ዘመናዊ ባርነት በኢትዮጵያ መንግስት እና በሳኡዲአረቢያ መንግስት እየተካሄደ ነው በማለት ኢሚግራንት ኮኔክት የተሰኘው ድርጅት አስታወቀ

በዘላለም ገብሬ

በአረብ አገራት ለስራ የሚፈለጉት ሰዎች ብዛት ወደ አርባ አምስት ሺህ እንደሚፈለግ ሰሞኑን በኢትዮጵያ ውጥስ ከሰራተናና ማህበራዊ ጉዳይ ጋር ውይይት ያደረጉት የአረብ አገራት ልኡካን የገለጹ ሲሆን በየወሩ ብዛት ያላቸውን ኢትዮጵያውያንን ወደ ሃገራቸው ለማስገባት የሚያስችላቸውን ስምምነት ለመፈራረም በዝግጅት ላይ እንደሆኑ ተጠቁሞአል ይህ በእንዲህ እንዳለ በዚህ የሰዎችን ወደ ተለያዩ የአረብ ሃገራት ለስራ ተብሎ በመንግስታዊም ሆነ በህገወጥ መንገድ ማስተላለፍ እንደባርነት የሚቆጠር መሆኑን የገለጹ አንዳንድ ሰዎች መንግስት ዜጎቹን ከሃገር ከወጡ በሁዋላ የት ደረሱ ሳይል ጉዳት ሲደርስባቸውም አላውቃቸውም በህገወጥ መንገድ ነው የወጡት በማለት ምላሽ በመስጠት የዜጎቹን ሰበአዊ መብት ጥሰት ሲከናወንባቸው ቆሞ ተመልካች ከመሆነም ባሻገር ጥርስ የሌለው አንበሳ በመሆን እወደድ ባይ በአንቀልባ ታዛይ ሆኖ ያለ ስለሆነ ወገኖቻችንን በድህነት ሰበብ አሳልፈን አንሰጥም ከሃገር ወጥተው ሰበአዊ መብታቸው ያልተጠበቀላቸው ወገኖችም የስራ ግብር ቀረጥ ተብሎ ሲገቡ ሲወጡ የሚደርስባቸውን እንግልት ልንታደግ ይገባል በማለት አንዳንድ ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ የመንግስት ሰራተኞች ገልጸዋል። እንደምሳሌነት በቅርቡ በጋዳፊ ቤተሰብ በፈላ ውሃ መቃጠል ምክንያት ሰቆቃና መከራ ለእረጂም ጊዜ ስትገፋ የነበረችውን ወጣት በሲኤንን ዘጋቢ አማካይነት ይህ ነገር ባይጋለጥ ኖሮ መንግስት ግድ እንደማይሰጠው እና በየጊዜው በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ ማላገጥ እና እንደ የበታችነት በመመልከት እየገዛ ነው በማለት እነዚሁ ሰዎች ገልጸዋል ።አሁንም ይላሉ እነዚህ ታዛቢዎች መንግስትም ሆነ እነዚህ ችግረኛ ቤተሰብ ያላቸው ልጃገረድ ሴት እህቶቻችን የማንም ጎረምሳ መጫወቻ እና እንዲሁም በግፍ ግዞት በጥቂት ገንዘብ ጉልበታቸውን ተገፍግፈው ወደ አገራቸው ከመመለሳቸው ባሻገር ምንም ትርፍ ያለው እና ቀሪ ህይወታቸውን ሊለውጡበት የሚችሉበትን ምእራፍ ላይ እንደማያደርሳቸው ቢታወቅም ለእለት ጉርስ ተብሎ የሰዎችን ህይወት በአጭሩ እንዲቀጭ ለማድረግ እና ለእንግልት አሳልፎ መስጠት የለበትም  በማለት ቅዋሜአቸውን ገልጸዋል ። አንድ በውጭ የሚገኝ ወጣቶች ወንዶች እና ሴቶችን ሰበአዊ መብት ተሟጋች ድርጅት ስለኢትዮጵያ ወጣቶች ያተተው ሃተታ እንደሚያመለክተው ከሆነ በአረብ አግራት የሚሄዱ ሰዎች ከጥክማቸው ጉዳታቸው እየከፋ መሆኑን የገለጸ ሲሆን በድርጅቱ የቁጥር አሃዝ መረጃ መሰረትም ከባለፉት አመታት ማለትም ከ1999 እስከ 2005 እ.