ትእግስት በቀለ ኑሮዋን በሰሜን አሜሪካ ላልተወሰነ ጊዜ እንደምታደርግ ገለጸች

by zelalem Gebre

(ሳቂታው)በሚለው በ1994 አ/ም ባወጣችው የዘፈን አልበሟ የምትታወቀው አርቲስት ትእግስት በቀለ  ኑሮዋን በሰሜን አሜሪካ መካከለኛው ምእራብ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ ማለትም በቺካጎ እና አካባቢው ኑሮዋን መጀመሯን ዛሬ ለዝግጅት ክፍላችን በሰጠችው  የቃለ መጠይቅ ፕሮግራም ላይ ገልጻለች ። ለረጅም ጊዜያት በአረብ አገር እና በጣሊያን አገር ኑሮዋን ስትመራ የነበረችው ተግስት በቀለ ወደ ሰሜን አሜሪካ ከመጣች ብዙ ጊዜ ባይሆናትም ኑሮዋን በቺካጎ ያደረገች ቢሆንም ከተወሰኑ አመታት በሁዋላ ግን ቀድሞ ወደነበረችበት ጣሊያን አገር ለመኖር እንደምትመለስም አክላ ገልጻለች ።የሁለት  ልጆች እናት የሆነችው ትእግስተ በቀለ ወደ ቺካጎ የመጣችበት ዋነኛ ምክንያት የትዳር አጋሯ የጣሊያን አገር ተወላጅ ሲሆን የእሱ የስራ  ቦታ ወደ ቺካጎ በመዛወሩ እና በዩንቨርሲቲ ኦፍ ቺካጎ በማስተማር ላይ ስለሚገኝ እሱን ለማገዝ እና ለመርዳት በሚያስችላት መልኩ ያደረገችው መሆኑን ገልጻ ልጆቿም የአባታቸው ፍቅር እንዳይለያቸው የማድረግ ሃላፊነቱም የእራሳችን በመሆኑነው ስትል ገልጻለች  በአሁን ሰአት በተለያዩ ቦታዎች በመንቀሳቀስ በአሜሪካ ውስጥ ኮንሰርቶችን በማዘጋጀት ላይ የምትገኝ ሲሆን ለመጀመሪያ ጊዜ በቺካጎ የፋሲካ በአልን በደመራ የኢትዮጵያ ምግብ ቤት ከአርቲስት ዘመነ መለሰ ጋር በጋራ በመሆን  ስራዎቿን ታቀርባለች በመቀጠልም ወደ ላስቬጋስ በመጓዝ ስራዎቿን በተጨማሪ ለማቅረብ ዝግጅቷን እንደአጠናቀቀች በቺካጎ ለሚገኘው የአፍሮ አዲስ ተባባሪ ሪፖርተራችን ዘላለም ገብሬ ገልጻለች

Advertisements
%d bloggers like this:
search previous next tag category expand menu location phone mail time cart zoom edit close