ስዬ አብርሀ ስለ “ኤፈርት” አዳዲስ የዊኪሊክስ መረጃዎች ምን ይላሉ?

በአምባሳደር ዶናልድ ያማሙቶ የተዘጋጀው ምስጢራዊ ሰነድ ማጠቃለያ1. በ1991 ሥልጣን የተቆጣጠረው ገዢው ህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ህወኃት) በጦርነት የተጎዳችውን ትግራይ ኢኮኖሚ መልሶ ለመገንባት የሚውል ትርፍ የሚገኝባቸው ተያያዥ ኩባንያዎች  ለማቋቋም እንደሚቻለው በንቅናቄው ስር የነበሩትን ወታደራዊ ያልሆኑ ንብረቶች ወደገንዘብ እንዲለወጡ አደረገ። ህወኃት ይህን  100 ሚሊዮን ዶላር ያክል የሆነ መነሻም በኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ኢህአዴግ) ውስጥ ላሉት ሦስት አባል  ፓርቲዎች በየክልላቸው ተመሳሳይ ሥራ እንዲፈጽሙበት አከፋፈለው። የኩባንያዎቹ የመጀመሪያ አመሰራረት በፓርቲው ታማኞች የባለቤት ስም ሆኖ ሳለ፤ ግለሰቦች ለራሳቸው ጥቅም ከድርጅቶች ገንዘብ ወጪ እንዳያደርጉ በሚገድበው በኢትዮጵያ ፍትአብሄር ህግ ውስጥ  በሚገኘው የ‹ኤንዶመንት› መመሪያዎች ወደኤፈርት በይፋ የተላለፉ ነበሩ። ምንም እንኳ የኤፈርት ቦርድ ዳይሬክተሮች ከስራቸው  ያሉትን ኩባንያዎች የእያንዳንዳቸውን የገንዘብ አያያዝ ወይንም ፋይናንስ እና ንግድ እቅድ በእቅብ የሚቆጣጠሩ ቢሆንም የኤፈርት የሂሳብ መዝገቦች ግልጽ ስለሆነ የውጪ ግምገማ እንዲቀርቡ የሚገደዱ አይደሉም። ከ1990 መግቢያ አንስቶ ላሉት አስርት ዓመታት ኤፈርት በመላ ትግራይ የገበያ ጥናቶችን ሲደጉም ለበርካታ  የንግድ ተቋማት መነሻ ካፒታል ሲያቀርብ ቆይቷል። ይሁንና ከፍተኛ ትርፍ  የተገኘ ቢሆንም ቅሉ አዳዲስ የኤፈርት ኢንቨስትመንት ፕሮጀክቶች ግን አልተቋቋሙም።  ይህም በህብረተሰቡ ውስጥ ሰፊ ተቀባይነት ያገኘውን ‹ገዢው ፓርቲና አባላቶቹን ለራሳቸው የግል ጥቅም የኢንዶመንቱን ኃብቶች  ይጠቀማሉ› የሚለውን አመለካከት ተዓማኒነት ሰጥቶታል። ወደገንዘብ የተለወጡ የእርዳታ ሃብቶች ኢንዶመንቱን ለመመስረት ውለዋል  2. ከ1987 አንስቶ ከህወኃት እስከተወገዱበት 1993 ድረስ የኤፈርት ዋና ሥራ አስፈፃሚ የነበሩት አቶ ስዬ አብርሃ  (ምስጢራዊው ሰነድ አቶስዬን በምንጭነት መጠቀሙን ቢገልጽም ስማቸው ግን በምስጢር እንዲጠበቅ ያሳስባል)  ከፖለቲካና ኢኮኖሚ ጉዳዮች ኃላፊ ጋር እኤአ በማርች 17ባደረጉት የ2 ሰዓት ውይይት ወቅት የኤፈርትን አመሰራረትና አሰራር ዘርዝረዋል። አቶስዬ እንደገለጹት ህወኃት በ1980ዎቹ ከደርግ መንግስት ጋር ለሚያደርገው  ትግል እንዲረዳውና ለትግራይ ህዝብ እርዳታ ሊያቀርብ እንዲችል ከፍተኛ ዓለም አቀፍ እርዳታ ይበልጡንም ከአሜሪካ ይቀበል ነበር።  