ንስሀዬ፤ እኔ እንደ መለስ ዜናዊ

clik here on pdf Zelalem Gebre
ሉሉ ከበደ
የሰው ልጅ በዓለም ላይ ከተፈጠረ ጊዜ ጀምሮ እስካሁን አለንበት ዘመን ድረስ፤ አዝጋሚ የሆነ የአካልና
የአእምሮ ለውጥ እያመጣ ሳለ፤ ዘመናዊ ልጣኔ በድንገት ብቅ ባለበት የቅርብ ዘመን ጀምሮ ባስተሳሰብ ረገድ
እያሳየ ያለው እድገት የፈጠነ ይምሰል እንጂ፤ ስልጣኔው ከጥግ እጥግ የዓለም ክፍል እኩል ስላልተጀመረና
ስላልተስፋፋ፤ ሰው በምድር ላይ ከኖረ ሶስት አራት ሚሊዮን ዓመታት በሗላም፤ አሁን ላይ ቆመን ስናየው
ከሚሊዮን ዓመታት በፊት የነበረ አኗኗር በአንዱ የዓለም ጥግ፤ ለማመን የሚያዳግት ስልጣኔ በሌላው
የዓለም ጥግ አለ። ዛሬም ቅጠላቅጠል እየበጠሰ፤ ስራስር እየማሰ፤ እያደነ፤ እርቃኑን የሚኖር የሰው ልጅ
አለ። ጥቂቱ ደግሞ ምድርን ለቆ፤ በመንኮራኩር ሌላ አካል ላይ አርፎ፤ ሌላ መኖሪያ መሆን የምትችል ዓለም
በመፈለግ ላይ ያለ አለ።
በአስተዳደርም ረገድ እድገቱ ተመሳሳይ ነው። ጥንታዊነቱና ዘመናዊነቱ አሁንም ጎንለጎን አሉ። በነገድ፤
በጎሳ፤ በንጉስ በሹም በአንድሰው አምልኮ የሚተዳደሩ አሉ። ስልጣን ላይ ከወጡ በሗላ ገዢነት ከፈጣሪ ለነሱ
ብቻ የተሰጠ አድርገው የሚያምኑና ዘለዓለማዊ ገዢ መሆናቸውን የሚያረጋግጡ፤ ዘመናዊው ስልጣኔ
አእምሮአቸውን ያልዳሰሰው፤ እየገደሉ መግዛት እንዳለባቸው የሚያመኑ ሰዎች አሉ። ሌሎች ደግሞ
የመረጣቸው ሕዝብ የፈቀደላቸውን የስልጣን ጊዜ ጨርሰው ተራውን ለሌላ ለቀው ወደ ግል ኑሮአቸው
የሚመለሱ አሉ። እንግዲህ ሰው ከሚሊዮን ዓመታት እድሜው በሗላ በዓለም ላይ ሰልጥኖም ደንቁሮም አብሮ
እየተተራመሰባት ነው።
ስልጣኔ የገባው ወገን ስልጣን ላይ የሙጢኝ የሚለውን ሰው “ስልጣኑን ልቀቅ፤ ተራውን ለሌሎች ስጥ” እያለ
ይጮሀል። ያልሰለጠነውም፡ ንጉስ ወይም መሪ “ስልጣኔን ሊቀሙ ነው፤ እያለ በስልጣኑ የመጣውን ጥቅምና
ዝና ሊያጣ መሆኑ እያባነነው፤ ጦር ሰራዊት እያዘዘ፤ ፊቱ የቆመውን ሁሉ ያስፈጃል። ይፈጃል። ይገላል”
ገዳዩም አይፈረድበትም። አእምሮው ያለበት የስልጣኔ ደረጃ ነው። ተቃዋሚውንም የሚያስጮኸው አእምሮው
ያለበት የእድገት ደረጃ ነው። እነዚህ ሁለቱ ወገኖች ሊስማሙ የሚችሉት የሰለጠነው መልሶ ከደነቆረ፤ ወይም
የደነቆረው ቶሎ መሰልጠን ከቻለ ነው። የዚህ ሁሉ ችግር መንስኤው የሁሉም እኩል አለመሰልጠን ነው።
እዚህ ላይ የተቃወመ ሁሉ ስልጡን ነው ማለትም አይደለም። የስልጣንና የጥቅም ረሀብ ያናወዘውም ስልጣን
