ሰበር ዜና የሙአመር ጋዳፊ የስልጣን ዘመን አበቃለት ጋዳፊም መሞቱ ተገለጸ!

ጋዳፊ ተደብቆበት የነበረው ዋሻ

ለ42 አመታት በግፈኝት አገዛዝ ሲገዛ የቆየው የሊቢያው መንግስት አስተዳደር ሞአመር ጋዳፊ ዛሬ ሃሙስ ማለዳ ከተደበቀበት ዋሻ በመገደሉ የስልጣኑ እድሜ እንዳበቃለት የእለቱ ሰበር ዜና አብስሮአል ።ባለፉት 9 ወራቶች በሃገሪቱ ላይ በተቀሰቀሰው የተቃውሞ ነውጥ አይሎ በመምጣቱ እና በጦር ሰራዊቶች ታጅቦ የሃገሪቱን መሰረታዊ ይዘት የለወጠው ይኸው ከፍተኛ ጦርነት ከብዙ ጊዜ የህይወት እና የንብረት መሰዋእት የተከፈለበት ሲሆን ዛሬ ግን ከተደበቀበት ዋሻ  በገጠመው አሳቻ እና አስቸጋሪ ጦርነት ማምለጥ ባለመቻሉ በጥይት ደረቱ ላይ ተመቶ ከወደቀ በሁዋላ ለማምለጥ ቢሞክርም በታጣቂ ሰራዊቶች ተይዞአል ።

በታጣቂዎች ጋር በተከፈተው የረጂም ሰአት የጦር መሳሪያ ተኩስ ልውውጥ የጋዳፊ ሰራዊት በከፍተኛ ሁኔታ ከመዳከሙም በላይ በጦርነቱ መካከል ሙአመር ጋዳፊ ተመቶ ከወደቀ በሁዋላ ተነስቶ ሊያመልጥ ቢሞክርም በተቃዋሚ ሰራዊቶች እጅ ላይ በመውደቁ ወደ የትም ማምለጥ አልቻለም ነበር ።

የሊቢያ ታጣቂዎች ቁስለኛውን ጋዳፊን በቃሬዛ አንስተው ከትውልድ አገሩ ሰርጥ ወደ ምስራታ ከመውሰዳቸው ከጥቂት ሰአታት በሁዋላ   የህይወት ደብዛው ጠፍቶአል :: በሌላም በኩል የጋዳፊ አንደኛው ልጁ ማለትም ሞሃመድ  ሙታሰን ጋዳፊ የቆሰለ ሲሆን በአሁን ሰአት በእስር ላይ እንደሚገኝ አልጀዚራ ቴሌቪዥን ገልጾአል   ።

የሊቢያ ህዝብም ደስታውን ለመግለጽ ከጎዳና ላይ በመውጣት በመጨፈር ርችት በመተኮስ እንዲሁም ጋዳፊ ይለብሳቸው የነበሩትን የክብር ልብሶች በመቅደድ እና በማቃጠል ሲገኙ በመላው ሃገሪቷ የብሄራዊ ባንዲራዋ እንዲውለበለብ አድርገዋል ። የጋዳፊ ደጋፊ ሰራዊቶች በአሁን ሰአት የደረሱበት ባይታወቅም በነዋሪ ማህበረሰቦች ላይ ግን ትልቅ ቀውስ ሊገጥማቸው ይችላል በማለት የፖለቲካ አናላይሲስቶች ይገልጻሉ ።

