የኢሕአዴግ ስብሰባና የተቃውሞ ሰልፍ በሚኒያፖሊስ

ZHabesha

ከዚህ በታች የተጠናቀረውን፡የጽሁፍ፡ሪፖርታዥ ያቀረበልንን፡የዘሃበሻ፡ዋና፡አዘጋጅ፡ሄኖክ፡አለማየሁን፡እናመሰግናለን፡

12:30AM

መንገዶች ሁሉ ወደ ዳውንታውን ሚኒያፖሊስ ያመራሉ…. እኔም ወደዛው እየነዳሁ ነው።
“መጽሐፍ ቅዱስ የሚሰበከው ሃገር ሲኖር ነው” ሃይማኖት እና ፖለቲካ የተለያዩ ናቸው ለሚሉት ም ዕመናን ያስተላለፉት መልዕክት
11:30AM
የሚኒሶታው ቅዱስ ዑራኤል ቤተክርስቲያን ቆሞስ አባ ገ/ሚካኤል ሰው ዛሬ ሰልፍ እንዲወጣ ቢጠይቁም እርሳቸው ግን በሰልፉ ላይ እንደማይገኙ አስታውቀዋል። እርሳቸው የማይገኙት የቤተክርስቲያኑ ኮሚቴ ስለከለካላቸው መሆኑም ታውቋል። የኮሚቴውን አባል በስልክ አነጋግሬው “እኛ ወደ ሰልፉ እንሄዳለን። ወደ ሴናተሮች ጋር የምንሄድ ቢሆን ኖሮ አባም ይመጡ ነበር። እኛ የምንሄደው ለመጮህ ስለሆነ ይህ ለአባ አይሆንም” ብለዋል። ይህ በ እንዲህ እንዳለም ከኢቫንጀሊካል ቸርችም የተለያዩ ፓስተሮች እንደሚገኙ ሲበጠቅ ስማቸውን እስካሁን አልደረሰንም።
ይህ ከታች የምታዩትን ፎቶ ግራፍ ዛሬ ሰልፈኞች በቲሸርት ለማሳተም ከላኩት ፎቶዎች መካከል አንዱ ነው። ምናልባትም በርከት ያሉ ሰዎች ይህንን ፎቶ በቲሸርታቸው ለጥፈው ተቃውሞ ይወጣሉ ተብሎ ይጠበቃል።

