ገዥዎቻችንና የሀገራችን ርሃብ

(ከአንተሁነኝ ይኸነው)Antehunegn Yehenew

ሃምሌ 2011

በቅርብ ርቀት ታሪክ የሚያስታውሳቸው ጥቂት ተከታታይ የኢትዮጵያ መንግስታት የህዝብን ፍሊጎትና ምኞት አክብረው፣ የሀገርን ዳር ድንበር  አስከብረው ወይም ታሪካችንን ተቀብለውና ጠብቀው ለተተኪው  ትውልዴ ለማስተላለፍ  ብቃት ያላቸው መሪዎች ሳይሆኑ ሀገራችን፤ በስሟ እየማሉና እየተገዘቱ የሚበጣጥሷትና የሚያዋርዷት፣ ታሪክን እየበረዙና እየጎማመዱ የወጣቶች ወጣት የሚያደርጓት፣ ከሀገርና ህዝብ ልእልና ይልቅ  የራስን ክብር፣ የዘመድ አዝማድን ደህንነት  ወይም የአላማንና የዓላማ ተጋሪን ማንነት በሚያሞግሱና በዚህም በሚኮፈሱ ጨካኝ አገዛዞች ስትተዳደር ቆይታለች። በተለይ ባለፉት 20 የግፍና የመከራ ዓመታት የመለስ ዜናዊ ዘረኛ አገዛዝ በማንነት ላይ መሰረቱን በመጣሉና ህዝባችንን በዚሁ መንገድ በመከፋፈል ወንድም ከወንድሙ ወገንም ከወገኑ ጋር እንዲይተማመንና እርስ በርስ እንዳይቀራረብ በማድረግ ህዝባችንን ይህ ነው በማይባል ግፍና በደል ዘፍቆት ይገኛል።

ዘረኛ አገዛዙ፣ የዳሞክራሲ እጦቱ፣ የፈለጉትን  መናገርና መጻፍ አለመቻልና  ይህን የመሳሰሉት እድሎችን ማሳጣቱ ሳያንሰው መለስ ዜናዊና ዘረኛው አገዛዙ በሚከተለት የተፋለሰ የኢኮኖሚ ፖሊሲ ምክንያት ህዝባችን ታይቶ በማይታወቅ ርሀብ እየተጠበሰ ይገኛል። “ጥፋቱን ወታደር አጥፍቶ ቢሆንም ግን ገበሬ ይካስ” አይነት ነገር፤ መለስ ዜናዊና የወያኔ ዘረኛ አገዛዝ ሆን ብሎ ለፈጠረው ችግር ህዝባችን እዳ ከፋይ ሆኗል።

በግርድፍ ስሌት ሲታይ፤ ላለፉት አንድ መቶ ዓመታት ሀገራችን ስሙ የሚጠቀስ በእውነት ስለ እውነት ለህዝብ የቆመ መሪ አላየችም። ግን ለምን?  እርግማን ይሆን እንዴ? በንጽጽር ስንመዝን ሀገራችን ካሳለፈቻቸውና ወያኔን ጨምሮ በቅርበት ከምናውቃቸው ሶስት መንግስታት ለሀገርና ለህዝብ በመቆርቆር፣ ሀገራዊ አንዴነትን በመፍጠር ወይም ለማጠናከር በመሞከርና በዘመናቱ ለተከሰቱት የርሃብ አደጋ የመሳሰሉትን ጠንካራ ችግሮች በአግባቡ ለመፍታት በመሞከር ሂደት መንግስታቱ ሀገራችንን ካስተዳደሩበት ዘመን፣ ከሚከተሉት ርዮተ ዓለም፣ ስለችግሩ ለማወቅ ካላቸው ፍላጎት አቅምና የቴክኖሎጂ መረጃ አንፃር ሲፈተሹ ያሁኑ ከቀዲሚዎቹ እጅግ የከፋው ለመሆኑ ማስረጃ ፍለጋ እሩቅ መሄዴ አያስፈልግም። ኤርትራ እንዴት እንደተገነጠለችና እንዴት ወደብ አልባ እንደሆንን፣ በሰበብ አስባቡ ለሱዳን የተሰጠው ሰፊ መሬታችንንና፣ ደሃው አርሶ አደር ህዝባችን  እየተፈናቀለ ለህንድና  አረብ ነጋዴዎች ባለመሬቱ አርሶ አደር በዓመት ከሚከፍለው የመሬት ግብር ባነሰ ዋጋ ለ90 እና ከዚያም ለሚበልጥ አመት እየተሸጠ ያለውን ለም መሬታችንን  ማስታወስ ብቻ በቂ ነውና። ለፈጠሩ የሚችሉ ችግሮችን ቀድሞ በመገመት ቴክኖልጂም ቢሆን የመለስ ዜናዊ ዘረኛ መንግስት ከቀዳሚዎቹ የተሻለ ነበር። ለበጎ አላዋለውም እንጂ።