ሊገለገልበት የሚችለውን  ወይም ወደትግራይ ሊያጓጉዝ የሚችለውን ምግብና መሰል እርዳታ እንደታቀደው ያውለዋል። የተረፈውን ምግብና እርዳታ ሱዳን ውስጥ  ይሸጠዋል። በትግሉ ማብቂያም ህወኃት ያሉትን ወታደራዊ ቁሶች በኢትዮጵያ ሰራዊት ንብረትነት ሲያካትት ከመቶ በላይ የሚሆኑ የመጓጓዣ መኪናዎችን ለግሉ አቆይቶ የተቀሩ አብዛኞቹ ንብረቶችን ለሽያጭ አዋላቸው። እንደአቶ ስዬ ግምት ህወኃት በ1991 ላይ 100 ሚሊዮን  ዶላር ያህል ከሽያጭ የተገኘ ገንዘብ ነበረው። ይህ ገንዘብ የህወኃት አባላት ንብረት እንዳልሆነ በመረዳትም ፓርቲው ገንዘቡን የጦርነቱ  ወላፈን ሰለባዎች ሆነው ለቆዩት የትግራይ ህዝቦች በቋሚነት የሚጠቀሙበት የእርዳታ መንገድ ሆኖ እንዲውል ወሰነ። ትግራይን መልሶ  ለመገንባት መዋዕለ-ነዋይን ማፍሰስ  3. በመነሻው አካባቢ በትግል ወቅት በጦር ሜዳ የሞቱ ታጋዮች ቤተሰቦችን በቀጥታ ለመርዳት እንዲውል  ለማቋቋም እንደመነሻ መዋዕለ- ንዋይ ሆኖ ነበር።  እንደ አቶ ስዬ ትንታኔ፣ በ1998 ዓ.ም የአቶ ስብሃት ነጋ ከህወኃት ማዕከላዊ ኮሚቴ መወገድ እና የእርሳቸው (የአቶ ስዬ) ከኤፈርት ዋና ስራ-አስፈፃሚነት መነሳት የሚያሳየው በአቶ ስብሐት እና በወ/ሮ አዜብ መስፍን መሃል ያለውን ፍጭት ነው። ፓርቲው የገንዘቡን የተወሰነ ክፍል መድቦ ነበር። ይሁንና በርከት ያለው ገንዘብ የዋለው ግን ለአዳዲስ መስኮች የገቢ ምንጭ የሚሆኑ ከባንያዎችን ከ1983-1987 ድረስ እነዚህ ኩባንያዎች በህወኃት የኢኮኖሚ ጉዳዮች ክፍል ሥር ተዋቅረዋል፡፡  በአቶ ስብሐት ነጋ ይመሩ ነበር። የፓርቲው የውስጥ  ሰዎች ከግል ጥቅማቸው ይበልጥ ለፓርቲው ታማኝነታቸው ያደላሉ ከሚል አመኔታ በመነሳት ኩባንያዎቹ  የተቋቋሙት በግለሰብ የፓርቲ የውስጥ አባላት ባለቤትነት ሥም ነበር። በሌሎች አዋጭ የሆኑ አካባቢያዊ  የንግድ እድሎች ላይ የሚደረጉ የገበያ ጥናቶችን ለመደጎም ደግሞ ተጨማሪ ገንዘብ ይሰጡ ነበር። 4. በ1987 የመከላከያ ሚኒስትርና  የጠቅላይ ሚኒስትር መለስ የረጅም ጊዜ ሚስጥረኛ የሆኑት አቶ ስዬ አብርሃ ለመልሶ ግንባታ የታቀዱትን ተቋማት በኃላፊነት ተረከቡ።  