ህወሃት በራሱ እና በአምሳሉ በፈጠራቸው ፓርቲዎች ውስጥ ሙስና በከፍተኛ ደረጃ መስፋፋቱን አመነ

Source: G7   

የዘረኛውና አምባገነኑ አገዛዝ ኢህአዴግ ጥምር ፓርቲዎች ውስጥ የተስንሰራፋው ሙስና ከፍተኛ ደረጃ ላይ መድረሱን ፓርቲው አደረኩት ባለው ጥናት ማረጋገጡንና ለመካከለኛ ደረጃ አባላቱ ገለጸ ማድረጉን የኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቪዥን ኢሳት ዘገበ፡፡

እንደ ኢሳት ዘገባ ሰሞኑን ከየክልሎቹ የተሰባሰቡ የወያኔ ኢህአዴግ ፓርቲና አጋሮቹ የመካከለኛ ደረጃ ኃላፊዎች በአዲስ አበባ የምክክር ስብሰባ ማድረጋቸው በዚሁም ስብሰባቸው ሙስና የፓርቲውን ህልውና የሚፈታተንበት ደረጃ ላይ እንደሚገኝ ተደረገ የተባለው ጥናት ማጋለጡ ታውቁአል::

በኢህአዴግ ጥምር ፓርቲዎች ውስጥ ከፍተኛ የሙስና ምንጭ ሆነዋል ተብለው በጥናቱ የተጠቀሱት ሦስት አበይት ተቋማት እንደሆኑ የዜና ምንጮቹን በመጥቀስ የዘገበው ኢሳት፤ እነኝህ ተቋማት የመሬት አስተዳደር ጉዳይ፣ ገቢዎችና ጉምሩክ እና በአገልግሎት አሰጣጥ ዙሪያ የሚሰሩ የፌዴራል መንግሥታዊ ተቋማትና ክልላዊ ተቋማት ናቸው በሚል በዝርዝር ማስቀመጣቸውን ገልጹአል፡፡

በገቢዎችና ጉምሩክ፣ እንዲሁም በአገልግሎት አሰጣጥ ላይ በሚሰሩ የፌዴራል መንግሥትና ክልላዊ ተቋማት ውስጥ የህወሃትና የብአዴን ሰዎች ቁጥር አንድ እና ቁጥር ሁለት ሙሰኞች መሆናቸውን ጥናቱ እንዳመላከተ የተናገሩት የ ኢሳት ምንጮች፣ የኦህዴድ ሰዎች ደግሞ በፌዴራልና በክልላቸው በመሬት አስተዳደር ጉዳይ ላይ ቁጥር አንድ ሙሰኛ መሆናቸው ተረጋግጧል ማለታቸው ተዘግቦአል፡፡

የወያኔው ኢህአዴግ ጥናቱን ቀደም ብሎ የአከናወነና ሁኔታውን በቅጡ የተረዳ ቢመስልም በሙሥና የአንበሳውን ድርሻ የያዙትን በዋናነት የህወሃት፣ ቀጥሎ የብአዴን ከፍተኛ ባለሥልጣናት ላይ ምንም ዓይነት እርምጃ ሳይወስድ በኦሮሚያ ክልል የሚገኙ የመካከለኛ ደረጃ እና አነስተኛ ባለሥልጣናት ላይ ብቻ የማስተካከል እርምጃ በመውሰድ ከ120 በላይ የኦህዴድ ባለሥልጣናትና ኃላፊዎችን ቀደም ብሎ ማሰሩ ፖለቲካዊ ጨዋታ ነው በማለት መረጃውን ያቀበሉትን የኢህአዴግ አባላት በመጥቀስ ኢሳት ዘግቦአል፡፡

እንደ ዜና ዘገባው ከህወሀት ሰዎች መካከል የዘረኛና አምባገነኑ አገዛዝ ቁንጮ መለስ ዜናዊ ባለቤት የሆነችውና የሙስና እናት በመባል የምትታወቀው አዜብ መስፍን ቁጥር አንድ በሙስና የተዘፈቀች ሰው ስትሆን፣ አዜብ ባሁኑ ሰአት በኢትዮጵያውያን ዘንድ ወ/ሮ ዘርፈሽዋል በሚል ስም መጠራት መጀመሩአ ዜናው አክሎ አመልክቶአል።

አዜብ መስፍን ወይም ወሮ ዘርፈሽዋአል ከጫት ጀምሮ እንጀራ ወደ ውጭ በመላክ ባሉት ስራዎች ላይ ሁሉ ተሰማርታ የምትገኝ ሲሆን፣ በብዙ መቶ ቢሊዮኖች የሚጠጋ ሀብት ያለውን የህወሀት ኩባንያ የሆነውን ኢፈርትንም በበላይነት ታስተዳድራለች። በቅርቡ ኤቢሲ የተባለው የስፔን ጋዜጣ የሙስና እናት አዜብ መስፍን ወደ አርባ ቢሊዮን ከሚጠጋው የዘረኛው አምባገነን ባሏ መለስ ዜናዊ ተቀማጭ ሀብት ውስጥ እንደልቡአ በማውጣት በአውሮፓ እና በአሜሪካ ውድ ልብሶችንና ጌጣጌጦችን እንደሚትገዛ ማጋለጡም አይዘነጋም።

ወ/ሮ ዘርፈሽዋል ወይንም አዜብ መስፍን እኔ ከኢትዮጵያ ህዝብ ገንዘብ አልዘርፍም በማለት በተደጋጋሚ ስታስተባብል ብትቆይም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግን ይህን የዝርፊያ ወንጀል መደበቅ ከማትቺልበት ደረጃ ላይ መድረሱአን አብዛኞች የሚስማሙበት ጉዳይ ሲሆን በቅርቡ የበአዲስ አበባ ዙሪያ የሚገኙ ነዋሪዎች ባቀረቡት ተቃውሞና በኦህዴድ ውስጥ በተፈጠረ የስልጣን ክፍፍል መነሻነት በርካታ ሰዎች በሙስና የተያዙ ቢሆንም በመሬት ሽያጩ ቁልፍ ተዋናይ የሆነችው አዜብ መስፍን መሆኗ መዘገቡ ይታወሳል::

Advertisements
%d bloggers like this:
search previous next tag category expand menu location phone mail time cart zoom edit close