ሼክ መሃመድ ሁሴን አላህ ሙዲ ለፌደሬሽኑ የገንዘብ ምህረት አደረጉ ! የፌደሬሽኑ ክስም መነሳቱ አይቀሬ ነው

በዘላለም ገብሬ

ባለፈው አመት ጀምሮ “የደም ገንዘብ” በሚል ስድብ በአከራካሪነት ለረጂም ጊዘያት የቆየው የሼኩ እና የሰሜን አሜሪካው ሽኩቻ ባሳለፈነው ሳምንት ስማቸው እንዳይጠቀስ በገለጹልን የእሳቸው የቀኝ እጅ በሆኑት አካል መሰረት የምህረት ቃል መናገራቸውን ተገልጾአል እንደ ሼኩ አገላለጽ ከሆነ ይህንን ክስ እስከ መጨረሻው ድረስ ማስኬድ ይፈልጉ እንደነበር የጠቆሙ ሲሆን ነገር ግን ፌደሬሽኑ በማይሆን እና መቀየም በማልፈልጋቸው ሰዎች  ሽምግልና መግባቱን ገልጸዋል ነገር ግን እኝህ ቅርበት አላቸው የተባሉትን ሰው እንዳነጋግረናቸው ከሆነ እኔ የፌደሬሽኑ አቋም እና ህልውና ስላሳሰበኝ እንጂ በእውነቱ ፌደሬሽኑ ልኮኝ አይደለም በአሁን ሰአትም ፌደሬሽኑ እዳውን ሊከፍል የሚያስችል ገንዘብ የለውም ብለዋል ይህ በእንዲህ እንዳለ በዚህ የፌደረሽኑ ክስ ላይ መሰረት ያደረገ ነገር ጠይቀናቸው እስካሁን ድረስ ምንም ነገር የሚያውቁት እንደሌል እና ክሱም በአሜሪካ በፍርድቤት ውስጥ በሼኩ ጠብቆች እንደተያዘ ተጠቁሞአል:: ከዚህ በፊት ሼክ መሃመድ ሁሴን አላህ ሙዲ ለፌደሬሽኑ ከ400000 ዶላር በላይ ቺካጎ ለተካሄደው ጨዋታ መለገሳቸው የሚታወቅ ሲሆን ለእያንዳንዳቸው ቡድኖችም ለማጠናከሪያ እንዲሰጣቸው ተብሎ ቢወሰንም በፌደረሽኑ የአመራር አካላት የት እንደደረሰ አለመታወቁ ከዚህ በፊት በሚዲያዎች ተጠቁሞአል ።ለፌደሬሽኑ ትልቅ ባለውለታ የሆኑትን እኝህን አንጋፋ ባለ ሃብት የደም ገንዘብ ነው የሰጡን በማለት የስድብ ውርጂብኝ ያወረዱባቸው የፌደሬሽኑ አካላቶች በክብር እንግድነት ተመርጠው በነበሩት በወ/ሪት ዳኛ ብርቱካን ሚደቅሳ እና በአርቲስት ማህሙድ አህመድ ምርጫ ምክንያት አርቲስቱ ይመረጥ የሚል ድጋፍ ገልጸዋል በማለት ነው እሳቸው የወያኔ ደጋፊ አባል ስለሆኑ ወዳጆቻቸውን በገንዘብ ሊያስመርጡን አይችሉም በሚል መንስኤ ሊሰድቡአቸው እንደቻሉ እና እሳቸውም ብስድቡ ንዴት ገንዘቤን ይመልሱ ብለው ክስ እንደመሰረቱ  ተገልጾአል በሌላም በኩል ፌደሬሽኑ ለ28 አመታት ሲመራው የቆየው ይህንን የስፖርት ማእከል እስከዛሬ ድረስ በሰው ድጋፍ መጓዙ እና ሁልጊዜም ከልመና አለመውጣቱ በፌደሬሽንኑ ውስጥ ያለውን ሌብነት እና ሙስናን የሚያሳውቅ መሆኑን አንዳንድ ያነጋገርናቸው ሰዎች ገልጸዋል ካነጋገርናቸው አንዱ የአትላንታ ነዋሪ የሆኑት አቶ ዳንኤል ሲገልጹ በአሁን ሰአት ፈደሬሽኑ እራሱን ችሎ ተጫዋቾችን ከእየ ስቴታቸው ማምጣት ሲገባው ተጨዋቾቹ በራሳቸው ገንዘብ ተጉዘው ህብረተባቸውን ማዝናናት እንደቻሉ ገልጸው 28 አመታት ቀልድ አይደልም በእነዚህ አመታት ውስጥ ፌደሬሽኑ እራሱን ይዞ መንቀሳቀስ ይገባው ነበር ሲሉ ትችታቸውን የሰነዘሩ ሲሆን በአሁን ሰአትም ያሉትን አመራሮች መቆየትም ሆነ ማየት አይገባንም በማለት የመጭውን ጊዜ ጨዋታ በአዳዲስ አመራሮች ተትክቶ ማየት የእኛም ተስፋ ነው ብለዋል ስለዚህ ደግሞ የስፖርት አካላቶች ተጨዋቾች እና እንዲሁም በሰሜን አሜሪካ የሚኖሩ ህብረተሰቦች ድጋፋቸውን አሰባስበው እነዚህን ሰዎች ማውረድ ይገባል የፌደሬሽኑን እድገት ከስር ያለውን ገንዘብ እየበዘበዙ አቀጭጨውታል ሲሉ አቶ ዳንኤል ጠቁመዋል ።

Advertisements
%d bloggers like this:
search previous next tag category expand menu location phone mail time cart zoom edit close