የመለስ ዜናዊ ተላላኪዎች ስብሰባና የቦንድ ሽያጭ በሚኒሶታ የሃገር ውስጥ ኢኮኖሚ ውድቀት

ስብሰባው የሚደረግበት ሆቴል
በሃገር ውስጥ የኢኮኖሚ ውድቀት በከፍተኛ የገንዘብ ችጋር ውስጥ የወደቀው የመለስ ዜናዊ አስተዳደር ከዲያስፖራው በዛም በዚህም በሚል ገንዘብ ለመሰብሰብ ሙከራውን ቀጥሏል። በአትላንታ “የዲያስፖራ ረቂቅ ሰነድ” ላይ ለመወያየትና በዛውም ለአባይ ወንዝ ማሰሪያ ቦንድ ሽያጭ ለማካሄድ ያደረጉት ስብሰባ በቆራጥ ኢትዮጵያውያን ትግል እንደከፈባቸው ከስፍራው የደረሰን ዜና ያስረዳል። በተለይ የመለስ መንግስት ለሆቴልና ለቱባ ባለስልጣናቱም የትራንስፖርት ከፍሎ ምንም ሳያገኝ ከአትላንታ መመለሱ ኪሳራ ውስጥ ወድቋል። ይህን የደረሰበትን ኪሳራ በብዛት የትግራይ ተወላጅ የሆኑ የቢዝነስ ሰዎች በሚኖሩበት ዴንቨር ከተማ ተደርጎ (ዴንቨርና አክሱም እህት ከተሞች መሆናቸው ይታወሳል) ለሆቴል ኪራይና ለባለስልጣናቱ ትራንስፖርት የማይተርፍ ገንዘብ ተሰብስቧል። ይህም የወያኔ ባለስልጣናትን ‘ከዲያስፖራው እናፍሰዋለን” ብለው ያለሙትን $$$ ሕልም እንዲሆንባቸው አድርጓል። ይህም የሚያሳየው ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በዲያስፖራው የስርዓቱ አቀንቃኝ የሆኑ የትግራይ ተወላጅ ቢዝነስ ሰዎች ሳይቀሩ አንቀረው እየተፏቸው መሆኑን ነው።
በአምባሳደር ግርማ ብሩ የሚመራው ይህ የአምስት ዓመቱን “የዲያስፖራ ረቂቅ ሰነድ” የመወያየትና ቦንድ የመሸጥ ተግባር ለመቀጠል በአንድ ሳምንት ጊዜ ውስጥ በሚኒሶታ ስብሰባ ተጠርቷል። ነገሩ እንዲህ ነው። ሴንት ፖል ሚኒሶታ የሚገኘው የቅድስት ማርያም ቤተክርስቲያን በአቡነ ጳውሎስ ስም የሚቀደስበት ቦታ ነው። ከዚህ ቤተክርስቲያን ውጭ መድሃኔዓለም እና ኡራኤል ቤተክርስቲያኖች ቢኖሩም ይህ የአምስት ዓመቱ ረቂቅ ሰነድ መጥሪያ ወረቀት የታደለው በቅድስት ማርያም ቤተክርስቲያን ብቻ ነው።
ባለፈው እሁድ ኖቬምበር ሃያ ሰባት በተበተነው የመጥሪያ ወረቀት ለትግራይ ተወላጆች እና ለጥቂት ስር ዓቱን ይደግፋሉ ተብለው ለሚታሰቡ ሰዎች የተሰጠ ሲሆን ዘ-ሐበሻ ጋዜጣን ጨምሮ ለሌሎች ኢትዮጵያውያን የጥሪው ወረቅት አልደረሰም። የዛሬ አመት ተመሳሳይ ስብሰባ ተደርጎ የዘ-ሐበሻ ጋዜጣ አዘጋጅ ወደ ስብሰባው ሊገባ ሲል “ስብሰባው አንተን አይመለከትም” በሚል እንዳይገባ መከልከሉ አይዘነጋም።
