ወጣቱ ኢትዮጵያዊ የስምንት አመት ፍቅረኛውን ሁለት አይኖች በጩቤ ዘንቁሎ አወጣቸው

ሁለት አይኖቿን ያጣችው ወጣቷ ኢትዮጵያዊት  by zelalem gebre

በዘላለም ገብሬ

በአሜሪካ ለተወሰኑ ጊዜያቶች ቆይታዋን አድርጋ ታናሽ እህቷን ለማሳደግ እና ለማስተማር ስትል ወደ ኢትዮጵያ በማቅናት በኢትዮጵያ አየር መንገድ የበረራ አስተናጋጅ በመሆን ስታገለግል የነበረችውን ወጣት አበራሽ ኪዳኔ ሃይሌ ሁለት አይኖቿን በጩቤ ተዘነቆሉ !

ለረጅም ዘመናት በጓደኝነት እና   በትዳር አጋርነት ፍስሃ ከተባለው ወጣት ጋር ትዳር መስርተው ቢኖሩም ትዳራቸው ሊሰምርላቸው ባለመቻሉ ከስምንት አመታት ቆይታ በሁዋላ ሊለያዩ በቅተዋል::  ይህችው ወይዘሮ ከአቶ ፍሰሃ ጋር በጋራ ሲኖሩ ቆይተው በመሃከላቸው በተፈጠረ አለመግባባት ባለፉት ሁለት ወራት የጋብቻ ፍቺ ቢያደርጉም በመከካከላቸው ለነበረው ግንኙነት መልካም እና የወዳጅነት ሆኖ እንዲቀጥል በማድረግ በጥሩ ጓደኝነት ይጠያየቁ የነበሩት እነዚህ ባልና ሚስቶች የአውደአመትን ምክንያት በማድረግ እና እንደዚሁም ወደ አሜሪካ እሄዳለሁ ብሎ የመሸኛ ዝግጅት ፕሮግራም አለኝ እና ወደ ዝግጅቱ ቦታ እንድትታደም የተጋበዘችውን ወጣት ጥሪዋን አክብራ ወደ ቦታው ሂዳ የጥሪው ተካፋይ በትሆንም በአዲስ አመት በገባ በአጥቢያው  የገጠማት ነገር  የተለየ ነበር የፍቅር አቅርቦት ሳይሆን ድብደባ ነበር። ለእረጂም አስሮ ሰአት ሲደበድባት ከቆየ በሁዋላ ሁለቱን አይኖቹዋን በጩቤ ዘንጥሎ ሲያወጣቸው በአንደኛው በኩል ያለው አይኗ ግን በከፊል ማለትም 10 % ደህና እንደሆነ ከ 10 ሰአታት በላይ በፈጀ የኦፕራሲዮን ህክምና ቢያረጋግጡም  የህክምና ባለሙያዎቹ ከአቅማቸው በላይ በመሆኑ የኢትዮፕያዊ ዜግነት እና የአርብ ዜግነት ያላቸው ባለሃብት ሼክ መሃመድ ሁሴን አላህሙዲ የህክምና ወጭዋን እና የትራንስፖርት ወጭዋን በመቻል በትላንትናው እለት ወደ ባንኮክ ሄዳ ህክምናውን እንድትከታተል ማድረጋቸው ከስፍራው የደረሰን ዘገባ ያመለክታል።

አንዳንድ ጋዜጠኞች የወንጀለኛውን ጓደኞች ለማነጋገር እንደሞከሩት እና ከጓደኞቹ አንዱ ከሆነው ያሬድ ሹመቴ አገላለጽ እንደተረዱት ከሆነ ምንም አይነት የዚህ

አይነት፡ጭካኔ ከዚህ በፊት ያልታየበት መሆኑን የገለጹ ሲሆን አሁንም  ይህ ወንጀለኛ እራሱን እጁን ለፖሊስ መስጠቱን ቢገለጽም ለፖሊስ በሰጠው መግለጫ  የጭንቀት በሽታ እዳለበት እና ከጭንቀቱ ብዛት ያንን ሊፈጽም እንደቻለ ቢገልጽም አንዳንድ የህግ ባለሙያዎች ደግሞ በሰጡት አስተያየት ይህ የመጀመሪያ ደረጃ የጭካኝ በማለት ክሱ ሊመሰረት እንደሚችል ገልጸዋል ።

በሌላም በኩል ለሁለት ቀናት በጉዳቱ እራሷን ስታ የነበረችው ወጣት አበራሽ ከሁለት ቀናት የህክምና እና የስቃይ፣ መከራ በሁዋላ ማን ምን እንዳደረጋት እና መቼ እና እንዴት ይህንን የከፋ ወንጀል  እንዳደረገበት ገልጻለች ። ታናሽ እህቷም በተደረገው ወንጀል ክፉኛ ከመጸጸቷ ባሻገር የእህቷን ህይወት በከፋ ሁኔታ እንዳጨለመባት በምሬት ገልጻ ለእህቷም የህክምና ወጪ በማውጣት እና ጉዞው እንዲቃና ላደረጉት ባለሃብት እና ለኢትዮጵያ አየር መንገድ  ምስጋናዋን  ቸራለች!

Advertisements
%d bloggers like this:
search previous next tag category expand menu location phone mail time cart zoom edit close