– ቤተመጻሕፍቱም በስማቸው ተሰየመ

በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የኢትዮጵያ ጥናትና ምርምር ተቋም፣ በማስገንባት ላይ ያለውን ቤተመጻሕፍት በፕሮፌሰር ሪቻርድ ፓንክኽረስት ስም እንደሰየመ አስታወቀ፡፡

በሕገ ወጥ መንገድ ከአገር የወጡ ልዩ ልዩ ጥንታዊ ቅርሶች በሕጋዊ መንገድ ወደ አገር እንዲመለሱ ላደረጉት አስተዋጽኦም ሽልማት አበረከተላቸው፡፡

የፕሮፌሰር ሪቻርድ ፓንክኽረስት የ50 ዓመት የወርቃማ የአገልግሎት ዘመን በራስ መኰንን አዳራሽ ጥቅምት 16 ቀን 2004 ዓ.ም. በተከበረበት ሥነ ሥርዓት ላይ በክብር እንግድነት ተገኝተው የአክሱም ቅርጽ ያለበትን ሽልማት የሰጡት ፕሮፌሰር ማስረሻ ፈጠነ የዩኒቨርሲቲው የምርምር ምክትል ፕሬዚዳንትና የድኅረ ምረቃ ትምህርት ቤት ዲን ናቸው፡፡ Continue reading “ፕሮፌሰር ሪቻርድ ፓንክኽረስት ተሸለሙ”

Advertisements