10:37AM
ሰልፉ ሊጀመር ወደ 3 ሠዓት አካባቢ ይቀረዋል። ሁሉም ሰው የተቀጣጠረው ከ12፡30 እስከ 1 ሰዓት ባለው ነው። አሁን ሴንት ፖል ፎርድ ፓርክ ዌይና ክሊቭላንድ አቬንዩ መገጣጠሚያ ላይ ያለው ስታር ባክስ ቁጭ ብያለሁ። ይህን ቦታ ብዙ ሃበሾች ስለሚያዝወትሩት ወሬ ለመልቀም ጥሩ ቦታ ነው። ከቤተክርቲያን መጥተው ቡና እዚህ ከሚገዙት መካከል ነዋሪነቱ በኢስት ሴንት ፖል የሆነው ጆኒ የተባለው ወጣት አረንጓዴ ቢጫ ቀይ ባንዲራ እንደ ሻሽ አስሯል። “ዛሬ ወዴት ነው”አልኩት? ጥያቄዬ ከይትኛው ወገን ነህ ለማለት እንደገባው በሚያስታውቅ መልኩ “ብቃ”ብዬ ልጮህ ነው” ብሎኝ ስለዛሬው ሰልፍ ስልክ እያወራ ጥሎኝ ሄደ።
9:16AM
መንገድ ላይ ነኝ። ግን አሁን በብዛት የኦሮሚያ ተወላጆች በሚገኙበት የፕሮቴስታንት እምነት ተከታይ ኢትዮጵያውያን ቤ/ክ በኩል ሳልፍ ትዝ ያለኝን ነገር ላጫውታችሁ ነው። ባለፈው ሳምንት እሁድ በዚህ ቤተክርስቲያን በር ላይ ከቆሙት ከ200 በላይ መኪናዎች ላይ በኦሮሚኛ ቋንቋ የተጻፉና “ጋዬ” የሚል ጽሁፍ ወረቀት ታትሞ ለዛሬ ሰልፍ እንዲወጣ ተበትኗል። በተለይ እንደሚኒሶታ ባሉ የብሄር ፖለቲካ በሚንጸባርቅባቸው ስቴቶች ለቅስቀሳ የተጠቀሙበት ዘዴ ለኦጋዴኑ በሶማሊኛ ቋንቋ፤ ለኦሮሚኛው በኦሮሚኛ፤ ለአኝዋኩም በአኝዋክኛ ተጽፎ ተበትኗል። አሁን አሁን የዘር ፖለቲካ እየቀረባት ሕዝቡም ወደ አንድነት እየመጣባት ባለችው ሚኒሶታ ሁሉም በአንድነት ሰልፍ እጅ ለ እጅ ተያይዞ ሰልፍ ይወጣል ተብሏል። በዚህ አካባቢ ከሚኖሩ የኦነግ ከፍተኛ አመራሮች መካከል መረዳት እንደቻልኩት ሁሉም የኦሮሚያ ተወላጅ ከኢትዮጵያዊው ወንድም እና እህቱ ጋር አንድ ላይ በመሆን ዘረኛውን እና አምባገነኑን ስር ዓት እንዲቃወም ጥሪ ማቅረባቸውን ነግረውኛል።
አሁን ወደ ቤተክርስቲያን አካባቢዎች እና ሕዝቡ ወደሚሰባሰባቸው ቦታዎች ደርሼ እመለሳለሁ:: ያኔ የሕዝቡን ስሜት ይበልጥ እጽፋለሁ:: ትንሽ ሰዓት ስጡኝ:: ዘገባው ይቀጥላል…
8:16AM
ከሚኒሶታ አጎራባች ስቴቶች ሳውዝ ዳኮታ; ኖርዝ ዳኮታ, አይዋና ዊስኮንሰን በርከት ያሉ ሰዎች የኢ ሕ አዴግ ሰዎችን ለመቃወም ወደ ሚኒያፖሊስ የገቡት ትናንት ማምሻውን ነበር:: ዛሬም በርከት ያሉ ሰዎች ይጠበቃሉ:: ትናንት በአንድ መኪና ውስጥ 4 ሆነው በመምጣት ካነጋገርኳቸው መካከል “ባለንበት ስቴት የወያኔ ስዎች ባይመጡም 3 እና 4 ሰአት ነድተን መጥተን ስሜታችንን ልንነግራቸውና በቃ ልንላቸው እዚህ መጥተናል” ብለውኛል::
8:13AM
ቀጣዩ ቭዲዮ የሚያሳየው በዋሽንተን ዲሲ ኢሕ አዴግ ያዘጋጀው ስብሰባ ካለ ውጤት ከተበተነ በኋላ የሕዝቡ ስሜት ምን እንደሚመስል ነው:: ይህ የጋለ የሃገር ፍቅርና የአንድነት ስሜት ዛሬም የሚኒሶታ ነዋሪዎች እንደግመዋለን እያሉ ነው:: እስኪ ፊልሙን ይመልከቱት::

7:54AM
በ እንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ ይሏል ይሄ ነው… የመለስ ዜናዊ አስተዳደር ንግድ ሚኒስቴር ከነገ ጀምሮ ተግባራዊየሚሆን አዲስ የነዳጅ ችርቻሮ የዋጋ ተመን ይፋ አደረገ።
ሚኒስቴሩ ለኤፍ ቢ ሲ የዋጋተመኑን መግለጫ ልኳል በዚህም መሰረት ።
ኢታኖል ድብልቅ ቤንዚን 18 ብር ከ33 የነበረው——- አሁን 20 ብር ከ94
ነጭ ናፍታ 16 ብር ከ37 ሳንቲም የነበረው ————17 ብር ከ73
ኬሮሲን 14 ከ05 የነበረው ————-ባለበት 14 ብር ከ05
ቀላል ጥቁር ናፍታ 14 ብር ከ01 የነበረው ———14 ብር ከ17
ከባድ ጥቁር ናፍታ 13 ብር ከ75 —————የነበረው 14 ብር
የአውሮፕላን ነዳጅ ደግሞ 18 ብር ከ12 ሳንቲም የነበረው 21 ከ 74 ሳንቲም ሆኗል
ይህ የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ከነገ ጀምሮ ስራ ላይ ይውላል።
እስኪ የነዳጅ ዋጋ እንዲህ እየጨመረ ባለበት ወቅት መለስ በ14 የአሜሪካና የካናዳ ከተሞች ቱባ ባልስልጣናቱን በስንት ሚሊዮን ብር መድቦ ከሚያሰማራ ለምን በዚህ ገንዘብ ነዳጅ ዋጋውን አይደጉመውም??
7:49AM

