ብርቱካን ሚደቅሳ በድጋሚ ነፃ የትምህርት ዕድል ተሰጣቸው

ናሽናል ኢንዶውመንት ፎር ዲሞክራሲ የተባለው ተቋም ሰሞኑን ለወይዘሪት ብርቱካን ሚደቅሳ ነፃ የትምህርት ዕድል መስጠቱን አስታወቀ፡፡

ለቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ሮናልድ ሬገንና ለአንጋፋው የአሜሪካ ኮንግረስ አባል ዳንቴ ፋሲል መታሰቢያነት የተቋቋመው ይኸው የትምህርት ፕሮግራም፣ በአመራር ታዋቂ የሆኑ ግለሰቦችን አወዳድሮ በዲሞክራሲ ላይ ጥናት እንዲያደርጉ ነፃ የትምህርት ዕድል የሚሰጥ ነው፡፡

ታዲያስ መጽሔት አዲስ ቮይስን ዋቢ በማድረግ እንደዘገበው፣ ለሁለት ዓመታት ያህል በእስር ላይ በነበሩት ወይዘሪት ብርቱካን ይህ ዕድል የተሰጣቸው፣ በኢትዮጵያ ውስጥ ባሳዩት ቆራጥ አመራር ነው፡፡ ወይዘሪት ብርቱካን ያገኙትን ይህን ልዩ የትምህርት ዕድል አስመልክተው፣ ‹‹ለዲሞክራሲና ለነፃነት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያበረከቱ የዓለም መሪዎችን ስቀላቀል እጅግ ከፍ ያለ ደስታ ይሰማኛል፤›› ብለዋል፡፡

ተቋሙ የዕድሉ ተጠቃሚዎችን አጠቃላይ የኑሮ ወጪና የጤና መድኅን ሙሉ በሙሉ የሚሸፍን ሲሆን፣ ሥልጠናው የሚጠናቀቀው በአምስት ወር ውስጥ ነው፡፡ የዚህ ዕድል ተጠቃሚዎች፣ በአሜሪካ የሚካሄዱ ከፍተኛ ስፍራ የሚሰጣቸውን ኮንፈረንሶችና ስብሰባዎች የመሳተፍ ዕድል ሲኖራቸው ከአሜሪካ መንግሥት ባለሥልጣናትም በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ይመክራሉ፡፡

Advertisements
%d bloggers like this:
search previous next tag category expand menu location phone mail time cart zoom edit close