ሀገራችን ኢትዮጵያ እንዲህ እንዳሁኑ በተከታታይም ባይሆን አለፍ ቀደም እያሉ በሚከሰቱ የድርቅም ሆነ የርሃብ አደጋዎች ስትጠቃ መቆየቷ አሌ የሚባል አይደለም። በመጥፎነቱ ታሪክ ከሚዘክረውና “ክፉ ቀን” እየተባለ ከሚጠራው የርሃብ ችግራችን ባንነሳ እንኳ በጊዜው የነበሩት  የሀገራችን  መሪዎች በተፈጠረው ችግር ምክንያት በከፍተኛ ደረጃ የተደራጁበትንና  የተዘጋጁበትን የዘመቻ እቅዴ ሁኔታው እስኪቃለሉ በሚል  ሰርዘው የህዝባቸውን ህመም አብረው እንደታመሙ  ታሪክ ይነግረናል። ሆኖም ከዚያ ወዲህ ያሉት የንጉሱና  የደርግና  መንግስታት  ለተፈጠሩት  ተመሳሳይ  ችግሮች  ይዘውት  የነበረው  አቋምና  አሁንም  ወያኔ  እያራመደው  ያለው በተቃራኒው ነው።

የወሎን ህዝብ ከልሂቅ እስከ ደቂቅ ሲፈጀው በነበረው የ1966ቱ የርሃብ አደጋ ወቅት የንጉሱ አገዛዝ ከህዝብ ፍላጎት በተቃራኒ በመሆን ችግረኛው ወቅታዊ እገዛ እንዲያገኝ የተፈጠረውን የርሃብ ችግር ከመደበቃቸውም በላይ ክብርና ሞገስን አግኝቼ እኖርበታለሁ፣ ሃብት ንብረት አፍርቼ ልጆቼን እድርበታለሁ እኩልበታለሁ ከሚለው ከተስፋው መሬት ተፈናቅል እርዳታ ፍለጋ በተቀረው የሀገሪቱ ክፍለ ስደት የገባውን የወል ችግረኛ  ህዝብ ወደ አዲስ አበባ እንዲይገባ እና አንዳንዴ የውጭ ሰዎች እንዲያዩት በማለት ከኮተቤ ማዶ ወዲህ ዝር እንዲይሌ ለማድረግ መሞከራቸውን ታሪክ ያሳየናል። የብርቅየ ውሻቸው የአመጋገብ ስርአትና የጤንነት ሁኔታ እጅግ ያሳስባቸው ነበር የሚባሉት ንጉሱ፤ በጊዜው በየዓመቱ ለሚከበረው የትውልድ ቀናቸው ክብረበአል አብዝተው የስቡ በጣምም ይጨነቁ ነበር እንጂ የወሎ ህዝባችን ችግር ሊፍታ እንኳ እንዳልታያቸው ታሪክ በትዝብት የስታውሰናል።

ይህን የንጉሱን ስህተት እያወገዘና የወልን ርሃብ እንደ ህዝብ ማነሳሻ ቤንዚንነት እየተጠቀመ የመጣው ደርግም “እኔም እንዳባቴ” በሚሌ መልኩ ከወገናችንና ከህዝባችን ፍላጎት ውጭ ፍጹም ፋሽስታዊ በሆነ መንገድ ሀገራችንን