ይህን ያውቁ ኖሯል?
እንደሚታወቀው መለስ ዜናዊ እያንዳንዱን ተለጣፊ ድርጅቱን የሰራው በዘር ሃረግ ነው::ላለመከዳዳት:: ሕወሓትን በስብሐት ነጋ ቤተሰብ በጋብቻ አስተሳስሮ ላይካካድ አስሮታል::ብአዴንን ደግሞ በብርሃኔ አበራ ቤተሰብ አስሯል:: በቁጥር የሚቆጠሩ የብ አዴን አባላት የብርሃኔ አበራን ልጆችና ዘመዶች አግብተዋል::እዚህ ሚኒያፖሊስ የሚመጣው ጁነዲን ሳዶ የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነሩ ወርቅነህ ገበየው ዘመድ መሆኑንስ ያውቁ ኖሯል?

“እኔ እንደማንኛውም ዜጋ ኢትዮጵያዊ አዝማሪ ነኝ:: በኢትዮጵያ የሕግ የበላይነት እንዲኖር ነው የምታገለው”
ታማኝ በየነ በትናንቱ የዲሲ ሰልፍ ላይ ከተናገረው

7:34AM
ከታማኝ ምንጮች እንደተረዳሁት አቶ ጁነዲን ትናንት በሴንት ፖል አካባቢ በደረሰችባቸው መጠነኛ ተቃውሞ ድንጋጤ ውስጥ ገብተዋል:: ይህም “ምሳ ልበላ ወጥቼ ይሄ ከሆነ አዳራሹ ፊት ለፊት ምን ይጠብቀኝ ይሆን?” የሚል ይመስላል:: እንደርሳቸው እቅድ ራታቸውንም በሌላ የሃበሻ ሬስቶራንት ውስጥ ለማድረግ የነበረ ቢሆንም ለሴክዩሪቲ በሚል ግን ሳይሆን ቀርቷል:: እንደተለመደው አንዱ ደጋፊ “ቱ ጎ” አሰርቶ ክትፎና ጥብስ ሆቴላቸው ድረስ ወስዶላቸው ይሆን?
አቶ ጁነዲን በዛሬው ስብሰባቸው ብዙ ተቃውሞ እንደሚደርስባቸው ከተረዱ ወዲህ በዘረኞቹ ስርዓት ሰዎች ዘንድ እንደሁለተኛ ዜጋ የምንቆጠር እንደኛ ያልን ሰዎች ተመሳስለን ወደ አዳራሹ እንዳንገባ ከፍተኛ ጥንቃቄ እንዲደረግ አዝዘዋል:: በዋሽንግተን ዲሲ የተደረገው ሚኒያፖሊስም እንዳይደገም በሚል ተጨማሪ እንቅልፍ ያጡት ጁነዲንና የ ኢሕ አዴግ ሰዎች 2 ዓይነት ኢትዮጵያዊ መፍጠራቸው ሃገሪቱን ወዴት ያመራት ይሆን? በሚል በየቦታው መወያያ ሆኗል::
7:10AM
ይህ ከታች የምትመለከቱት በዳውንታውን ሚኒያፖሊስ ሂልተን እነ ጁነዲን ሳዶ የሚሰባሰቡበት ትልቅ አዳራሽ ነው:: አዳራሹ ከ250 እስከ 2500 ሰው ይይዛል:: ይህን አዳራሽ ከምግብ እና ከመጠጥ ውጭ ለመከራየት ራሱ በሰዓት የሚከፈል ሲሆን የምግብና የመጠጥ ሂሳብ ከተጨመረበት በ10 ሺዎች የሚቆጠሩ ዶላሮች ለኪራይ ይከፈልበታል:: ዛሬ ኢትዮጵያ ውስጥ ዘይትና ስኳር በወረፋ እንዲሁም ልክ እንደ ደርግ ጊዜ በራሽን ካርድ (በኮታ) በሚሰጥበት ወቅት; ይህ ሁሉ ሺሕ ዶላር ለዛ ደሃ ሕዝብ ስንት በርሜል ዘይትና ስንት ኩንታል ስኳይ ይገዛለት ይሆን? ብለን እናስብ::