በግለሰቦች ስም ከፍተኛ ሃብት ማስቀመጥ ሊያመጣ የሚችለውን ብክለት በመገንዘብም አቶ ስዬና ህወኃት ለመልሶ ግንባታው ጥረት  ሞግዚት ተቋም እንዲሆን ኤፈርትን መሰረቱ። አቶ ስዬ እሳቸው ስልጣን ከመያዛቸው በፊት ባሉት ጊዜያት የተወሰነ ገንዘብ መጥፋቱን  ወይም መጉደሉን አምነው ዝርዝር ከመስጠት ግን ተቆጥበዋል። ህወኃት ኃብቱን በኢህአዴግ ውስጥ የሚገኙት ሦስት ፓርቲዎች የራሳቸውን ኤንዶመንት ፈንድ እንዲያቋቁሙበት ሰጠ። እነዚህም ኤፈርት ተብሎ የሚጠራው የብአዴን ኤንዶውመንት፣ የደኢህዴን ወንዶ ትሬዲንግ እና የኦህዴድ ዲንሾ ናቸው። (ማስታወሻ፣ ህወኃት ለእነዚህ ኋላ ኢንዶመንት ለሆኑ መልሶ የማቋቋሚያ ፈንዶች ድጋፍ ማድረጉን አቶ ስዬ ቢያረጋግጡም በነዚያ ፈንድ/ኢንዶመንት ተግባራት ውስጥ ግን ቀጥተኛ ተሳትፎ አልነበራቸውም።) 3. በኤፈርት ስር ከተቋቋሙ በኋላ  እያንዳንዱ ኩባንያ ወደ አክሲዮን ኩባንያነት ተለወጠ። አቶ ስዬ እንደሚሉት በ1980ዎቹ የህወኃት ፍላጎት ኤፈርት አገር በቀል ኃብቶችን  የሚጠቀሙና ለትግራይ ህዝብ የሥራ እድል የሚያመጡ አትራፊ ድርጅቶች ጥናት እያደረገ እንዲያቋቁም ነበር። ቀድመው ከተቋቋሙ ድርጅቶች መኃል ለምሳሌ በበፊቱ የእርዳታ አቅርቦት ጊዜ ያገለግሉ የነበሩ መኪናዎችን የሚጠቀመው የትራንስፖርት ኩባንያ፣ ከመቀሌ ወጣ ብሎ  የሚገኘው መሶቦ የሲሚንቶ ፋብሪካ፣ የንግድ ቤት፣ እና ከመቀሌ ወጣ ብሎ የሚገኘውና ትግራይ ውስጥ የሚበቅልን ጥጥ እንደግብአት  የሚጠቀመው አልመዳ ጨርቃጨርቅ ይጠቀሳሉ። የእምነ-በረድ ፋብሪካ፣ የወርቅ ቁፋሮ (ከጋናው አሻንቲ ጎልድ ጋር በሽርክና)፣ እና የኮንስትራክሽን ተቋም ላይ የገበያ ጥናት ተደርጓል። ኤፈርት ድርጅቶችን የሚያቋቁማቸው በመገንባት-መንቀሳቀስ-ማዛወር (Build-Operate-Transfer-BOT) ሞዴል ሲሆን የተቋቋሙትን ድርጅቶች አክሲዮን ለግለሰቦች በማስተላለፍ  ትርፍን ወደ አዲስ የንግድ ተቋማት ያዞራል። ኤፈርት የእያንዳንዱን ኩባንያ የፋይናንስና የንግድ እቅድ የመገምገም ኃላፊነት  አለው። ኤፈርት ከህወኃት ፓርቲዎች በተመረጡ ሥራ አስፈፃሚና የዳይሬክተሮች ቦርድ ቁጥጥር ስር ሆኖ ሳለ አቶ ስዬ እንዳረጋገጡት  እያንዳንዱ ኩባንያ በዘርፉ ከፍተኛ ልምድ ባላቸው ባለሙያዎች የሚመራና የሚንቀሳቀስ ነው። ሥራ አስኪያጆቹ  ዝርዝር የሂሳብ ደብተር እንዲይዙ የሚጠበቅ ሲሆን ዳግም በመዋዕለ-ንዋይ ያልዋለን ትርፍ ግን ለኤፈርት እንዲያስተላልፉ ይጠበቅባቸዋል።  የኤፈርት የሂሳብ ደብተር በፓርቲው ብቻ የሚመረመር ነው። 