የኢሕእዴግ ቅጥረኛ ሰለሞን ተካልኝ የአትላንታ ነዋሪ አዛውንትን ደበደበ

by zelalem Gebre

ይድረስ ለውድ ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያዊያን፤እሁድ April 10፣ 2011 ቀን በአትላንታ ከተማ የኢሕአዳግ የጥፋት መልዕከተኞች የስብሰባ ጥሪ አድርገዋል።የዚህ የስብሰባ አንደ ዓላማ በኢንቨስትመንት ሥም በዉጭ የሚኖረዉን ኢትዮጵያዊ በባድ የቃሊት ጋጋታ፣ ባድ ተስፋና የተሳሳተ የኢኮኖሚ መረጃ በመስጠት ለፍቶ ያጠራቀመዉን ሀብቱን ለመዝረፍ ሲሆን፣ ዋነኛዉ ዓሊማዉ ግን ዓሇምን እያናወጠና የአምባገነኖችን መጨረሻ እያበሰረ ያለዉን የለዉጥ ማዕበል የኢትዮጵያ ሕዝብ እንዲይጀምረዉና ለለዉጥ እንዲይነሳ አትኩሮቱን ለመስረቅ የተደረገ የኢሕአዴግ የተለመደ ተንኮሌ ነዉ፡፡ልማትና ዕድገት፣ ነፃነቱን አጥቶ በታፈነ ሕዝብና ሀገር ሊኖሩ አይችለም።ኢትዮጵያንና ሕዝቦችዋን በዘር፣ በቋንቋ ፣ በጎሳና በሃይማኖት በመከፋፈል የሕዝብን ዴምጽ በመቀማት፣ የተሳሳተ የኢኮኖሚ ፖሉሲ በመከተልና የአገሪቷን ለም መሬት ለባዕዳን በመቸርቸር የአገሪቷን ሀብትና ሥሌጣን በጥቂት ግለሰቦች ሥር ያስገባዉ ይህ አፋኝ ቡድን ስለልማትና ዕዴገት ሊደሰኩርብን ብቃትና ችሎታ የለዉም፡፡በአገራችን የሚያደርጉት አፈናና ድብደባ፣ ግድያና ዝርፊያ አልበቃ ብሎቸዉ፣ ዛሬ ደግሞ ድንበር ተሻግሮ ባሕር አቋርጦ በመጣ ዕብሪታቸዉ በዚህ ሕግና ስርኣት በሰፈነበት፣ ሠብዕዊ መብት በሚከበርበት አገር እንኳን ለፍትህ፣ ለነጻነት፣ ለሃገር በጎ አመለካከት ያላቸዉን የመብት ታጋዮችን በወኪሎቻቸዉ ማስደብደብ ጀምረዋል።ሰሞኑን በአትላንታ የተከሰተዉም ይኸዉ ነዉ።  የኢሕአዴግ ልኡካን April 10 ቀን ለሚያደርጉት ስብሰባ ለመዘጋጀት፣ በApril 4 ቀን 2011 በዲካልብ ኮሚኒቲ ሴንተር ስብሰባ ያቅዳሉ።  በዚሁም ስብሰባ ላይ፣ በአትላንታ የአንዴነት ፓርቲ የድጋፍ አካል አባል የሆኑና፣ በኢትዮጵያ ዱሞክራሲያዊ ሥርዓት እንዲኖር በዚህ ከተማ የረጅም ጊዜ የትግል ታሪክ ያላቸዉ አዛዉንት አቶ ሲሳይ መርሻ፣ በአንድ የኢሕአዴግ ደጋፊ አባል ይጋበዛለ።  አቶ ሲሳይ መርሻ በስብሰባዉ ሊይ በመገኘት ገና ወንበር እንደያዙ፣ ለሆደ ያደረዉ ሰለሞን ተካልኝ ያለምንም ምክንያት ከተቀመጡበት ቦታ በመሄዴና ከኋሊቸው አንገታቸዉን አንቆ በመደብደብ ከፍተኛ ጉዳት ያድርሶባቸዋል።  “ቅንድቡ”በማለት ለመለስ ዜናዊ ራስን በሚያዋርድና በሚያስንቅ መልኩ የዘፈነዉ ይህ ሥርዓት የለሽ ሰው፣ ዛሬ ደግሞ ኢትዮጵያዊ ጨዋነት በጎደለዉ ሁኔታ ሕመምተኛና አቅመ ደካማ አረጋዊ በመደብደብ የኢሕአዴግን እውነተኛ መልክ በሥራው አጋልጦአል።ይህ ሁለ አሳፋሪ ድርጊት የተፈጸመው፣ የኢሕአዴግ ኤምባሲ ተወካይ እና ሌሎችም የኢሕአዳግ ልኡካን በጠሩትና በሚመሩት ስብሰባ ላይ ነው።  የሰለሞን ተካልኝ ድርጊት የኢሕአዳግን ባሕሪይ ቁልጭ አዴርጎ የሚያሳይ ነዉ። እንግዱህ እንደዚህ መረን የለቀቁ ሥርዓት አልበኞችና ዕብሪተኞች ናቸዉ ለልማትና ዕድገት ገንዘባችሁን አምጡ የሚለን። እነዚህ ነፍሰ ገዳዮችና አገር አጥፊዎች ናቸዉ ስለ  ዕድገት ሊሰብኩን የሚቃጡት።  የሰለሞን ተካልኝ አይነት ሕልውና የለሽ ደግሞ የነሱ የጥፋት ወኪልች ናቸዉ።ልማትና ዕዴገት ነፃነቱን አጥቶ በታፈነ ሕዝብና አገር ሊኖር አይችሌም።  “ሥልጣኔን ከማጣ ኢትዮጵያ ትጥፋ” የሚል የጥቂት ግለሰቦች ቡድንም የልማት ወይም የሃገር መሪ የመሆን ብቃት የላቸውም።በአቶ ሰለሞን ተካልኝ ዉክልና ኢሕአዴግ በአቶ ሲሳይ ላይ ያደረሰዉን ጥቃት በሁላችን በኢትዮጵያውያን ላይ አንደደረሰ ነው የምንቆጥረው። እናም እንዱህ አይነቱን ዕብሪት፣ በአትሊንታ የአንዴነት ፓርቲ የድጋፍ አካል በጥብቅ ይቃወማል።  የአትሊንታ የአንዴነት ዴጋፍ አካሌ፣ በኢሕአዴግ ቅጥረኛ በሰለሞን ተካልኝ በኩሌ በሃገር ወዳድና ዱሞክራሲያዊ ታጋይ በሆኑት በአቶ ሲሳይ መርሻ ሊይ የደረሰውን የአካልና የመንፈስ ጥቃት ኢትዮጵያውያን ሁለ የኢሕአዳግ ልኡካን በሚግኙበት ቦታ ሁለ በመገኘት አጥብቀው እንዱያወግዙና በተለይም በልማት ስም ኢትዮጵያውያንን ለማዘናጋት በየከተማው በሚጠሩት ስብሰባ ሊይ ሁለ በመገኘት አጥብቀው እንዲቃወሙ እንጠይቃለን።አምላክ ኢትዮጵያን ይጠብቅ!አንድነት አትሊንታ የድጋፍ አካል።

Advertisements
%d bloggers like this:
search previous next tag category expand menu location phone mail time cart zoom edit close