ሳምቮድ(ሳሚ ካሳ)ለመጀመሪያ ጊዜ ሙዚቃዎቹን በቺካጎ ሜይ21 ሊያቀርብ ነው

በሬጌ ዳንሶል በዎርልድ ሲጅን በዘመናዊ የአማርኛ  አዘፋፈን ስልቱ የሚታወቀው እና እንዲሁም የተለያዩ ዘፋኞችን በማጀብ ከፍተኛ እውቅናን የተቀዳጀው ሳምቮድ (ሳሚ ካሳ ) በዚህ ወር መገባደጃ ላይ በቺካጎ የራሱ የሆኑትን እና የሌሎችንም የሙዚቃ ስራዎች ለማቅረብ በተጋባዥ እንግዳ በመሆን ሙዚቃዎቹን ከዲጄ ፍጹም ካሊፎርኒያ ጋር በመሆን ለቺካጎ ህዝብ  ለማቅረብ መዘጋጀቱን ለዝግጅት ክፍላችን  የደረሰን መረጃ ያመለክታል ይሄው ውጣት ድምጻዊ በሃሊውድ ውስጥ በጫጭር የፊልም ስራዎች ውስጥ በመስራት ላይ የሚገኝ ሲሆን በሙዚቃው ስራም ከሃገሩ ከወጣ ጀምሮ ከቀድሞው በበለጠ እያሻሻለ እና አዳዲስ የሆኑ ስታይል እየተከተለ ስራዎቹን ማቅረቡንም ምንም እንዳልገደው ለዝግጅት ክፍላችን ሳምቮድ ገልጾልናል:: በቅርቡም በተለያዩ የ አውሮፓ ሃገራቶች እና ካናዳ እንዲሁም በመካከለኛው ምስራቅ አግሮች የሚያቀርብ ሲሆን ከቺካጎ በመቀጠል በካናዳ የሚደረገው ልዩ የኮንሰርት ዝግጅት ላይ በዙ ስራዎች ሊጠብቁት እንደሚችሉ ገልጾአል ሳምቮድ በሌላም በኩል ሲገልጽ በመጪው ሳምንት በአዲሱ ሙዚቃው 2012 በትሰኘው ሰራው የቪዲዮ ቪዡዋል ስራውን እንደሚጀምር እና ለየት ያለ የአስራር ስታይል ይዞ አቀራረብ ይዞ እንደሚቀርብ ጠቁሞአል ።በሌላም በኩል በተለያዩ በቺካጎ በሚገኙ ወጣቶት እና የሙዚቃ ወዳጆች ጋር ባደረግነው የስልክ ጥሪ ምላሻቸው በጉጉት እየጠበቁት እንደሆነና ስራዎቹንም በብቃት ሊያቀርብ እንደሚችል ግምታቸውን ገልሰውልናል የሳምቮድን መምጣት ከሚጠብቁት አንዱ ወጣት ዳንኤል አለሙ እንዳለን ከሆነ የሳምቮድ መምጫ ቀን በዚህ ወር ላይ ከመሸረሳው ሳምንት ቀደም ብሎ ቢሆንም እስከአሁን በጉጉት ላይ ነኝ may 21 ቀን መቼ ደርሶ ወደ 2577 ዲቫን ከሚገኘው አዳራሽ ጎራ በዬ ደስታዬን ከሱ ጋር ባሳለፍኩ ብሎናል ።ሳምቮድ  በመጀመሪያው የነጠላ ዜማ ማለትም “ተይ ተይ ” በሚል ርእስ  የዘፈነው ድንቅ ዘፈን በተለይም በወጣቱ ዘንድ አድናቆትን ከማትረፉም በላይ በቪዲዮ ቅንብሩም እጅግ የተዋጣለት ተብሎ ተመስክሮለት እንደነበር የቅርብ ጊዜ ትውስታ ነው ማለት ይቻላል በመቀጠልም ይህ ወጣት አቀንቃኝ ድምጻዊ ምነው ቆንጆ ባልሆንሽ ፣ እንቢ እንቢ ፡”ፊዲጋልቤን” እና አቢሲኒያ   የሚለውን ቀጣዩን ነጠላ ዜማ በሎስ አንጀለስ ካሊፎርኒያ ከተሰራ በሁዋላ ስራዎቹን ለህዝብ ሲያቀርብ ለጆሮ የማይሰለች ረቂቅ ስራ ማቅረቡንም የማንዘነጋው ነው ይህ በእንዲህ እንዳለ ፊዲጋል በሚለው ዘፈኑ ላይ የተለያዩ ታላላቅ የአሜሪካን የሙዚቃ ባለሙያዎች የተሳተፉበት እንደሆነ መረአዎቹ አክለው ገልጸዋል በሌላም በኩል ሳምቮድ አሁን በርቡ የሚለቀው አዲሱ የሙዚቃ ስራው 2012 የተሰኘ ሲሆን ይህም አዲስ የዘፈን ስራ በ2012 አለም ተጠፋለች በሚለው ፊልም ላይ ያተኮረ እንደሆን ምንጮቻችን ገልጸዋል  .።

Advertisements
%d bloggers like this:
search previous next tag category expand menu location phone mail time cart zoom edit close