዎች የኢትዮጵያ ልማት ባንክንና የኢትዮጵያ ንግድ ባንኮችን እያጨናነቁ ነው፡፡ ካለፈው ማክሰኞ ጀምሮ ለሽያጭ የቀረበውን የሚሌኒየም ቦንድ ለመግዛት የንግዱ ማኅበረሰብ፣ የመንግሥትና የግል ሠራተኞች፣ ግለሰቦች፣ ማኅበራትና የተለያዩ የኅብረሰቡ ክፍሎች ወደ ባንኮች እየጎረፉ ነው፡፡ Continue reading “የሚሌኒየም ቦንድ ገበያው ደርቷል ወያኔ በአጭር ጊዜ በቦንድ ግዢ ከበርቴ እንደሚሆን ተጠቆመ”

የግብፅ ኩባንያ በቤኒሻንጉል ከፍተኛ የወርቅ ክምችት አገኘ

የግብፁ የማዕድን ኩባንያ አስኮም የሚሌኒየም ግድብ በሚገነባበት ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ውስጥ ባካሄደው የወርቅ ፍለጋ ከፍተኛ የወርቅ ክምችት ማግኘቱ ተረጋገጠ፡፡ የግብፁ ኩባንያ አስኮም ከአንድ ዓመት በላይ ለሆነ ጊዜ በክልሉ 8,000 ስኩዌር ኪሎ ሜትር ቦታ ላይ ወርቅና የከበሩ ማዕድናትን ሲፈልግ ቆይቷል፡፡ Continue reading “የግብፅ ኩባንያ በቤኒሻንጉል ከፍተኛ የወርቅ ክምችት አገኘ”

‹‹በኢትዮጵያ ዓመፅ ቢነሳ ባለቤቱ ሕዝቡ እንጂ ፓርቲዎች አይደሉም››

አንድነት ፓርቲ

– መድረክ ዛሬ በመቀሌ ለጠራው ሕዝባዊ ስብሰባ እንዳይቀሰቅስ መከልከሉን ገለጸ

ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ሰሞኑን ‹‹ሽብርና አመፅን ከሚቀሰቅሱ መካከል›› ያሉዋቸውን የአንድነት የፓርቲ አባላት ማስጠንቀቃቸውን ተከትሎ፣ አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ ባወጣው መግለጫ፣ በኢትዮጵያ ሕዝባዊ አመፅ የሚቀሰቀስ ከሆነ የእንቅስቃሴው ባለቤት ራሱ ሕዝቡ እንጂ ፓርቲዎች አይደሉም አለ፡፡ ከዚህ ይልቅ ኢሕአዴግ የፖለቲካ ፓርቲዎችን ማስፈራራት አቁሞ የሕዝቡን ብሶት እንዲያዳምጥ አሳስቧል፡፡ አጋጣሚውን ተጠቅሞ ተቃዋሚዎችን ለመምታት የተደረገ ሴራ ነው ሲሉም የፓርቲው አመራሮች ይወቅሳሉ፡፡ Continue reading “‹‹በኢትዮጵያ ዓመፅ ቢነሳ ባለቤቱ ሕዝቡ እንጂ ፓርቲዎች አይደሉም››”

Blog at WordPress.com.

Up ↑

%d bloggers like this: