ሐሰት የሚጽፉ ጠልሳምያን፤ እውነት የሚጽፉ ኃያላን ናቸው።

“ እንደ እነ እስክንድር ነጋ ያሉ የዘመናችን ጸሀፊዎች የህዝቡን ጉዳትና ያረመኔዎችን ጭካኔ ለዓለም እያጋለጡ የሚመሰክሩት በጽሁፋችው ብቻ አይደለም። በኃያሉ ኪነታቸው አረመኔዎች በህዝቡ ላይ ያፈጠጡ ዓይኖቻቸውን፡ ያገጠጡትን ጥርሶቻቸውን፡ ያንጨፈረሩትን ጥፍሮቻቸውን ከሚያሰቃዩት ሕዝብ ላይ ነቅለው ወደራሳቸው እንዲያዞሩ በማድረግ ጭምር ነው። ኃያላን ጸሀፊዎች የአረመኔዎችን ጭካኔ ከህዝቡ ወደራሳቸው በመሳብ እየረኩ: አረመኔዎች ስግብግብ ስሜታቸውን ለማርካት ከመጣደፋቸው በቀር ሀፍረተ ሥጋዋን መሽፈን የተሳናት ፍየል በመሆናቸው ስለግብዝነታቸው ያለቅሱላቸዋል።
እውነተኞች ጸሀፊዎች የግድያ ተልእኮውን ለመፈጸም መድፍና መትረየስ ታጥቆ ከተሰለፈ ሠራዊት ይልቅ፤ ሕሊናቸው የሕይወት የሽምግልና የፍቅር የእርቅና የጥበብ ምንጭ በመሆኑ መጽሐፈ ቅዳሴያችን ሃያላን አላቸው። አረመኔዎች ሰውን ከሚያስሩበት ሰንሰለት: ከሚገሉበት ጥይት ዕንዲላቀቁ: ተበዳዮችም ከአረመኔዎች ወገኖቻቸው ሰንሰለትና ጥይት ነጻ እንዲወጡ ለሁሉም እኩል ከማሰብ በቀር እንደ እነ እስክንድር ነጋ ያሉ ጸሀፊዎች በሚዛን የለሽ ስሜት ብዕራቸውን በሰው ላይ እያነጣጥሩም። “
 ቀሲስ አስተሰርየ-ጽጌ
Advertisements
%d bloggers like this:
search previous next tag category expand menu location phone mail time cart zoom edit close