የሽብር ጥቃት እና አሸባሪነት ማለት ምን ማለት ነው ?

በዘላለም ገብሬ

አሸባሪነት የሚለው ቃል ጥሬ ትርጉም ሙሉ በሙሉ ይዞ ባይመጣም የአንድን አካባቢ ሰላም መንሳት ለጉዳት ማድረስ እና ለጥቃት ማጋለጥ የሚሉት በተወሰነ መልኩ ሊገልጹት ሲችሉ በተቀራራቢነት ምን ማለት እንደሆነ በስነ ስርአት ሊገልጸው የሚችል ትርጉም ይነረዋል ለማለትም ያስቸግራል ። እንደ እንግልዝኛውም አጠራር እና የትርጉም ሁኔታም የሚያመለክተው ተመሳሳይ አይነት ትርጉም ቢሰጠውም ትክክለኛ ትርጉሙን ለማስቀመጥ  ከበድ ያለ ቢሆንም አጠቃላይ ይዘቱን ሲታይ ግን በህብረተስብ እና በሃገር ጉዳይ ላይ ከፍተኛ ጉዳት የሚያደርስ እና ሃገርን ከምንም በላይ ችግር ውስጥ የሚያስገባ የሰላማዊ ህዝብን ሰላም የሚነሳ እና እንዲሁም የሃገርንም ሆነ የመንግስትን ኢኮኖሚ የሚጎዳ ሆኖ ሲገኝ አሸባሪ ሊያሰኝ የሚችል ሲሆን በአንድ አካባቢ ወይንም በሃገር ላይም ሆነ ብህዝብ ንብረት ላይ ውድመትን የሚያካሂድ ሰው ፣በሰዎች ላይ ለአደጋ የሚያጋልጥ ስራ ሲፈጽም ካልሆነም ደግሞ ለአደጋ የሚያጋልጥ ነገር ቅስቀሳ ሲያደርግ በትክክለኛ መረጃ የተያዘ ሰው አሸባሪ ተብሎ ሊያዝ እንደሚችል የተለያዩ ጽሁፎች ያመለክታሉ እንደምሳሌ ያህል በዩናይትድ ስቴትስ ኦፍ አሜሪካ የህግ አንቀጽ ቁጥር (From U.S. Code Title 22, Ch.38, Para. 2656f(d)

በተጠቀሰው መሰረት አሸባሪ የሚለው ቃል ከላይ የጠቀስኳቸውን ዋና ዋና ነገሮች አሟልቶ ሲገኝ እና  በኢትዮጵያ ውስጥ ግን የምናየው በጽሁፍ ስራ የተሰማሩ ሁሉ አሸባሪ ብሎ ፈርጆአቸው ይገኛል ስለዚህ ምን ማለት ነው የሚለውን የኢትዮጵያ መንግስት ማወቅ የሚገባው ይመስለኛል ። በተለይም የአሸባሪዎች ባህሪ እድርጅት ተዋቅረው ሰዎችን እና ትልልቅ ድርጅቶችን ከማጥቃታቸው ባቻገር የመንግስትን የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ ለማሽመድመድ የሚያደርጉት ትግል ትልቅ ቦታ እንዳለው  በኒውዮርክ ታይምስ ከአስር አመት በፊት የወጣው ጋዜጣው እትም ያሳያል ።ይህንንም እንደማጠናከሪያ አድርጎ የአሜሪካው የህግ ረቂቅም በተመሳሳይ መልኩ አስቀምጦታል ።ለዚህም ከላይ የጠቀስኩት የአሜሪካውን የህግ ቁትር ከሚተነትናቸውን የአሸባሪነት ትርጉም እና የድርጅቶቻቸውን ስራ በህጉ መሰረት ያስቀመጠውን እንዲህ በተወሰነ መልኩ  ከስር አስቀምጠዋለሁ ።

United States Law Code – the law that governs the entire country – contains a definition of terrorism embedded in its requirement that Annual Country reports on Terrorism be submitted by the Secretary of State to Congress every year. (From U.S. Code Title 22, Ch.38, Para. 2656f(d)