ላይ ለመቆናጠጥ አጋጣሚ ቢያገኝ ሊቃወም ይችላል። ስልጡን የምንለው በመሪነት ደረጃ ተሰይሞ ህግ
የፈቀደለትን ጊዜ ሲጨርስ አመስግኖ ወደ ግል ህይወቱ ለመሄድ ወኔውም ብቃቱም ያለውን ዜጋ ነው።
ይኸን ከላይ ለንስሀዬ እንደመግቢያ ያስቀመጥኩትን ሀሳብ ያነሳሁበት ምክንያት እኔና እንደኔ ስልጣን ላይ
የሙጢኝ የሚሉትን ሁሉ ካልሰለጠነው የሰው ልጅ ክፍል እንድትቆጥሩና አገር ‘’በ አንድሰው የበላይነት
ዘለዓለም አይመራም። ዜጎች በሀገራቸው አስተዳደር የመሳተፍ እድል አግኝተው እየተፈራረቁ አገራቸውን
ያገልግሉ።” የሚሉትን ሁሉ ከሰለጠነው የሰው ልጅ ወገን እንድትቆጥሩ ነው።
ባልታሰበ ሁኔታና አጋጣሚ ማለት ይቻላል ሕሊናዬ ተለውጧል። አስተሳሰቤ ተቀይሯል። እስካሁን
የተጓዝኩባቸው መንገዶች በስህተት የተሞሉ መሆናቸው ድንገት ሳላስበው ተከስቶልኛል። ንስህ ልገባ
የኢትዮጵያን ህዝብ ይቅርታ ልጠይቅ ከዚያም አልፎ በሀገርና በህዝብ ላይ ለፈጸምኩት ጥፋት ለፍርድ
ለመቅረብ ራሴን አዘጋጅቻለሁ።
ከሁሉ በፊት ግን እስካሁን በህዝብና በሀገር ላይ እያደረስኩ ያለሁትን በደል ከብዙ በጥቂቱ ልናዘዘው።
እታገላለሁ ብየ ወደ በረሀ ከገባሁበት ዓመት ጀምሮ ከኢትዮጵያ ታሪካዊ ጠላቶች በሙሉ ጋር
ተባብሬአለሁ። ሰርቻለሁ። ሶማሊያ ኢትዮጵያን በወረረች ወቅት በምክር በሀሳብ እነሱን አሸናፊ ያደርጋል
ባልኩት መንገድ ሁሉ ረድቻለሁ። እነሱም ረድተውኛል። ሱዳን ከኢትዮጵያ አለኝ የሚለውን የግዛት ጥያቄPage 2 of 4
ያለምንም ቅድመ ሁኔታ እንደምንመልሰት አረጋግጨለታለሁ። በትግሉ ወቅት ሙሉ ድጋፉን ስለሰጠን
በገባሁት ቃል መሰረት 1600 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለውን ግዛት አስረክቤዋለሁ። በስልጣናችን። ሻዕቢያ
ኤርትራን እንዲገነጥል እስከመጨረሻው የትግራይን ልጆች በእሳቱ ውስጥ አገፋፍጨለታለሁ። ሰላሳ ዓመት
ታግሎ ያልተሳካለትን በትግራይ ልጆች ደም በአጭር ጊዜ እንዲገነጠል አድርጌአለሁ።
ኢትዮጵያን ሐገራችን ብለው አንባገነናዊ ስርአት እንዲወገድና ዲሞክራሲያዊ ስርዓት እንዲገነባ ትግል
የጀመሩ የትግራይ ታጋዮችን ሁሉ፤ ከሻእቢያ ጋር በመመሳጠር፤ የቻልኩትን አስገድዬ፤ ያመለጡት
አምልጠው፤ በሻእቢያ እርዳታና ድጋፍ እኔ በህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ግንባር ውስጥ የበላይ ሆኘ በመቆጣጠር፤
