በየመን የሚገኙ ስደተኞች ወደ ሃገር ቤት እንዳልተመለሱ ተጠቆመ


በየመን የሚገኙ ስደተኖችን አስመልክቶ የኢትዮጵያ መንግስት ለተከታታይ ሳምንታት በጉልበት በሚያስተዳድራቸው የመገናኛ ብዙሃኖች ላይ በነፍስ አድን ስራ ተሰማርቼ ዜጎቼን ለሃገራቸው አበቃሁ እያለ የፖለቲካ ማሻሻያ ይሆነው ዘንድ በስማቸው ሲነግድ እና ሲጠቀምባቸው የቆየ እንደሆነ ይታወቃል ይህ በእንዲህ እንዳለ ግን በየመን ውስጥ የሚገኙ ስደተኞች ግን ቅሬታቸውን ለማሰማት ወደላይ ወደታች ቀና ደፋ እያሉ ይገኛሉ በስማችን ነገደብን ተጠቀመብን የሚሉት እነዚሁ  ስደተኞች ማንም ሰው ከሰነአም ሆነ ከሌሎች ቦታዎች ስደተኞች አልተወሰዱም የትሰወሰዱት ስደተኞች ከየመን ሳይሆን አቅራቢያ ከሚገኙት ጎረቤት አገሮች ከሚገኙ እስርቤቶች የታጎሩ ኢጥዮጵያኖች ሲሆኑ እነሱንም የማጓጓዣ ክፍያ ተጠይቀው ከፍለው የተጓዙ እንጂ የኢትዮጵያ መንግስት ምንም ፋይዳ ያደረገላቸው ነገር የለም ከዚያ በበለጠ ግን የአለም የስደተኞች ተቋም  ማለትም ዩኤንኤችሲአር unhcr እየተባለ በምህጻረ ቃል የሚታወቀው ድርጅት በከፊል የትራንስፖርት ክፍያ እና ከእስር ቤት የማስለቀቂያ ቦንድ መክፈሉን ከስፍራው የሚገኘው ተባባሪ ሪፖርተራችን ዘግቦአል ይህንን የተጠናቀረውን ዘገባ ሙሉውን ምንም ሳንቀንስ ሳንጨምር እናቀርብላችሗለን  የመን ያለ ኢትዮጵያዊ ሁሉ በኢትዮጵያ መንግስት ውሸት ተናዷል ይለናል  ግሩም ተክለሃይማኖትን ከልብ እናመሰግናለን ::
በግሩም ተ/ሀይማኖት
የምሰራበት ቦታ ብቅ ያለ አንድ ስደተኛ ወዳጄ..”የዛሬውን ዜና አየኸው?” አለኝ::አለማየቴን ነገርኩትና ለጆሮ እስኪስለች የሚደጋገም በመሆኑ ጠብቄ አየሁት::ያሳፍራል…በጣም ያሳፍራል::የመንግስት መዋሽት ለእነሱ አዲስ ሆነ እንጂ እኔ ስለማውቀው አዲስ አልሆነብኝም::
የገልፍ ኦፍ አደንን ባህር ሲያቋርጡ የተበሳቆሉ::በእስር የተጎዱ..የከሱ የጠቋቆሩ..ልብሳቸውን በፌስታል..የያዙ..ወንድሞቻችንን አሳየን::ለውሸትም ለከት አለው::የመን የሚኖር ቢያንስ ሻንጣ መግዣ ያጣል?ያስብላል::የብዙዎችን ስብዕና የነካ ነገር ነው::ከሁለት ሳምንታት በፊት ለወትሮው እንደማደርገው ኢሚግሬሽን እስር ቤት እስረኛ ለመጠየቅ ጎራ ስል በራሱ ሳንቲም ከውጭ የሞባይል ካርድ ገዝቼ እንዳቀብለው የጠየቀኝን ልጅ በዜናው ላይ አየሁት::እህ…!!ነገሩ እንዴት ነው?ራሴን ጠየኩ::በባህር ሲገቡ የተያዙትን እስከዛሬ ሲመለሱ ከሰው የቆጠራቸው የለም ነበር::አሁን ምነው ለፖለቲካ መጠቀሚያ  ተዋሸባቸው?