የአፍሪካው ዲክታተር  ዛሬ አለቀለት ዛሬ ሁላችንም ነጻ ወጣን እያሉ ዝማሬአቸውን ያሰሙት የሊቢያ ነዋሪዎች ካለፈው ስምንት ወራት ጀመሮ የተሰውትን ሰማእታት ፎቶግራፎችንም በሚዲያ ላይ ለቀዋል ። የመአመር ጋዳፊ ደጋፊ የነበሩት ሁለት ዘሮች በአሁን ሰአትም ወደ ተቃዋሚ ፓርቲው መቀላቀላቸውንም አልጀዚራ አክሎ ገልጾአል ።ፍትህ በመጀመሪያ አስፈላጊ ነው የግብጹም ፕሪዚዳንት የገጠማቸው ይኸው እጣ ፈንታ ነው ዛሬም ይህ ቀን ለጋዳፊ በመሆኑ የትሪፖሊም ሆነ የሌሎች አገር ተወላጆች ደስታቸው ነው በማለት ቀጣዩ አስቸኳይ የሊቢያን ግንባታ ማድረግ ሲሆን 10 ወይን 12 % የአገሪቱን ረቂቅ አዋጅ መቀየር ነው ዛሬ መሃመድ ጋዳፊ ተገሎአል እንዴት እና የት ተገደለ በማን የሚለውን ዝርዝር ዘገባ እናቀርባለን በማለት ጊዜአዊ አስተዳደሩ ጠቁሞአል:: የጋዳፊ አስከሬን ከተወለደባት ሰርጥ ወደ  ሚስራታ የተወሰደ ሲሆን በዋና ከተማዋ ትሪፖሊ የድል ምልክት የሆነውን የሁለት ጣት ምልክት በማሳየት እና የሃገሪቱን ባንዲራ በከፍተኛው ሁኔታ ሰቅለው በማውለብለብ ላይ የሚገኘው የሊቢያ ህዝብ ዛሬ ሰላምን እንሻለን ሰላም ዛሬ ወርዶአል የሰርጥ የትሪፖሊ ተብሎ የሚታሰብ ህዝብ የለም እኛ ህዝባችን አንድ ነው በማለት የታጣቂ ሰራዊቶች ገልጸዋል ። በሌላም በኩል የፖለቲካል አናላይስቶች እንደገለጹት ከሆነ በቅርቡ 10 ወይንም 12 % የሚሆነውን የሃገሪቱን ህገ መንግስት አዋጅ የመቀየር ሂደት የሚከናወን እንደሚሆን የጠቆሙ ሲሆን የሃገሪቱን መልሶ ማቋቋም ግንባታም ተያይዞ የሚደረግ መሆኑን አክለው ገልጸዋል ።የሽግግር መንግስቱ በአሁን ሰአት አገሪቱን ሊመሩ የሚችሉትንም ሰዎች ስም ዝርዝር አውጥቶ ለህዝብ አሳውቆአል ። “ዛሬ ለአለም ህዝብ የምናሳውቀው ቢኖር መሃመድ ጋዳፊ ተገሎአል የአለም ሚሽነሪዎችም ልታውቁት የሚገባው ዛሬ የሽግግር መንግስታችንን እንመሰርታለን “በማለት የተቃዋሚ አሰተዳደሮች ገልጸዋል ” በሌላ በኩል የእንግሊዙ ጠቅላይ ሚንስትር ዴቪድ ካመሮን የሊቢያ ህዝብ እንኳን ደስ ያላችሁ ዛሬ ትልቅ ድላችሁ ነው የአለምም ድል ነው ሲሉ ተደምጠዋል ወደፊትም ከእናንተ ጋር ሆነን እረዳዳለን” በማለት መለክታቸውን ሲያስተላልፉ የዩናይትድ ኔሽኑ ባንኪሙንም “ከእንግዲህ የእድገት ቀናችሁን ጀምራችኋል እና ወደ ልማት ጎዳና ፊታችሁን አዙሩ” ብለዋል

።በመላው ሃገሪቱ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ህዝቦች በከተማዋ በመውታት ደስታቸውን በመግለጽ ላይ ይገኛሉ ።።በመጨረሻም ይህንን ዜና እስካጠናከርኩበት ሰአት የሞአመር ጋዳፊ ልጅ ሙታሰን ጋዳፊ መያዙን የተረጋገጠ ቢሆንም ከሰአታቶች ቆይታ በሁዋላ በሰርጥ ውስጥ መገደሉን አሶሼትድ ፕሬስ ዘግቦአል የሞተውንም ሰውነቱንም ምስል ለህዝብ አቅርበዋል ።

Advertisements
%d bloggers like this:
search previous next tag category expand menu location phone mail time cart zoom edit close