የቀድሞ የኢትዮጵያ ህዝባዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐሊክ /ኢህዲሪ/ ፕሬዝዳንት መንግስቱ ኃ/ማርያም ባለፈው ሐሙስ ዕለት አውስትራሊያ አገር በሚተላለፈው ኤስ ኤስ ሬዲዮ ጋዜጠኛ ካሣሁን ሰቦቃ ጋር ቃለ ምልልስ አድርገዋል፡፡ የቃለምልልሱን ዝግጅት ክፍሉ እንደሚከተለው አቅርበናል፡፡”ሐሳብን በነፃነት መግለጽና ለመብት መሟገት በሽብርተኝነት አያስወነጅልም”!ነጋሶ ጊዳዳ

ሐሳብን በነፃነት መግለጽና ለመብት መሟገት 
በሽብርተኝነት አያስወነጅልም!

የቀድሞ የኢህዲሪ ፕሬዝዳንት መንግስቱ ኃ/ማርያም 
ደቡብ ሱዳን ነፃነቷን ተቀዳጅታ 54 የአፍሪካ ሀገር ኅብረት 
አባል ሆናለች፡፡ በነፃነት ትግሉ ወቅት በእርስዎ የአመራር 
ዘመን የኢትዮጵያ አስተዋጽአዎች ምን ነበሩ? በግል 
እንደወቅቱ መሪነትዎ እንዲሁም የኢትዮጵያ ህዝብ እንደ 
ህዝብ ለትግሉ ስኬት ያደረገው አስተዋጽኦ በታሪክ ምን 
ሥፍራ ይኖረዋል? ደቡብ ሱዳን በአሁ ወቅት ነፃ አገር 
በመሆኗ ምን ይሰማዎታል?
ወደ ዋናው ጉዳይ ከመግባቴ በፊት እኔ በአጠቃላይ እስከ 
ዛሬ ድረስ ብዙ እንደ አንተና አንተን የመሰሉ ኢትዮጵያኖች 
በተለያዩ ጊዜ በተለያየ አጋጣሚ በተለያየ ርዕስ ላይ 
ሊያነጋግሩኝ ፈልገዋል፡፡ እንደዚህ ያሉትን ጥያቄዎች 
ለማስተናገድ ፍላጐት የለኝም፡፡ በአጠቃላይ የኢትዮጵያን 
ህዝብ አብዮት ታሪክ የሚመለከት ያዘጋጀሁት መጽሐፍ 
ከአንድ ወር በማይበልጥ ጊዜ ውስጥ ወጥቶ ለብዙዎቹ 
ምናልባት መልስ ይሰጣል ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ፡፡ 
በተከታታይ እስከ ክፍል ሦስት ድረስ ይወጣል፡፡ ከዚህ 
አኳያ ነው ኢትዮጵያውያን ወንድሞቼን እህቶቼን እኔ 
የነበርኩበትን ሁኔታ ልመልስ እችላለሁ፡፡ ከዚህ በተረፈ 
ጋዜጠኞችና አንዳንድ ሰዎችን ላላስተናግድ እችላለሁ፡፡ 
ለዚህ የበቃንበት ብዙ ምክንያቶች አሉ፡፡ በእኔና ከእኔ ጋር 
በነበሩ ጓዶቼ ከእነሱ ጐን የቆምነው በእውነቱ ከደቡብ ሱዳን 
ህዝብ ታሪክ ብሶትና አረቦች ከሚያደርሱባቸው ባርነትና 
ረገጣ አኳያ እጅግ የሚያሳዝን ህይወት የሚገፉ ስለነበሩ 
ከንፁህ አፍሪካዊ ስሜት ነው፡፡ ከንፁህ ስብአዊ ስሜት 
ነው፡፡ 
ያንን ያህል ድጋፍ አገሪቱ ካለችበት ችግር ላይ እያለች 
የራሷ ጦርነት እያከናወነች ባለችበት ወቅት 80ሺ ጠንካራ 