ኤ.አ በግምቱ ከ 130000 በላይ ሰዎች ወደ ገልፍ ኦፍ አደን፣ዱባይ፣ሊባኖስ ፣እና ጂዳ አካባቢ መሰደዳቸውን ይገልጻል ከእነዚህም መካከል በእድሜአቸው ያለበሰሉ ሲሆኑ  ወንዶች ከ 8 እስከ 14 እና ሴቶች ደግሞ ከ8 እስከ ሃያ አራት የሚሞላቸውን አቅማቸው በማይችለው መንገድ ለካምፓኒ ስራ ፣ዎንዶችንም ሆነ ሴቶችን ለግብረሰዶም እና ለሴተና አዳሪነት እንዲሁም ከቤት ሰራትኝነት አሳልፈው ለሌሎች ወዳጆቻቸውም ጭምር ሰራተኛ በማድረግ ከፍተኛ ተጸኖ እያሳደሩባቸው እንደሚጠቀሙባቸው የገለጸ ሲሆን  በልጆቹ ላይም ከፍተኛ የአእምሮ መዛባት እና ፍርሃትን እንዲሁም በራስ አለመተማመን ሊያድርስ የሚችል ጉዳት ሲደርስባቸው ከ129 በላይ የሚሆኑ ሴቶች እራሳቸውን በማጥፋት አስከሬኖቻቸው ወደ ኢትዮጵያ መግባቱን ይገልጻል ከዚህ ጋርም በማያያዝ ከአረብ አገር በመጡ ሴቶች ላይ በተደረገ ጥናት መሰረት አብዛኞቹ ሴቶች የማስተዋል እና የማሰብ ችግር በከፍተና ደረጃ ሲታይባቸው ሚዛናዊ የሆእ አስተሳሰብ እና የማመዛዘን ተግባራቸው ስለሚጎድል ማናቸውም ከአረብ አገር የሚመጡት ሴቶችም ሆኑ ወንዶች ሳይካትሪስት ሊያስፈልጋቸው ይገባል በማለት ሃተታውን ያትታል ፣በሌላም በኩል በዚህ ሳምንት በኢትዮጵያ ውስጥ ለሰራተኞችን ጉዳይ  ለመዋዋል ያቀኑት የሳኡዲ አራቢያውን አምባሳደር እና እንዲሁም የኢትዮጵያውን አቻቸውን ለዘረፋ እና የሰዎችን ህይወት ለባርነት ለማጋለጥ የተነሱ አምባገነኖች በማለት ዘልፎአቸዋል ። በዘመናዊ የአሰራር ዘዴ ሰዎችን በተለያዩ አገራት በማጓጓዝ የሚደረገውን ዘመናዊ ባርነት እንዲቆም የሁላችንም ጥረት ያስፈልገዋል ይኅን ጉዳይ የአፍሪካ ጉዳይ ሳይሆን የሌሎችም ሃገራት ጥረት ነውና መንግስትም ይህንን አውቆ የሰዎችንን የማጓጓዝ እና የባርነት ሽያጭ ስራውን ቢያቆም ይሻላል በማለት ኢሚግራንት ኮኔክት የተሰኘው ድርጅት ዳይሬክተር የገለጹ ሲሆን ሰሞኑን ለኦባማ አስተዳደር ምክርቤት ይህ ጉዳይ በሰፊው የሚታይበትን ሁኒታ ለመግለጽ የሚያስችለውን ድብዳቤ እንደሚጽፍ አክሎ ገልጾአል ።

Advertisements
%d bloggers like this:
search previous next tag category expand menu location phone mail time cart zoom edit close