በኢትዮጵያ የኑሮ ውድነት እና የነዳጅ ዋጋ እያየለ መጥቶአል

  • በዘላለም ገብሬ
   በኢትዮጵያ የነዳጅ ዋጋ ከጊዜ ወደ ጊዜ እያሻቀበ እየመጣ መሆኑን ከአካባቢው የተጘኘ መረጃ ያመለክታል  በዛሬ እለት በደረሰን መረጃ መሰረት የአገሪቱ የዋጋ ግሽበት እና የኑሮ ዉድነት እየባሰበት እንጂ ምንም ቀነሰ ተብሎ የሚወራለት እንዳለሆነ ምንጮቻችን ገልጸዋል ይህ በእንዲህ እንዳለ በትራንስፖርትና መገናና ባለስልጣን የሚከናወን ማናቸውም የትራንስፖርት ችግሮችን የመቅረፍ ሁኔታ ባይታይም በከተማይቱ የሚገኙት የግል የትራንስፖርት ድርጅቶች በስራ መግቢያና መውጫ ሰአታት የዋጋ ጭማሪ በማሳየት ህዝቡን ለስቃይ እየዳረጉት እንደሆነ ተገልጾልናል ከዚህ ጋር በተያያዘ ዜና መሰረት በአዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 1 2003 (ኤፍ ቢ ሲ) የንግድ ሚኒስቴር ከነገ ጀምሮ ተግባራዊየሚሆን አዲስ የነዳጅ ችርቻሮ የዋጋ ተመን ይፋ አድርጝዋል።
   ሚኒስቴሩ ለኤፍ ቢ ሲ የዋጋተመኑን መግለጫ ልኳል በዚህም መሰረት ።
   ኢታኖል ድብልቅ ቤንዚን 18 ብር ከ33 የነበረው——- አሁን 20 ብር ከ94
   ነጭ ናፍታ 16 ብር ከ37 ሳንቲም የነበረው ————17 ብር ከ73
   ኬሮሲን 14 ከ05 የነበረው ————-ባለበት 14 ብር ከ05
   ቀላል ጥቁር ናፍታ 14 ብር ከ01 የነበረው ———14 ብር ከ17
   ከባድ ጥቁር ናፍታ 13 ብር ከ75 —————የነበረው 14 ብር
   የአውሮፕላን ነዳጅ ደግሞ 18 ብር ከ12 ሳንቲም የነበረው 21 ከ 74 ሳንቲም ሆኗል
   ይህ የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ከነገ ጀምሮ ስራ ላይ ይውላል።
Advertisements

1 thought on “በኢትዮጵያ የኑሮ ውድነት እና የነዳጅ ዋጋ እያየለ መጥቶአል

 1. egege betame tedesehalehu bemeteserot zian katelubete

Comments are closed.

%d bloggers like this:
search previous next tag category expand menu location phone mail time cart zoom edit close