የመን ነዋሪ ከሆነው ውስጥ አንድም ችግሩን ፈርቶ ወደ ኢትዮጵያ የተመለሰ የለም::አይን ያወጣ ውሸት በመሆኑ ያላዘነ የመን ያለ ሀበሻ የለም::ከ80 ሺህ በላይ ኢትዮጵያዊ የሚያውቀውን እው
ነታ መካድ..4 ሚሊዮን ተውልደ ኢትዮጵያዊ የሚታዘበውን መዋሸት ከአንድ መንግስት የማይጠበቅ ነው:: በጣም የሚያሳዝነው ኢህአዲግ በችግር ተወጥረን እያለ ቤተስቦቻችን እንዲረበሹ በማድረግ ፖለቲካውን ሊያራዘም ፈልጎ ነው የሚሉ በርካታዎች ቅሬታቸውን በተለያየ መንገድ ገልጸዋል::
በስደት ያለንባት የመን <<ይርሀል..>> የሚል መፈክር ባነገቡ ነዋሪዎችዋ ችግር ውስጥ ከገባች የስጋት ወረዳ ከሆነች ሰነበተች::የሀገሪቱን ፕሬዘዳንት አሊአብደላ ሳላህን <<ይወረድ..>> የሚሉ ተቃዋሚዎች ዳይሪ በሚባለው የሀገሪቱ ዩንቨርስቲ በር ላይ ከተቀመጡ ሶስተኛ ወር አስቆጥረዋል::ከሁሉ ነገር የከፋው በሀገሪቷ ላይ በርካታ እስከታንክ ድረስ የታጠቁ የየግል ወታደር  እያላቸው ሼሆች መኖራቸው ነው::እንደ አንዳንድ መገናኛ ብዙሀን ዘገባ እስከ 40 እና 50 ሺህ ሰራዊት ያላቸው ሼሆች መኖራቸው ይነግራል::ስለዚህ ተቃዋሚዎች ጦርነት ሊከፍቱ እንደሚችሉ ቀድሞ ተግምቷል::በዚህም የተነሳ ያደላቸውና ለዜጎቻቸው የሚሳሱ መንግስት ያላቸው  የውጭ ዜጎች ወደ የሀገራቸው ሄደዋል::ሶማሊያዊያኑ መንግስት ስለሌላቸው..አሉ::ኤርትራዊያን እና ኢትዮጵያዊያን አስታዋሽ አጥተው ተቀምጠዋል::
ኢትዮጵያ ኤምባሲ በስደት የመን ካለው ወደ 80 ሺህ የሚጠጋ ኢትዮጵያዊ 200 የማይሞላ ስብስቦ ወደሀገር እናስገባለን::የኢትዮጵያ መንግስት እናንተን ለማዳን ዝግጁ ነው የሚል ቃል ሰጠ::ካደረገው እሰየሁ የሚያሰኝ ነው::ተመዘገቡ እና ዝግጁ ሁኑ አንድ ችግር ሲመጣ….ተባለ::ለመመዝገቢያ ከእያንዳንዱ 2000 ሪያል ተቀበሉ::እኔ ያልገባኝ ወገኑን ለማዳን ከልብ ያሰበ ኤምባሲ ክፍያ እያለ መመዝበሩ ነው::
ሰሞኑን በዚህ አንድ ለእናቱ ኢትዮጵያ ቴሌቭዢን ላይ በተደጋጋሚ ሀሰተኛ ዜና ተደመጠ::<<ባለው የፖለቲካ ችግር ምክንያት ወደው ወደ ሀገራቸው የተመለሱ …>> በማለት በፍጹም ውሸት የሆነና ያልተገናኘ ዜና ተሰማ::ሁሉም ቀሬታውን አሰማ::የኤምባሲው አጫፋሪዎች ሳይቀር አንገት ደፉ::ሀቀኛውና ሁሉን እሱ ብቻ አድራጊ አድርገው የደሰኮሩለት መንግስታቸው ውሸት አንገታቸውን አስደፋ::
እውነታውን ለማጣራት ከተለያየ ቦታ መረጃ አሰባሰብኩ::በመጀመሪያ ዙር የገቡት ከጅቡቲና ሶማሊያ በባህር ወደ የመን ሲገቡ የተያዙ ሚግሬሽን እስር ቤት ውስጥ የከረሙ ሁሌም የየመን መንግስት ከUNHCR እና ከሳዑዲ አረቢያ መንግስት ጋር በመተባበር ወደሀገራቸው የሚመልሳቸው እስረኞች ናቸው::በሁለተኛ ዙርም ሆነ በቀጣዩ ዙር ከሳዑዲ አረቢያ ህጋዊ ያልሆኑ የመን ገብተው ወደ ኢትዮጵያ በመሄድ ሀጋዊ ሆነው ለመመለስ የሚፈልጉ ከሁለት መቶ ዶላር በላይ እያስከፈሉ የወሰዷቸው ናቸው::በሌላ በኩል ሀምራ እና ሀረዝ ካለ የቀይ መስቀል ካምፕ ውስጥ ወደ ኢትዮጵያ መመለስ የሚፈልጉትን ቀይ መስቀል ራሱ 125 ዶላር እየሰጠ እንደመለሳቸው መረጃ አለኝ::
<<..ታዲያ ምንም ያላረገው የኢትዮጵያ መንግስት መዋሸትን ምን  አመጣው?..>>የሚሉ አስተያየት ሰጭዎች ተደምጠዋል::ግን ድሮስ እውነት አውርቶ ያውቃል ወይ ነው ዋና ጥያቄ መሆን ያለበት::
የኢትዮጵያ ህዝብ እንዲያውቅ የምንፈልገው ከየመን ነዋሪ የነበረ ወደ ሀገር ቤት የተመለሰ የለም ዜናው ውሸት መሆኑን ይረዳ::
የተለያዩ ሰዎችን በዚህ ዙሪያ አነጋግሬያለሁ ቃል-ምልልሱን እመለስበታለሁ::የበለጠ መረጃ ለማግኘት የሚፈልግ ካል ከህዝቡ ጋር ለማገናኘት ዝግጁ ነኝ::girum_tekl@yahoo.com
Advertisements
%d bloggers like this:
search previous next tag category expand menu location phone mail time cart zoom edit close