ጐሬላ ልናስለጥንላት የቻልነው፡፡ አገሩ ሰፊ ከመሆኑም 
በላይ መላው የአረብ መንግስታት በእነዚያ ጭቁን ድሀዎች 
ላይ ይረባረቡባቸው ከነበረው ጭቆና አኳያ ለመመከት 
ባልተፈለገ ምክንያት ነው፡፡ ሰው ገብረንላቸዋል፡፡ 
አስልጥነንላቸዋል፡፡ አስታጥቀናቸዋል፡፡ የጦር አመራርና 
ጠቅላላ የትጥቅና የምክር እስትራቴጂ ረድተናቸዋል፡፡ 
በአገሩ በሙሉ ተዋጊዎች ብቻ ሳይሆኑ ስደተኛ ህዝብ 
ከ10-15 ዓመት በላይ ሙሉ ኢትዮጵያ ውስጥ ነው 
የተጠለለው፡፡ ስደተኛ እንመግባለን፡፡ ዓለም አቀፍ እርዳታ 
እየለመንን እናስቀርብላቸዋለን፡፡ ሠራዊቱን እንመግባለን፡፡ 
ለሠራዊቱ የሚያስፈልገውን ቁሳቁስ እናቀርባለን፡፡ በዚህ 
ውጤትና በእነሱ ቁርጠኛ ታጋይነት የተነሳ በብዙ ጥረትና 
ላብና ደም መስዋዕት ዛሬ ነፃ መውጣት ችለዋል፡፡ ይህ 
ማለት ምን ማለት ነው? ቢባል ከሁሉ በፊት ያ የተበደለና 
የተጨቆነ አፍሪካዊ ህዝብ ነፃ መሆኑ ማንኛውንም ሰው 
የሆነውን ሁሉ ሊያስደስት ይገባል፡፡ እኔም የህዝብን 
ስሜት ነው የምጋራው፡፡ ሌላ ደግሞ የሰሜኑ ሱዳን 
መንግስት በአገራችን የሰሜኑን ክፍል ከመነሻው አረቦችን 
እያስተባበረ ሲያደማን፣ሲያስወጋን ብሎም ዛሬ ኢትዮጵያ 
የደረሰችበትን ደረጃ ዋናውን አስተዋጽኦ ያደረገ ኢትዮጵያን 
ያስገነጠለ መንግስት ስለሆነ እኛ 3ሺ 4ሺ ካሬ ሜትር 
ኤሪያ ከአንድ 3ሚሊዮን የሚደርስ ህዝብ ወገኖቻችን ህዝብ 
ተነጥለናል፡፡ እንዲሁም ወደባችንን ባጠቃላይ የዚህ አገር 
ህዝብ መነጠል የሚያሳዝን ነው፡፡ እና ደግሞ የማይረሳ 
አጥንት የሚሰብር ቁስል ቢሆንም ቅሉ ከሱዳን ጉዳት ጋር 
የታየ እንደሆነ ኢትዮጵያን የሚያህል ሀገር ነው፡፡ ዛሬ 
ሱዳኖች ያጡት ይኸው ለም ዐፈር፣ወርቅ፣ነዳጅ፣ ያካበቱ 
ሀብት ነው፡፡ ያለ ደቡብ ሲዳን ሱዳን ምን እንደሚመስልና 
ምን ዓይነት ክፍለ ሃገር እንደሚሆን መገምገም የሚቻል 
ይመስለኛል፡፡ የቀረው በረሃው ነው፡፡ የቀራው አሸዋው 
ነው፡፡ ይህ ብቻ አይደለም፤ደግሞ በምዕራብ ------ ሌላ 
ትግል ይጠብቃቸዋል፡፡ ምናልባትም ደቡቡን ሊቀላቀሉ 
ይችላሉ እና ሱዳኖች እየለመናቸው አንድ ወንዝ ኩታ 
ገጠም ድንበርተኞች ነን፤አንድ ዓይነት ቋንቋና ባህል 
ያላቸው ህዝቦች በድንበር እንወራለን አገሮች በከፋ መልኩ 
ብቻ ሳይሆን የተለዋወጧቸው በበጐ ጐኑ የሚነሱ መልካም 
መልካም ነገሮች አሉ፡፡ ኢትዮጵያኖች በፋሽሽት ወረራ ጊዜ 
