በኢትዮጵያ የዓለም የፕሬስ ነፃነት ቀን ማክሰኞ ይከበራል

በኢትዮጵያ የዓለም የፕሬስ ነፃነት ቀን ማክሰኞ ይከበራል
SUNDAY, 01 MAY 2011 00:00
ሆርን ኦፍ አፍሪካ ፕሬስ ኢንስቲትዮት፣ የኢትዮጵያ ብሔራዊ የጋዜጠኞች ኅብረት የኢትዮጵያ የኢንቫይሮሜንት ጋዜጠኞች ማኅበር ከዩኔስኮና ከመንግሥት ጉዳዮች ኮሙዩኒኬሽን ጽሕፈት ቤት ጋር በመተባበር፣ የፊታችን ማክሰኞ በሒልተን ሆቴል የዓለም የፕሬስ ነፃነት ቀንን ያከብራሉ፡፡ የፕሬስ ነፃነትን አስመልክቶ በሚደረገው በዚሁ ዓውደ ጥናት ላይ የተለያዩ ጽሑፎች የሚቀርቡ ሲሆን፣ በተሳታፊዎችም ውይይት ይደረግባቸዋል፡፡

የዚህ ዓመት የፕሬስ ነፃነት ቀን የሚከበርበት መሪ ቃል “የ21ኛው ክፍለ ዘመን ሚዲያ አዲሱ ገደብ፣ አዲሱ እገዳ” የሚል ሲሆን፣ የተለያዩ የዓለም ዓቀፍና የአገር ውስጥ የሚዲያ ድርጅቶች፣ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶችና ባለድርሻ አካላት ይሳተፋሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚከበረው ይህ ቀን በመሠረታዊ የፕሬስ ነፃነት ዙሪያ በተለይም በሚዲያው ምክንያት ሕይወታቸውን ያጡ ጋዜጠኞችን በማሰብ ይከበራል፡፡

ባለፈው ዓመትም የዓለም የፕሬስ ነፃነት ቀን “የመረጃ ነፃነትና የማወቅ መብት” በሚል መሪ ቃል መከበሩ ይታወሳል፡፡

Advertisements
%d bloggers like this:
search previous next tag category expand menu location phone mail time cart zoom edit close