ተጣብቀው የተወለዱ ህጻናቶች በተሳካ ሰርጀሪ ሊለያዩ በቁ

በዘላለም ገብሬ

በትላንትናው እለት ነበር በእንግሊዝ የሚገኘው ብሪትሽ ቻርቲ ዘ ዎርልድ የተሰኘው ድርጅት የሁለቱን ተጣብቀው የተወለዱ ህጻናት ፎቶ ግራፍ ለህዝብ እይታ ያበቃው ሲሆን በእለቱ አስደናቂ በሆነ የህክምና ጥበብ የአስራ አንድ ወራት እድሜ ያላቸውን መንትዮች ህጻናት ያለምንም ችግር ህይወታቸውን በማትረፍ ሊለያዩ በቅተዋል ። እነዚህ ሁለት ህጻናቶች እይታቸው የነበረው ሁለቱም በተለያዩ የተቃራኒ ቦታ ማለትም የአንደናው ከአንደኛዋ ግራ እና ቀኝ ከአንገታቸው ዞረው የተወለዱ ሲሆን በልጅነት እድሜአቸው ለመለያየት መቻላቸው እራሱ ከሞት ሊያተርፋቸው እንደቻለ ለንደን የሚገኘው የህጻናት ሆስፒታል ገልጾአል ። ሪታል እና ሪታግ የተበሉት እነዚሑ ጨቅላ ህጻናቶችን ለመታደግ ረጂም ጊዜ መውሰዱን የህክምና ባለሙያዎቹ ጠቅሰዋል ። ተጣብቀው የሚወለዱ መንትዮች ከ 2.5 ሚሊዮን ህጻናት አንድ ጊዜ ሊወልድ የሚችል ሲሆን በህይወት የሚተርፉት ግን የተወሰኑት መሆናቸውን አክለው ገልጸዋል ።”በጣም ከፍተኛ ሃላፊነት ነው “በማለት የገለጹት በኒውዮርክ የሚገኘው ሞንቴፊዮሪ ህጻናት ሆስፒታል ኮኦርዲኔተር  ዶ/ር ጀምስ ጎድሪች ከዚህ በፊትም ማለትም እንደ ኤሮፓውያን ዘመን አቆጣጠር በ 2004 አካባቢ በተመሳሳይ ሁኔታ ሁለት መንትዮዎችን ማለያየታቸውንም ጠቁመዋል ።ቻርቲ እንደገለጸው ከሆነ  ህክምናው የተከናወነው በግሬት ኦርሞንድ ሆስፒታል ሲሆን ይህ የህክምና ስራ የተጀመረው ግንቦት ወር ላይ ሲሆን የሰውነት ሴሎችን የመዘርጋት ሁኔታ ነበር የተከናወነው ቀጥሎም በሰውነት ውስጥ የስራ ተግባራቸውን ለማከናወን የሚችሉ ሌሎች የሰውነት አካሎች ጥገና የተደረገ ሲሆን ቀጣዩም ከባድ ስራ የቆዳ ሽፋን በተከፈተው ቦታላ የመሸፈኑ ተግባር እንደሆነ ተገልጾኣል ።በሰኔ ወር ደግሞ የማለያየቱ ስራ በአጣዳፊ ሁኔታ መከናወኑን ቻርቲ አስታውቆአል ።ሁለቱም ህጻናት በአሁን ሰአት በሙሉ ጤንነት ላይ የሚገኙ ሲሆን ከሆስፒታል ወጥተው ወደ ቤተሰቦቻቸው መቀላቀላቸው ትልቅ ደስታ ለቤተሰቦቻቸው መፍጠሩን አጃንስ ፍራንስ ፕሬስ አክሎ ጠቁሞአል !

Advertisements
%d bloggers like this:
search previous next tag category expand menu location phone mail time cart zoom edit close