5:00AM
እንግዲህ አሁን ገና ከንጋቱ 5ኤ.ኤም ነው:: የኢሕ አዴግን የሚኒያፖሊስ ስብሰባ ተቃውመው ሰልፍ ከሚወጡት ወገኖች መካከል ቴክስት ሜሴጅ ደረሰኝ:: ይህ ቴክስት ሜሴጅ ከትናንት ወዲያ ጀምሮ 11 ሰዎች ልከውልኛል:: መልክቱ ባጭሩ “በቃ እንበል; ሆዳሞች ሲሰበሰቡ ፎቶግራፋቸውን አንስተህ ታገላቸው:: ይህንን የዘረኛ ስር ዓት በቃ እንበለው:: በ12:30 ዳውንታውን ሚኒያፖሊስ ከሂልተን ሆቴል ፊት ለፊት እንገናኝ” ይላል::

4:55AM
የመለስ ዜናዊ አስተዳደር ወደ አሜሪካ ከላካቸው ባለስልጣኖቹ መካከል ወደ ሚኒሶታ የሚመጣውና ዛሬ ከጠራቸው ሰዎች ጋር ይወያያል ተብሎ የሚጠበቀው ጁነዲን ሳዶ ነው:: ጁነዲን ከትናንት በስቲያ ሚኒያፖሊስ ሴንት-ፖል ኤርፖርት በገባበት ወቅት የተቀጠሩ ናቸው የተባሉ ሶማሊያውያን ተቀብለውታል:: ትናንትም በርከት ባሉ አጃቢዎቹ በመታገዝ ሴንትፖል በሚገኘው ፋሲካ ሬስቶራንት ምሳውን በልቶ ሲወጣ አካባቢው በነበሩ ሰዎች ተቃውሞ ገጥሞታል:በሌላ በኩል የመለስ ዜናዊ አስተዳደር ደጋፊዎቹን ብቻ የጠራበትን ይህንን የሚኒያፖሊስ ስብሰባ በመቃወም የተቃውሞ ሰልፍ ይደረጋል: ከአሁን ሰዓት ጀምሮ zehabesha.com በየሰዓቱ በሚኒሶታ ያለውን ነገር እንደምንዘግብ እንገልጻለን::


5:05AM
የዛሬውን ስብሰባ የሚመሩት ጁነዲን ሳዶን ከ15 በማያንሱ የሶማሊያ ተወላጆች ከ 3 እና ከ 4 በማያንሱ ነጮች በመታጀብ በጥቋቁር ፎር ባይ ፎር ሼቭሮሌት መኪና በመታጀብ ከፋሲካ ሬስቶራንት ሲወጡ አይቻቸው የነበራቸው መደናገጥ በጣም አስገርሞኝ ነበር:: ጠባቂዎቻቸው አቶ ጁነዲንን እያንቀለቀሉ ወደመኪናቸው በመክተት ይዘዋቸው ሲሄዱ ላየ “ተኩላ ያየችን ፍየል” ያስታውሳል:: ይህ ሁሉ ድንጋጤና ፍርሃት ለምን ይሆን? በተለይማ በአካባቢው በነበሩ ሰዎች “ሆዳም ወያኔዎች; በቃችሁ; ስልጣን ገደብ ይኑረው” የሚል ተቃውሞ ሲደርስባቸው ከአጃቢዎቻቸው መካከል አንዱ የሆነው ሶማሌ በተኮላተፈ አማርኛ “እናውቃችኋለን; እዛች ሃገር ትገቧታላችሁ” ሲል ለማስፈራራት ሞክሯል::

