“ኢህአዲግን የማጋለጥ ዘመቻችን ተጠናክሮ ይቀጥላል”ሲፔጄ (CPJ)በታምሩ ገዳ

ኢህአዴግ መራሹ አገዛዛ በነጻ ፕሬስ ላይ ያለውን ኤ-ዲሞራሳዊ አቋም እስካላቆመ ደረሰ፣ አገዛዙ አደረጋቸውያሉትን ኢ-ሰብአዊ ድርጊቶችን በማስረጃ በማስደገፍ ለአገዛዙ ድጎማ ለሚያደርጉ እና አፍቃሪ ኢህአዴግ ለሆኑ ለጋሽ አገሮች ከግብር ከፋዩ ህዝባቸው ጉሮሮ እየነጠቁ ለአገዛዙ የሚያደርጉትን የእርዳታ እጃቸውን እንዲስበሰቡ መጠነ ሰፊ ዘመቻውን አንደሚቀጥል ሲፔጄ ገለጸ፡፡

ተቀማጭነቱ በአሜሪካ አገር በኒዮርክ ከተማ ያደረገው እና ለጋዜጠኞች መብት የሚታገለው ኮሜቲ ቱ ፕሮቴክት ኦፍ ጆርናሊስትስ (Committee to Protect Journalists ) የተባለው ደርጅት ከፍተኛ ተማረማሪ የሆኑት ሚሲስ ኤልዛቤጥ ዊቼል በኢትዮጵያ አጠቃላይ የነጻ ፕሬስ ሁኔታ ዙሪያ በአሜሪካን አገር በላስቬጋስ ከተማ ዘወትር እሁድ ከሚሰራጨው ህብር ራዲዮ ጋር ሰሞኑን ባደረጉት ቃለምልልስ ” በኢትዮጵያ ውስጥ ያለው የጸረ- ነጻ ፕሬስ ዘመቻ አለም በአምባገነንታቸው ከሚያውቃቸው ከእነ ዙምባብዌ እጅግ የከፋ ነው ፡፡ ምንም እንኳን ዙምባብዌ ፍጹም ዲሞክራሲ አገር ሆናለች ባይባልም ባለፉት አምስት አመታት ያደረግነው ጥናትን ስንመለክት በዙምባብዊ መጠነኛ መሻሻል ታይቷል ፡፡ በተቃራኒው ግን በኢትዮጵያ የነጻ ፕሬሱን የማሳደድ እና የማዋከብ ዘመቻው ይበልጥ ተባብሶ ነው ያገኘነው” በማለት የሁኔታውን አሳሳቤነት በማነጻጸር ገልጸዋል፡፡
ሲፔጄ ከአንድ ወር በፊት ባወጣው በአለም ላይ በስደት የሚገኙ ጋዜጠኞች አመታዊ ዘገባን በዋንኛ አጥኝነት ያጠናቀሩት ሚሲስ ኤልዛቤጥ ደርጅቱ \ሲፔጄ\ በቀጣይነት በኢትዮጵያ ነጻ ፕሬስ ይዞታ በተመለከተ ምን እቅድ እንዳለው ለቀረበላቸው ጥያቄ ሲመልሱ ” የኢህዲግ መንግስት የዜጎች የዴሞክራሲ መብቶች በሆኑት ሃሳብን በነጻ መግለጽ፣ በነጻ የመደራጀት ፣ የመቃወም ፣የመሰለፍ .ወዘተ መበቶች ላይ ሲያደረጋቸው ለቆዩት ወይም በማድረግ ላይ ያለው አፈራሽ ተገባራትን በማስረጃዎች የተደገፉ በመሆናቸው አርዳታን ከሰበአዊ መብት አያያዝ ጋር ከሚያያዙት ምአራባዊያን ለጋሽ አገሮች ሁኔታውን በማቅረብ በአገዛዙ ላይ ብርቱ ጫና እንዲፈጥሩ ሲፔጄ ጥረት ያደርጋል” በለዋል ፡፡

