ሰበር ዜና ፡ የታሰሩት ሁለት ጋዜጠኞች በአሸባሪነት ወንጀል ተጠርጥረው መሆኑ ተገለጸ

የአውራምባ ታይምስ ጋዜጣ ምክትል ዋና አዘጋጅ ውብሸት ታዬና ፤ አዲስ ፕሬስና ፍትህ ጋዜጦች ላይ የፖለቲካ አምደኛ የሆነችው ወይዘሪት ርዕዮት አለሙ የታሰሩት በአሸባሪነት ወንጀል ተጠርጥረው መሆኑን መንግስት አስታወቀ፡፡

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኢብዴፓ) ሊቀ መንበር አቶ ዘሪሁን ገ/እግዚአብሔር ፣ የፓርቲዉ አባል አቶ ደጀኔ ተፈራና እንዲሁም ሌሎች አምስት ግለሰቦች በአሸባሪነት ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የፌደራል ፖሊስ አስታውቋል፡፡

መግለጫውን የሰጡት የመንግስት ኮምዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት ምክትል ኃላፊ አቶ ሽመልስ ከማልና በፌደራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ምክትል ኮሚሽነር ደመላሽ ገ/ሚካኤል ናቸው፡፡

ተጠርጣሪዎቹን አስመራ ላይ ሆኖ ሲረዳቸው የነበረው አቶ ኤሊያስ ክፍሌ መሆኑን በመግለጫው ተገልጿል፡፡ አቶ ኤሊያስ ከግንቦት 7 ተጠርጣሪዎች ብርጋዲየር ጄኔራል ተፈራ ማሞ ጋር ክስ ተመስርቶበት በሌለበት በሞት እንዲቀጣ መወሰኑ ይታወሳል፡፡ ለተጠርጣርሪዎቹ አቶ ኤሊያስ የፋይናንስና የተለያዩ ዕርዳታዎች እንደሚያደርግ ከመግለጫው ለማወቅ ተችሏል፡፡ ሁለት ጋዜጠኞች ባለፈው ሳምንት በማዕከላዊ እስር ቤት መታሰራቸው ይታወሳል፡፡

በታምሩ ጽጌ

Advertisements
%d bloggers like this:
search previous next tag category expand menu location phone mail time cart zoom edit close