ለ17 አመታት በዝብዟታል ህዝባችንንም ረግጦ ገዝቷል ። ሀገራችን ኢትዮጵያን ከኑሮ ውዴነትና ስደት በተጨማሪ ለ1977ቱ ድብቅ ርሃብ ዳርጓታል። የወቅቱን ርሃብ ታዋቂው ጋዜጠኛ መሀመድ አሚን እስኪያጋልጠው ድረስም ደርግ ምንም ነገር እንዳልተከሰተና ሀገራችን በተረጋጋና በጥሩ ሁኔታ ሊይ እንዳለች ይሰብክ ነበር። እልፍ አእላፍ ዜጎቻችን በሚረግፉበት በዚያ ወቅት የደርግ ጭንቀት የነበረው የ10ኛው የአብዮት በአልና ተያያዥ የሆኑ ለበአል አስፈሊጊ የሆኑ ማስዋቢያ የመንገድ  ላይ መብራቶችና መጠጦች እንዲሁም በወቅቱ ተገንብቶ የተጠናቀቀው ኢፌዲሪ ህንፃ (ጆንትራ ህንጻ) ምረቃ እንጂ  የፈጣሪ ውሃ አጥቶ በየሰከንዱ ፍግም ይል የነበረው ህዝባችን ርሃብና ችግር አልነበረም።

ከሁለቱም አገዛዞች እጅግ የከፋው የመለስ ዜናዊ ዘረኛ አገዛዝ ደግሞ ከዓመታት በፊት ጉዳዩ ከሚመለከታቸው ተቋማት  የተሰጠውን ማስጠንቀቂያ  ከምንም ባለመቁጠርና  ልማታዊ መንግስት ነኝ አቅምም አለኝ  ሁሉም ነገር ከቁጥጥር አልወጣም በሚል መልኩ እስከቅርብ  ጊዜ ድረስ ርሃቡን ደብቆ በመያዙና እርዳታ ሰጭ ድርጅቶችን፣ የሀገር ውስጥም ሆነ አለምአቀፍ ጋዜጠኞችን   ጨምሮ ማንኛውም የረድኤት ሰጭ ተቋም ከዓመታት በፊት ከአካባቢው በማባረሩና እስካሁንም ድረስ ወደተጎዳው አካባቢ እንዲይገቡ ባቋሙ እንደፀና በመሆኑ እንሆ ሀገራችን በ60 ዓመት ታሪክ ውስጥ ታይቶና ተሰምቶ በማይታወቅ እልቂት ላይ ትገኛለች።

ህዝባችን አፈር ለብሶ አፈር መስሎ ላሉት ጉልበቶቹን በሁለት እጆቹ ታቅፎና በተስፋ ማጣት ጭንቅላቱን ጉልበቶቹ ላይ እንዲሳረፈ እየረገፈ ነው። ህፃናት ጉድ ሊያሰኝ በሚችል አኳሗን በካሜራ እይታ ስር እያሉ እስትንፋሳቸው ፀጥ ስትል ዓልም ባይኖቹ አስተውሏል። ለእርዳታ ሁለት አጆቻቸውን የዘረጉና ላንዲት ጠብታ ውሃ አፋቸውን የከፈቱ አስከሬኖች በየቦታው እየተለቀሙ እንደሆነ ይነገራል። ህዝባችን መኖርን ተመኝቶ ሞትን፤ የእርዳታ እጆችንና ትንፋሽ ማቆያ ጣቢዎችን አስቦ ከቤቱ ወጥቶ በየበረሃው ያለቀባሪ እየቀረ ነው።