5:20AM
ጁነዲን ሳዶ የቀድሞ የኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንት ከኦክቶበር 2001 እስከ ኦክቶበር 2005 የነበሩ ሲሆን በአባዱላ ገመዳ ተተክተዋል:: ከዛም የሳይንስና ቴክኖሎጂ ም/ር ሆነው ሰርተዋል::በአሁኑ ወቅት ደግሞ የሲቭል ሰርቭስ ሚኒስትር ናቸው:: ከኦሮሚያ ተወላጅ የ ኢ ሕ አዴግ ባለስልጣናት ውስጥ አቶ ጁነዲን በሙሰኝነት ከአባዱላ ገመዳ ቀጥለው ሁለተኛ ናቸው ሲባሉ በተለያዩ ጊዜያትም እንደተገመገሙ የውስጥ አዋቂዎች ይናገራሉ::
5:30AM
በሂልተን ሆቴል የሚደረገውን ስብሰባ ለመሳተፍ የሚፈልግ ሁሉ መግባት እንደማይችል ተነገሮናል:: የስርዓቱ ደጋፊዎች “በሃገር ቤት መሬት እንዲሰጥህ ትፈልጋለህ?” በሚል የተንገዳገደ የፖለቲካ አቋም ያላቸውን እና ዘረኛውን ስር ዓት የሚያንቆለጳጵሱ ተነጂዎችን ሃገር ቤት በለመዱት “የጠርናፊና የተጠርናፊ” ማጥመጃ ዘዴያቸው የመግቢያ ካርድ የሚሰጡት:: ትናንት በፋሲካ ሬስቶራንት ውስጥ ከተለጠፈው ፖስተር ላይ “ስብሰባውን ለመካፈል የምትፈልጉ በስልክ ቁጥር ******** ደውሉ” ይላል:: አይነሳም:: ምናልባት ስልኩ የዘ-ሐበሻ ጋዜጣ ስለሆነ ይሆናል ብዬ ከወደአስተባበሪዎቹ መካከል አንዱ ሆነው ደወልኩና “ከዘ-ሐበሻ ጋዜጣ ነበር የምደውለው:: ይህንን ስብሰባ ለመታደምና አንዳንድ ጥያቄዎችንም ለማቅረብ ስለምፈልግ ካርድ ይሰጠኝ” ስል ጠየኩት:: “ስብሰባው እናንተን አይመለከትም; እንደናንተ ያለውን የደርግ ርዝራዥ አንፈልግም” ሲል ጆሮዬ ላይ ዘጋብኝ:: እኛ ለኢትዮጵያ 2ኛ ዜጋ ነን ማለት ነው? – ወዲያውኑ በጭንቅላቴ ውስጥ ያጫረብኝ ጥያቄ ነበር::
5:45AM
በዳውንታውን ሚኒያፖሊስ የኢ ሕ አ ዴ ግ ሰዎችን ስብሰባ በመቃወም ሰልፉን ከሚያስተባበሩት መካከል አንዱ የሆነው አሸብር ጋር በስልክ ተገናኝተን ነበር:: አሸብር እንደነገረኝ ከሆነ ለዛሬው የተቃውሞ ሰልፍ ከ20 በላይ ወቅታዊና የኢትዮጵያን ሕዝብ በደል የሚያሰሙ መፈክሮች ተዘጋጅተዋል:: የተዘጋጁት ከ30 በላይ ካሜራዎችም በር ላይ የሚገቡ የዘረኛውን ስርዓት ስብሰባ ተከታዮችን ፎቶ ግራፍ ያነሳሉ ያለው አሸብር ከምንጊዜውም የበለጠ የተቃውሞ ሰልፈኛ ዳውንታውን እንደሚመጣ ያለውን ዕምነት ገልጾልኛል::
6:15AM
ትናንት በዋሽንግተን ዲሲ የተደረገውን ስብሰባና በውዝግብ ስለመበተኑ ብዙ ተዘግቧል:: ከዚህ ስብሰባ በኋላ ታማኝ ያደረገውን ቃለ ምልልስ ፊልም ይመልከቱ::

Advertisements
%d bloggers like this:
search previous next tag category expand menu location phone mail time cart zoom edit close