በግርማ ብሩ ተላላኪነት የሚመራው ይህ ቡድን ነገ ማምሻውን ሚኒያፖሊስ ይገባሉ ተብሎ ይጠበቃል። በቅርቡ በሚኒሶታ የወያኔ ሰላዮችን ለማጋለጥ እንቅስቃሴ የጀመረው የኢትዮጵያ ወጣቶች ክንድ አምባሳደሩን ኤርፖርት ሄደው የሚቀበሉትን፤ በመኪና የሚያዘዋውሩበትን፤ ራት ወይም ምሳ ይበሉበታል ተብሎ በሚጠበቀው ሬስቶራት የሚያጅቡትን፤ በስብሰባው ላይ ቦንድ በመግዛት የሃዜብን እና የመለስን የባንክ አካውንት የሚያደልቡትን ፎቶ ግራፍ በማንሳት በድረ ገጾች ላይ ለመለጠፍ እንቅስቃሴ መጀመሩን ይህ ክንድ አስታውቋል። ስብሰባው የፊታችን ቅዳሜ ዲሴምበር ሦስት ዳውን ታውን በሚገኘው ሃያት ሆቴል ይደረጋል። በዚህ ወቅት የጥሪው ወረቀት የደረሰው ሁሉ ቦንድ ለመግዛት አስፈላጊውን ነገር ይዞ እንዲገኝ ማስጠንቀቂያ የተጻፈ ሲሆን ከዚህ ቀደም እንደተደረገው ወደ ስብሰባው ለመግባት የጥሪውን ወረቀት የግድ መያዝ አለበት።

ይህ በፎቶ ግራፉ ላይ የምታዩት በሚኒያፖሊስ ዲሴምበር ፫ የመለስ ዜናዊ ተላላኪዎች የሚሰበሰቡበት አዳራሽ ነው። ሰባ አምስት ሺህ ስኩዌር ስፋት ያለው ይህ አዳራሽ እንደፈለገው ሊጠብም ሊሰፋም ይችላል። እዚህ አዳራሽ ላይ አንድ ስብሰባ ለማድረግ በሺዎች የሚቆጠሩ ዶላሮች ያስፈልጋሉ። ስብሰባውን ለሚያካሂዱት አበል፣ የሆቴልማደሪያ፣ የትራንስፖርት፣ ለሚቀጠሩት የውጭ ሃገር ዜጋ ጋርዶች ወጪ ሲታሰብ በግምት ወደ ሃያሺ ዶላር ያወጣሉ። አሳዛኙ ነገር ይህ ገንዘብ ከኢትዮጵያ ሕዝብ ተወስዶ ቢከፈልም በሚኒያፖሊሱ ቦንድ ሽያጭ ይህን ያህል ገንዘብ ማግኘት አይችሉም።
በአጭር ጊዜ ስብሰባው ሊጠራ የቻለበት ምክንያት እጅግ ግልጽ ነው። የሚፈልጉት ሰው ብቻ እንዲገኝላቸው እንዲሁም ተቃዋሚዎች ተደራጅተው ስብሰባውን እንዳያውኩባቸው ሰግተው ነው። አንዳንዶች መሬት ይሰጣችኋል እየተባሉ በስብሰባው ሲገኙ፤ በቅርቡ በቀጥታ የሕወሃት አባላት የሆኑና በዩኒቨርሲቲ ኦፍ ሚኒሶታ ውስጥ በስኮላር ሺፕ እንዲማሩ እየተደረጉ ያሉት ታጋዮች በቅስቀሳ ላይ ሲገኙ፤ በተለይ ደግሞ ለወያኔ መንግስት ገንዘብ በማዘዋወር ስራ (ሃዋላ) ላይ የተሰማሩና ሱቅ ከፍተው እየሰሩ ያሉ የመለስ ዜናዊ ደጋፊዎች በሱቃቸው ውስጥ ሰዎች በስብሰባ ላይ እንዲገኙ መቀስቀስ መጀመራቸውን የተመለከቱ ወገኖች ካሁን ወዲህ በነሱ በኩል ገንዘብ ላለመላክ፣ ላለመገበያየት፣ መወሰናቸውን እየገለጹ ነው።
ስብሰባው የሚደረግበት ቦታ Hyatt Regency Minneapolis
1300 Nicollet Mall,
Minneapolis, Minnesota, 55403
የስብሰባው አስተባባሪዎች ስልክ 763 502 9990 / 214 675 6107 ነው።
Advertisements
%d bloggers like this:
search previous next tag category expand menu location phone mail time cart zoom edit close