ዘረኛው መለስ  ዜናዊ ለ1977ቱ  ርሃብ በተደጋጋሚ ደርግን  ሲያወግዝ እንዳልነበረና በወቅቱ ለተከበረው 10ኛው አብዮት በአል ስለወጣው ወጭና ስለኢፌዲሪ ህንጻ ግንባታም ዴሃውንና ርሃብተኛውን ህዝባችን አለማሰብ ነው ሲል የነበረው መሇስ ዜናዊ አሁን በሱ ተራ በ60 ዓመት ውስጥ ታይቶ የማያውቅ ርሃብ ህዝባችንን እያንገላታው መለስ ግን ያለሰው የሚበር የጦር አውሮፕሊን ይሸምታል፣

100 ሚሉዮን ዶሊር አውጥቶ የጦር ታንክ ይገዛል፣ 8.4 ቢሉዮን ዶሊር በላይ ከሀገር ያሸሻል። ህዝባችን የሚላስ የሚቀመስ አጥቶ በጠኔ እየተላወሰ ዘረኛው መለስ ዜናዊ የነዳጅ ዋጋ ይጨምራል፣ በዋጋ ውድነትም ይጠብሰዋል። የዓለም አይኖች ወደ ምስራቅ አፍሪካው ርሃብ በሆኑበት በአሁኑ ወቅት  “ታሪያለሽ ትተክኛለሽ ምን ታረጊኛለሽ” በሚሌ ይመስላሌ የኛው ዘረኛ መለስ እያንዳንዱ ዜጋ “ተማሪ እንኳ ሳይቀር” ለአባይ ግድብ ማሰሪያ ቦንድ እንዲገዛ እስገደደው ይገኛል፣ ከዚህም በተጨማሪ ሀገራችን እያስከፈለች ያለው የነፍስ ወከፍም ሆነ የንግድ ስራ ግብር ከአካባቢው ሀገሮች ጋር ሲወዳደር አነስተኛ መሆኑን ምክንያት በማድረግ ከፍተኛ ግብር በሰራተኛው ህዝባችን ላይ በመጣል እያማረረው ይገኛል። ካነስ አነስ በቦብ ጊሌድፍ አስተባባሪነት የተሰባሰባውንና በሗላም ራሱ የዘረፈውን የእርዳት ገንዘብ ለማግኘት የተናገራትን ንግግር እንኳ (“ነፃ አውጠዋለሁ ብየ እየታገሌኩለት ያለው ህዝብ በርሃብ እየረገፈ ነው”) ችግሩን አምኖ ለመናገር አልደፈረም። ይህ ነው እንግዲህ ህዝብን እየመራን ነው ለእድገት ቆርጠን ተነስተናልና የመሳሰለትን ማስመሰያዎች በማውራት ሊይ የሚገኘው መሪ ተብየ ቡድን።

“ውሾቹ እየጮሁ ነው ግመሉም ጉዞውን ቀጥሏል” እኛም ከእንቅሌፋችን በቅጡ አልነቃንም፣ አይናችን ተገልጦ እያየ ስለመሆኑም ያደረግነውና  እያደረግነው  ያለው  ነገር አያረጋግጥም። የሚገባንን ሳይሆን የምንችለውን እንኳ መፈፀም ተስኖን ሰንካላ ምክንያቶችን በመደርደር “የናቴ መቀነት…” እያሌን እንገኛለን። የፈፀምነውም ሆነ እየፈፀምነው ያለው ነገር ከወያኔ እኩይ ተግባር አንፃር “ከውሾቹ ጩኸት” በታች ነው። እሰከ  መቼስ ይህን   መታገስ ይቻላል?  ይህ ሁላ  ከሽክምስ በሊይ አይደለምን? በእርግጥ የኢትዮጵያ ህዝብ የሁላችንንም የተባበረ እገዛ እያለመ መሆኑን ሌብ ብለናል? አጆቹን ወደ ላይ ዘርግቶ እየጠበቀን ነው! በምንችለው ሁላ በመረባረብ አሁኑኑ  እንድረስልት። በወቅቱ የተገኘች ጠብታ ውሃ ከእርካታ በላይ  መሆኗን እናስብ ነገም ሌላ ቀን መሆኑን እንዱሁ። ቸር እንሰንብት።

Advertisements
%d bloggers like this:
search previous next tag category expand menu location phone mail time cart zoom edit close