(d) Definitions
As used in this section—
(1) the term “international terrorism” means terrorism involving citizens or the territory of more than 1 country;
(2) the term “terrorism” means premeditated, politically motivated violence perpetrated against noncombatant targets by subnational groups or clandestine agents;
(3) the term “terrorist group” means any group, or which has significant subgroups which practice, international terrorism;
(4) the terms “territory” and “territory of the country” mean the land, waters, and airspace of the country; and
(5) the terms “terrorist sanctuary” and “sanctuary” mean an area in the territory of the country—
(A) that is used by a terrorist or terrorist organization—
(i) to carry out terrorist activities, including training, fundraising, financing, and recruitment; or
(ii) as a transit point; and
(B) the government of which expressly consents to, or with knowledge, allows, tolerates, or disregards such use of its territory and is not subject to a determination under—
(i) section 2405(j)(1)(A) of the Appendix to title 50;
(ii) section 2371 (a) of this title; or
(iii) section 2780 (d) of this title. ይህንን ካየን ትርጉሙ የአሸባሪነት ስራን ከ ጋዜጠኞች ጋር እንዴት ሊገናኝ ይችላል ብለን ልንጠይቅ እንችላለን ,በእርግጥም ጋዜጠኞችን ሊያስከሥ የሚችልበት ሁኔታ ሊኖር ይችላል ግን እንደዚያም ቢሆን የጋዜጠኞች ስራ የመረጃን ማቀበል ስራ እስከሆነ ድረስ የመገናኛ ብዙሃንን ህግ ተከትሎ ማናቸውንም የመረጃ ፍሰቶች ያለምንም የመንግስት ገደብ እና የኤዲቶሪያል ፖሊሲ ቁጥጥር ውጭ ለህብረተስብ የማቅረብ እና መረጃን ሰጥቶ የማስተማር የማሳወቅ መብት እንዳላቸው ይታመናል በዚህም መንግስት ከባድ ግዴታ እንዳለበት ቢታውቅም ያንን ግዴታ ለመፈጸም የአፍሪካ መንግስታቶች እንደማይወዱ እና እንደማይፈቅዱ በኢትዮጵያ መንግስት በተደጋጋሚ የሚታየው የጋዜጠኞችን የማሰቃየት እና የማሰር ባልተገባ እና ምንም መረጃ በሌለው የስራ አፈጻጸም ክስ መመስረት የሚያሳይ ትልቅ መረጃ መሆኑን ለመግለጸ የሚያሻ አይመስልም ስለዚህ ወደ ዋናው ርእስ ልመለስ እና  እንደ ዩናይትድ ኔሽን አገላለጽ ከሆነ ደግሞ አሸባሪነት የፖለቲካ ድርጅቶች የፖለቲካ ድርጅታቸውን ከገዚው ፓርቲ ጋር  ላለማዋሃድ እና እራሳቸውን ወደ ስልጣን ለማምጣት የሚያደርጉት የነውጥ እንቅስቃሴ ወይንም ከመንግስት ፈቃድ ውጭ የሚያደርጉትን ሰላማዊ ሰልፍ ወይንም የተቃውሞ ሰልፍ በማስመልከት በመንግስት እና በሃገር ላይ ጉዳት ሲያደርሱ እና ሰላማዊ ሰውን ለጉዳት ሲያደርሱ እና ጉዳትም ከልክ ያለፈ ሆኖ ከተገኘ በአሸባሪነት ሊከሳቸው እንደሚችል ይገልጻል ይህ በእንዲህ እንዳለ ግን አሸባሪ ተብሎ ተጠርጥሮ ሊከሰስ የሚችል ማንኛውም ግለስብ ሊኖር እንደማይችል ይጠቁማል ይህም ማለት በትግባር ተሳትፎ እስካላደረገ ድረስ ለማለት የሚያስችል ይመስላል የጽሁፉ አቀራረብ ይህም ማለት መረጃ እስካልተገኘበት እና በማህበር ተደራችቶ መንግስትንም ሆነ መንግስታዊ ድርጅቶችን ለማጥቃት እስካልተነሳሳ ድረስ እና በአካባቢው የሚኖሩ ማህበረሰብን ለጥቃት እስካልዳረገ ድረስ አሸባሪ ተብሎ ሊሰየም እንደማይችል ይገልጻል ። በማህበር ተደራጅቶ አንድን አካባቢ ሃገር እና መንግስትን ለማጥፋት እና ምንም ርህራኄ ባልተሞላበት ሁኔታ በማህበረሰቡም ሆነ በቲልልቅ ተቋማት ወይንም በመንግስት ላይ የሚካሄድን ጥቃት የአሸባሪዎች ጥቃት ሊባል ሲችል ለአንድ ሃገር እድገት ወይንም የነጻነት እንቅስቃሴ በሃገር ውስጥ በመንግስት ፈቃድ ፖለቲካዊ ድርጅቶችን አቋቁሞ ማናቸውንም እንቅስቃሴዎች ማድረግ ግን ከአሸባሪነት ከምንም በምንም በኩል ሊፈረጁ እንደማይችሉ ተገልጾአል ። ስለዚህ መንግስት ለምን የፖለቲካዊ እንቅስቃሴ እንዲያካሂዱ ፈቃድ ከሰጠ በሁዋላ መልሶ ተቃዋሚዎችን ማሰር አልፈለገም ነው ወይስ ሽንፈቱን ስለማይቀበል እነሱን በማሰር እና በማንገላታት በመግደል ወይም በማሰደድ ድል መቀናጀት ፈልጎ ነው ? በመላው አለም የአሸባሪነት የተጠቀሱት የተለያዩ አሳዛኝ እና ዘግናኝ ሂደቶች እንዳሉ ይታወቃል እንደምሳሌ ያህል የዛሬ አስር አመት በኒውዮርክ የተካሄደው የአሸባሪዎች ጥቃት የመጀመሪያ ደረጃውን ሲይዝ ይሀውም የመጀመሪያ ደረጃነቱን የያዘበት ምክንያት አላማ ተደርጎ የታሰበው ጥቃቱ በትክክል አላማውን በመምታቱ እና አላማውን እንዲመታ ያደረጉት ማህበረሰቦች እራሳቸውን ጨምረው ሌሎች በሺዎች የሚቆጠሩ ንጹሃንን ዜጎች በመፍጀታቸው ሲሆን በሁለተኛ ደረጃ በአለም ላይ የሚታወቀው በቤይሩት  ኢንተርናሽናል አየር መንገድ ላይ ኦክቶበር 1983  የተከናወነው ጥቃት ሲሆን 241 የአሜሪካን ሰራዊቶችን ሰለባ ያደረገበት  መሆኑን በአለም አቀፍ ደረጃ በአስከፊው የጥቃት መዝገብ ተብሎ ተመዝግበው የሚገኙት ናቸው ።በሌላም በኩል በ 1972 ሙኒክ ላይ የተደረገው ጥቃት ሲሆን ይሄውም ቀን ብላክ ሴብቴምበር የሚል ስያሜ የተሰጠው መሆኑን መረጃዎች አክለው ገልጸዋል። በማጠቃለያ ደረጃ አሸባሪ ማለት በማህበርም ሆነ በነጠላ መንግስታዊ ተቋምን እና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋሞችን እንዲሁን ዜጋዎችን ለጥቃት እና ለከፋ ደረጃ ማድረስ ፣ማስፈራራት መግደል እና ሌሎችም በጭካኔ የተሞሉ ስራ ሲከናወኑ መሆኑን ሳልጠቁም አላልፍም እና የኢትዮጵያ መንግስት በአሸባሪነት የሚፈርጃቸውን ጋዜጠኞች በአስጨኳይ መፍታት የሚገባው መሆኑን በዚሁ ጽሁፍ ሳሳላነሳ  አላልፍም ”  መረጃ ሃይል ነው ” ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር እግዚአብሄር ኢትዮጵያን ይባርክ !

Advertisements
%d bloggers like this:
search previous next tag category expand menu location phone mail time cart zoom edit close