አቤ ቶኪቻው አገር ለቅቆ ወጣ !

 

በአዝናኝ የፖለቲካ ጽሁፎቹ የሚታወቀው “አቤ ቶኪቻው” ኢትዮጵያን ለቅቆ የወጣ መሆኑን ለማረጋገጥ ችለናል። አቤ ቶኪቻው ቀድሞ በአውራምባ ታይምስ፣ አሁን ደግሞ በፍትህ ጋዜጣ ላይ በአሽሙር እያዋዛ የህብረተስቡን ብሶት ያቀርብ እንደነበር እና እነዚህን ጽሁፎች በመጽሃፍ መልክ ያሳተማቸው መሆኑ ይታወሳል። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግን በደህንነት ሰራተኞች ማስጠንቀቂያ የደረሰው መሆኑን ገልጿል።ኢህአዴግ በጋዜጠኞች ላይ የሚያደርገውን ሰዶ ማሳደድ ቀጥሎአል ብዙ ጋዜጠኞችም የማስጠንቀቂያ ደብዳቤ እና የቃላት ውርወራ ቢደርስባቸውም ከማንኛቸውም ነገሮች  ቢሆን ከስራችን አንታቀብም ስራችን መረጃን ለህብረተሰቡ ማድረስ ነው ብለው በከፍተኛ ደረጃ በመስራት ላይ ቢገኙም መንግስት ግን ጦርነት ከፍቶባቸዋል አብዛኞቹንም በአሸባሪነት መንፈስ ያለበቂ መረጃ ወደ ቃሊቲ እስር ቤት መወርወሩ ይታወቃል ይህ በእንዲህ እንዳለ አቤ ቶክቻው  “ሽሙጦች “በሚሉት የአጻጻፍ ዘይቤው የህብረተሰብን ልብ የነካ ጽሁፍ ሲሰራ ቆይቶ በአሁን ሰአት ወደ ስደት እንዳመራ ምንጮቻችን ገልጸዋል ።መንግስትም የመገናኛ ብዙሃንን አፍኖ በዕራሱ እጅ የሚንቀሳቀሱትን ብቻ ማሰራት ይፈልጋል ይህ ደግሞ የነጻነት ነጸብራቅ አይደለም እና ጋዜጠኞቻችን  ንጹሃን እና የምንም የሽብር ባለቤቶች አይደሉም ግን በእንደዚህ አይነት የክስ ሁኔታ ተፈርጀው ማየት መንግስት አቋም እንደሌለው ያሳያል

ኢ.ኤም.ኤፍ… (ኢትዮ ሚዲአ ፎረም ) አቤ ቶኪቻውን ካለበት የስደት ስፍራ በስልክ አነጋግሮት ነበር። በነገው እለት (እሁድ) ከአቤ ቶኪቻው ጋር ቃለ ምልልስ ያደርጋል። የምትጠይቁት ነገር ካለ፤ ጥያቄያችሁን ላኩልን። እኛም እናደርሳለን ።አፍሮ አዲስ 

Advertisements
%d bloggers like this:
search previous next tag category expand menu location phone mail time cart zoom edit close