የዘ-ሐበሻ ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ ከወያኔ ስብሰባ በፖሊስ ተባረረ

ኮፍያ ያደረገው የዘ-ሐበሻ ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ ሔኖክ ዓለማየሁ ሲሆን፤ ሱፍ አድርጎ የቆመው ደግሞ በሚኒያፖሊስ አካባቢ የወያኔ ቀንደኛ አስተባባሪ ነው። የዘ-ሐበሻ ጋዜጣ አዘጋጅ ከስብሰባው እንዲባረር ሲሯሯጡ ከነበሩት አስተባባሪዎች መካከል አንዱ ነው።

ኮፍያ ያደረገው የዘ-ሐበሻ ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ ሔኖክ ዓለማየሁ ሲሆን፤ ሱፍ አድርጎ የቆመው ደግሞ በሚኒያፖሊስ አካባቢ የወያኔ ቀንደኛ አስተባባሪ ነው። የዘ-ሐበሻ ጋዜጣ አዘጋጅ ከስብሰባው እንዲባረር ሲሯሯጡ ከነበሩት አስተባባሪዎች መካከል አንዱ ነው።

እየተደረገ ባለው የወያኔ ተላላኪዎች እና የቦንድ ሽያጭ ስብሰባ ላይ ቁጥራቸው ከ30 የማይበልጡ ሱማሌዎች እና ከ10 የማይበልጡ ኢትዮጵያውያን በተገኙበት ስብሰባ ላይ የዘ-ሐበሻ ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ ሔኖክ ዓለማየሁ በስብሰባው እንዲገባ ቢፈቀድለትም፤ ጥቂት እንደተቀመጠ ፎቶ ግራፍ ለማንሳት ሞክረሃል በሚል ከስብሰባው አዳራሽ በሱማሌዎች እና በአንድ የትግራይ ተወላጅ ወጣት እንደዚሁም በስብሰባው ላይ በነበሩት ሁለት ፖሊሶች ተገዶ እንዲወጣ ተደረገ።
“እኛ ፎቶ ግራፍ ማንሳት መከለከል የለብንም፤ ምክንያቱም እዛ ጋር ፎቶ የሚያነሳውን ሰው ሳትከለክል እኛን የመከልከል መብት የለህም” ሲል የዘ-ሐበሻ ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ ሔኖክ ዓለማየሁ ቢጠይቅም ስብሰባው ላይ ስሙን ጽፎ ያስገባውና ሲልቨር ሱፍ ያደረገው የትግረኛ ቋንቋ ተናጋሪው አስተባባሪ “እሱ የኛ ሰው ነው ፎቶ ግራፍ ማንሳት ይችላል፤ እናንተ ግን በምንም ምክንያት ፎቶ ግራፍ ማንሳት አትችሉም” ሲል ጮኸ።
በዚህ መካከል ስብሰባው ተቋረጠ። ጭቅጭቁ እያየለ ሲመጣ የመለስ ዜናዊ መል ዕክተኛ አቶ ግርማ ብሩ ሳይቀሩ የነበረውን ግርግር መመለከት ጀመሩ። “እርሱ ፎቶ ግራፍ ማንሳቱን ካላቆመ እኛም አናቆምም” ሲል ሔኖክ ተናገረ። ድሮም መንፈሳቸውን መቆጣጠር የማይችሉት የወያኔ ተላላኪዎች ወደ ውጭ ወዳስቀመጧቸው ሁለት የሚኒያፖሊስ ፖሊሶች ጋር በመሄድ “ስብሰባውን እየረበሹ ነው አስወጡልኝ” ሲል ነገራቸው። ፖሊሶቹን ተከትለው የአምባሳደሩ ጋርዶችና ሱማሌዎች እና የወያኔ ፍርፋሪ ናፋቂዎች የዘ-ሐበሻ ጋዜጣ አዘጋጅን እንደዚሁም በሚኒያፖሊስ አካባቢ ከፍተኛ የፖለቲካ እንቅስቃሴ በማድረግ የምትታወቀውን ሶስና የተባለችውን ወጣት እንዲባረሩ አድርገዋል።
በተለይ ሔኖክ ከስብሰባው ሲወጣ አምባሳደሩ እንዲሰሙት ጮክ ብሎ በመናገር “ሃገር ቤትም ፈርታችሁ እዚህም ፈርታችሁ እንዴት ይሆናል? ይህ ስብሰባ የኢትዮጵያውያን ነው ከተባለ የመሰብሰብና የመጠየቅ መብት አለን። በኢትዮጵያዊነታችን በሱማሌ እጅ እንድነነካ አድርጋችሁ አዋርዳችሁናል” ሲል ተናግሯል። የበር መዝጋቢውም “ማን እንደሆንክ እናውቅሃለን፤ እድሉን ሰጥተን ብናስገባህም ልትበጠብጥ ነው የመጣኸው ውጣ” ተብሏል።
“በጋዜጠኝነቴ ልዘግብ ልጠይቅ ነው የመጣሁትና ዕድሉ ሊሰጠኝ ይገባል” ብልም ፖሊሶቹ “ይሄ የነሱ private event በመሆኑ ምንም ልናረግ አንችልም፤ የናንተን ሃገር ፖሊቲካም አናውቅም ስለዚህ አዳራሹን ለቀህ ውጣ ሲሉ” ከስብሰባው እንዲወጣ የሆቴሉ በር ድረስ ሸኝተውታል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ በመቶዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን በሚኒያፖሊስ ከፍተኛ በረዶ እየወረደባቸው ተቃውሟቸውን ሲያሰሙ ውለዋል።
ስለ ሚኒያፖሊሱ ስብሰባ በፎቶ ግራፍ የተደገፈ ዘገባ ይዘን እንቀርባለን።
Advertisements
%d bloggers like this:
search previous next tag category expand menu location phone mail time cart zoom edit close