ኃይሌ በዛሬው ዕለት 38ኛ ዓመት የልደት በዓሉን ያከብራል።

ኬንያዊው ጀፍሪ ሙታይ በ2፡03.02 ገብቷል

በ ሰሎሞን ክፍሌ | ዋሺንግተን ዲ ሲ  18 April, 2011

ለጓደኞች ይላኩ

በለንደኑ ማራቶን በሁለተኛና ሦስተኝነት የሀገሩን ልጆች አስከትሎ የሥፍራውን ጊዜ በማሻሻል ጭምር በአንደኛነት የገባው የ 26  ዓመቱ ኢማኑኤል ሙታኢ 2 ሰዓት 4 ደቂቃ  ከ 400 ሴኮንድ አስመዝግቧል። በዚህ ውድድር ያሸንፋል ተብሎ ቅድሚያ ግምት የተሰጠው ያምናው ሻምፒዮና ኢትዮጵያዊው ፀጋዬ ከበደ በአምስተኝነት ፈጽሟል።

በሴቶቹ በ 2 ሰዓት 19 ደቂቃ ከ  ሴኮንድ ፈጣን ጊዜ ያሸነፈችው ኬንያዊት ሜሪ ኬይታኒ በማራቶን ስትሳተፍ ትላንት የመጀመሪያዋ መሆኑ ተዘግቧል።

በትላንቱ የለንደን ማራቶን ድል ይቀዳጃሉ ተብለው ከተጠበቁ መካከል የኢትዮጵያ አትሌቶች ይገኙበታል። ከምን ገቡ? አሰልጣኝ ገመዱ ደደፎ ባጭሩ ውድድሩን ገምግመዋል።

በሌላ በኩል የዓለም ማራቶን ክብረወሰን ባለቤት አትሌት ኃይሌ ገብረ ሥላሴ ትላንት በቪዬና ግማሽ ማራቶን በድንቅ አሯሯጥና በፈጣን ጊዜ አንድ ሰዓት ከ18  ሴኮንድ አስመዝግቦ ድል ተቀዳጅቷል። ኃይሌ በዛሬው ዕለት 38ኛ ዓመት የልደት በዓሉን ያከብራል።

በዚሁ ዕለት በተካሄደ ሙሉ ማራቶን፥ በሴቶች ፋጤ ቶላ ከኢትዮጵያ በወንዶች ጆን ኪፕሮቲች ከኬንያ አሸንፈዋል

Advertisements
%d bloggers like this:
search previous next tag category expand menu location phone mail time cart zoom edit close