ብዙዎቹ ሱዳን አገር ኖረዋል፡፡ ይህንን እና እንደ ትልቅ 
ውለታ እንቆጥረዋለን፡፡ እንዲህ ዓይነት ደግ ደጉን ነገር 
ከማራመድ ይልቅ በአገራችን ጉዳይ ገብታችሁ ይህንን 
መስራታችሁ አግባብ አይደለንም፡፡ እኛም ከፈለግን በእናንተ 
ቁስል ደካማ ጐን ገብተን ብዙ ነገር ለማድረግ የሚሳነን 
አይደለም፡፡ ስለዚህ ይህንን ድርጊታችሁን አቁሙ፡፡ ብለን 
ከአንዴም ሁለት ጊዜ አገራቸው ድረስ ሄደን ለምነናቸዋል፡፡ 
ሊቀበሉን አልቻሉም እና ዛሬ የእጃቸውን አግኝተዋል፡፡ 
ከእንግዲህ ወዲያ ያግንባር ወይም የሱዳን ግንባር የአረቦች 
የጥፋት መንደርደሪያ እንደመሆኑ መጠን ዛሬ ነፃነቱን 
ያገኘው አፍሪካዊ የደቡብ ሱዳን ተጠናክሮ የቆመ እንደሆነ 
በዚያ በኩል ኢትዮጵያ ስጋቷ በጣም የቀለለ ወይም 
ጨርሶ የተወገደ ነው ብዬ አስባለሁ፡፡ በተመሳሳይ በሱማሌ 
ተደረገው ዛሬ ሱማሌ ለእኛ የምታሰጋ አገር አይደለችም፡፡ 
ስለዚህ በሱዳንና በሱማሌ በኩል የተደረገው ነገር በአጥቂነት 
ሳይሆን በእነሱ እብሪተኝነትና እኛን በማጥቃት የወሰዱትን 
እርምጃ ለመከላከል የተወሰደ እርምጃ ነው፡፡ በዚህ ረገድ 
ኢትዮጵያኖች በሙሉ ሊኮሩ ይገባል፡፡ ከነፃነትና ከአገር 
ህልውና አኳያ የሚያዝና ግኝት ድል ነው፡፡ በአጠቃላይ 
ለማጠቃላል የምለው ይህንን ነው፡፡”
“እዚህ አውስትራሊያ ጨምሮ በመላው ዓለም ላይ 
በስደት ለሚገኙ ኢትዮጵያውያንና አገር ቤት ለሚገኙ 
ኢትዮጵያውያን በጠቅላላ የሚያስተላልፉት መልዕክት 
ይኖራል?” 
“ኢትዮጵያ በምን ሁኔታ ላይ እንዳለች ለማንም 
ግልጽ ነው፡፡ በእርግጥ እንደ ግንዛቤአችንና እንደ ንቃተ 
ህሊናችን እንደ መረጃ ግንዛቤአችን አመለካከታችን ሊለያይ 
ይችላል፡፡ ስለዚህ ኢትዮጵያዊ ሁሉ ኢትዮጵያን ከዚህ 
አስከፊ ሥርዓት ለማውጣት መታገል አለበት፡፡ ለዚህ 
ነገር መተኛት የለበትም፡፡ ይህ ሊሆን ካልቻለ ለዘላለም 
ለትውልድ አስፋሪና አሳፋሪ ታሪክን ጥሎ ማለፍ ነው፡፡ ዛሬ 
አሳፋሪ ቡልኮ ለብሰን ነው የምንኖረው ማለት የምችለው 
ይህንን ነው፡፡” 
“የቀድሞው የኢህድሪ ፕሬዝዳንት መንግስቱ ኃ/ማርያም 
ስለትብብርዎ አመሰግናለሁ!”
ዛሬ የምንኖረው አሳፋሪ 
ቡሉኮ ለብሰን ነው!!


Advertisements
%d bloggers like this:
search previous next tag category expand menu location phone mail time cart zoom edit close