4. በ1993ቱ የህወኃት ክፍፍል ጊዜ በርካታዎቹ የኤፈርት የቦርድ ዳይሬክተሮች ከስራ አስፈፃሚው ከአቶ ስዬ ጋር ወግነው ከፓርቲው ተወገዱ። ያላበሩት አቶ ስብኃት ነጋ የሥራ አስፈፃሚነት  ቦታውን ያዙ (ማስታወሻ ከ1993 ዓ.ም አንስቶ አቶ ስዬ በኤፈርት ውስጥ ያልነበሩ በመሆኑና አሁን በፖለቲካ ተቃዋሚነት ስለቆሙ  ከ1993 ወዲህ ስላለው የኤፈርት ጉዞ አመለካከታቸው ውስን ወይም ተፅዕኖ ለማሳረፍ የታለመ ይሆናል። ይህም ቢሆን ከፓርቲው  ከፍተኛ አባላት ጋር ካላቸው የረዥም ዘመን ቅርበትና አሁንም በስልጣን ላይ ካሉ ሰዎች ጋር ካላቸው ወዳጅነት አንፃር ከ1993  ወዲህ ስላለው የኤፈርት እንቅስቃሴ የሰጡት ትንተና ተዓማኒ ሊሆን ይቻለዋል።) እንደአቶ ስዬ አገላለጽ አቶ ስብሐት የስራ አስፈፃሚነት ስፍራውን ከወሰዱ በኋላ – ቀድሞ በተጠቀሰው የBOT አካሄድ መሰረት – ሁሉም የኤፈርት ኩባንያዎች ከአክሲዮን ድርጅትነት  ወደኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማሕበርነት ተለውጠው ተመዘገቡ። የኤፈርት ኩባንያዎች ምን ያህል አትራፊ እንደሆኑ ባናውቅም የመንግስት  ጥበቃና የተሰማሩበት ተፈላጊ የሆነ የትራንስፖርት፣ ሲሚንቶና ግንባታ ዘርፍ የኤፈርት ኩባንያዎችን ከፍተኛ ትርፍ እንዳስገኘላቸው  እንገምታለን። በዚህ ጊዜ አቶ ስዬ እንዳረጋገጡት ኤፈርቱ ውስጥ እያሉ የገበያ ጥናት ተደርጎባቸው የነበሩ የንግድ ሥራዎች በቀጣይ  ዓመታቱ እንዳልተቋቋሙና ይህም ትርፍ ለአዳዲስ የትግራይ መልሶ ግንባታ አንቅስቃሴዎች ሳይውል ግን ወደሌላ ጉዳይ መዘዋወሩን የሚጠቁም ነው። 5. አቶ ስዬ በእርግጠኝነት እንዳስቀመጡት የእፈርትና መሰል የኢህአዴግ ፓርቲ ኤንዶመንት ኩባንያዎች ከመንግስት የተፈቀደ የብድር  አቅርቦት ወይ የውጭምንዛሪ፣ የመንግስት ጨረታና ኮንትራት፣ የወደብ ግልጋሎትና የአስመጭና ላኪ ፍቃድ ቅድሚያ ያገኛሉ የሚባለው እውነት መሆኑን ነው። ከዚህም በላይ  ከመንግስት ድርጅቶችም በላይ ልዩ ግልጋሎት ይሰጣቸዋል፣ ቅድሚያ ያገኛሉ ብሎ ይከራከራል። እንደ አቶ ስዬ ትንታኔ፣ በ1998 ዓ.ም የአቶ ስብሃት ነጋ  ከህወኃት ማዕከላዊ ኮሚቴ መወገድ እና የእርሳቸው (የአቶ ስዬ) ከኤፈርት ዋና ስራ-አስፈፃሚነት መነሳት የሚያሳየው በአቶ ስብሐት እና በወ/ሮ አዜብ መስፍን መሃል ያለውን ፍጭት ነው።

Advertisements
%d bloggers like this:
search previous next tag category expand menu location phone mail time cart zoom edit close