የአዲስ አባባ መንግስት በአሁኑ ወቅት ” ሃሳባቸውን በመግለጻቸው የታሰሩ ጋዜጠኞች የሉም፣የታሰሩ ካሉ ከአሸባሬነት እና ከድረቅ ወንጀል ጋር በተያያዘ ጉዳይ ተጠረጥረው ነው…ወዘተ ” በማለት ሰሞኑን የሚያሰራጫቸው ተከታታይ መግለጫዎችን ስፒጄ እንዴት አንደሜመለካትቸው ለቀረበላቸው ጥያቄ ሚሲስ ኤልሳቤጠ ሲመልሱ “የኢህአዲግ መንግስት የተለያዮ ምክንያቶችን በማቅረብ ጋዜጠኞችን በቀጥታ ይሁን በእጅ አዙር አንደሜያዋክብ እና እንደሜያስር በደንብ እናውቃለን ፡፡ከዚህ አኳያ ገዤው ፓርቲ የሜያናፍሳቸውን ማሰተባበያዋችን ሲፔጄ በጭራሽ እይቀበልም “ብለዋል፡፡

በአለፈው አስር አመታት ውስጥ ከሙያቸው ጋር በተያያዘ ከደረሰባቸው ዛቻ፣እስርት እና ግርፋት በማመለጥ የሚወዱት ሙያቸውን እና ቤተሰባቸውን ጥለው ለስደት የተዳረጉ 649 ጋዜጠኞች በአለም ላይ መመዝገባቸውን በማውሳት ከእነዚህ መካካል ኢትዮጵያ ከ80 በላይ ጋዜጠኞችን ለሰደት በመዳረግ የሃሳብን በነጻ የመግለጽ ጭቆና ከተንሰራፋባቸው አገሮች በቀዳሜነት ደረጃ ተጠቅሳለች፡፡

ሲፔጄ በቅርቡ ለሁለት የኢትዮጵያ ነጻ ፕሬስ አባላት (በአሁኑ ወቅት አንዳይሰራጩ የታገዱት የታዋቂዎቹ የምኒልክ፣ሳተናው እና አሰኳል ጋዜጦች አሳታሜ እና ልጇን በእሰር ቤት ውስጥ እንድትገላገል ለተደረገችው ጋዜጠኛ ሰርካለም ፋሲል እና የጋዜጠኛ ሰራውን በአስቸጋሪ ሁኔታ ለሚሰራው የአውራምባ ታይምስ ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ እና አሳታሜ ዳዊት ከበደ ) መሸለማቸው ለኢትዮጵያ የነጻ ፕሬስ አባላት ሆነ በተቀረው አለም ለሚገኙ ጋዚጠኞች የሚያሰተላልፈው መልእክት ምን አንደሆነ ለቀርበላቸው ጥያቄ ” ጨቋኝ መንግስት እና ጨቋኝ የፕሬስ አዋጅ ባለበት እንደ ኢትዮጵያ በመሳሰሉ አገሮች ውስጥ ሙያዊ ግዴታቸውን ሲወጡ ድርጅታቸው በመንግስት የጸጥታ ሃይሎች ለተዘጉባችው ወይም በአስቸጋሪ የጋዜጠኝነት ህይወት ውስጥ ለሚገኙ ጋዜጠኞች የሞራል ማበረታቻ ይሆን ዘንድ ታስቦ የተሰጠ ሽልማት ነው ፣ወደፊትም ቢሆን ተመሳሳይ እገዛችን ይቀጥላላ ” በማለት ለኢትዮጵያ የነጻ ፕሬስ አባላት በተለይ ለሁለቱ ጋዜጠኞች ያላቸውን ልዩ አድናቆት ገለጸዋል፡፡ ባለፈው አመት በአለም ላይ 67 ጋዜጠኞች አገራቸውን ጥለው የተሰደዱ ሲሆን የኢሃዴግም መንግስት 5 ጋዜጠኞችን በማሳደድ ከጨቋኞቹ ኢራን፣ ኩባ እና ኤርትራ መንግስታት በመቀጠል በአራተኛ ደረጃ ላይ አንደሜገኝ የሲፔጄ አመታዊ ዘገባ ጠቁሟል፡፡

Advertisements
%d bloggers like this:
search previous next tag category expand menu location phone mail time cart zoom edit close