በጓደኞቼም ላይ ሁሉ ክህደትን ፈጽሜአለሁ። ባላሰቡት ሁኔታና ጊዜ የሚቃወሙኝን ሁሉ አስመትቻለሁ።
አስወግጃለሁ።
በትግሉ ወቅት የትግራይ ህዝብ እንዲሸፍት ለማድረግ፤ ለዓላማዬ ግብ መምቻ እንዲሆነኝ፤ ደርግ በህዝብ ላይ
አደጋ ሊያደርስ የሚያስችለውን አጋጣሚ እያጠናሁ፤ እያቀድኩ፤ ሰራዊታችን ቤተክርስቲያን አካባቢ መሽጎ
ተኩስ እንዲከፍት በማድረግ፤ በገበያ ቀን ገበያ አካባቢ እንዲንቀሳቀስ (አውዚን)፤ ደርግ ለጠላት ብሎ
የተኮሰው ሰላማዊ ዜጎችን አንዲገል በማድረግ፤ የትግራይ ህዝብ በሽፍትነት ወደ ትግሉ እንዲቀላቀል
አድርጌአለሁ። ተሳክቶልኛልም።
በተቆጣጠርናቸው አካባቢዎች ድርቅና ረሀብ በተከሰተ ቁጥር፤ የውሸት አሀዝና መረጃ እያቀረብኩ ከለጋሾች
ከፍ ያለ ገንዘብና እርዳታ እንዲገኝ፤ ከረጢት ባሸዋ እየሞላሁ ፤ እየደረደርኩ ፤ ለጋሾች እንዲገዙ
አድርጌአለሁ። በሚገኘው ገንዘብ ሕዝቡ እየሞተ ለውጊያ የምንጠቀምበትን ነገሮች እየገዛሁ ስራላይ
አውያለሁ።
ባጋጣሚም ድል አድርጌ ሁሉን ከተቆጣጠርኩ በሗላ፤ የሀገሩን ሉዓላዊነት ለመጠበቅ ይዋጋ እንደነበረ ልቤ
እያወቀ፤ ሀያል ክንዱንና ጀግንነቱን አጣጥሜ እያወኩ፤ የታሪክ አጋጣሚ የዘመን ቀውስ ፈጠረና፤ የኢትዮጵያ
ጦር ሰራዊት በኛ ተሸንፎ ሳይሆን፤ የራሱ የውስጥ አስተዳደርና አመራር ጥሎት፤ ትጥቁን አውርዶ፤ ባዶ
እጁን የቆመውን ሰራዊት አሸነፍኩ ብዬ፤ እንዲበተን አድርጌ፤ አእላፍ ቤተሰቦቹን ለረሀብ ዳርጌአለሁ። ሀገር
በኔዘር የበላይነት ትገዛ በሚለው ደካማ አቋሜ ምክንያት ጦር ሰራዊቱንም ፖሊሱንም ሁሉ በትግራይ
ታጋዮች የበላይነት በቁጥርም ብዛት፡ ባመራርም ደረጃ በሽፍታ ቡድን ስር እንዲሆን አድርጌአለሁ።
ይህንንም ሳደርግ በቀላሉ እንዲታዘዘኝና የተቃወመኝን ሁሉ በቀላሉ ለማጥፋት እንዲያስችለኝ በማስላት
ነው። ህዝቡን ለመቆጣጠር ማናቸውንም እርምጃ መውሰድ እንዲያስችለኝ ነው። ስህተቴ ሳይሆን እብደቴ
መሆኑ የገባኝ አሁን ነው።
በህብረተሰቡም ውስጥ ደግ ነገር እያደረኩ አይደለም። እያንዳንዱ ሰው ምን ይላል? ምን ያወራል ምን
ያሴራል? አያልኩ፡ እንደሸረሪት ድር በመላ ህዝቡ ውስጥ ባጠላለፍኩት የስለላና የመረጃ መረብ እያንዳንዱ
ሰው ቤት ውስጥ ገብቻለሁ። ያስፈራኝን እቀስፋለሁ፤ አስቀስፋለሁ። የገዢ እንጂ የተገዢ ክፉ እንደሌለ
የተረዳሁት ዛሬ በድንገት ነው። ሕዝብን እየፈሩት አስተዳድርሀለሁ ከማለት አስገብርሀለሁ ቢሉት የሚሻል
ይመሰለኛል። ለምንድነው ይህንን የዋህ ህዝብ፤ ለራሱ የማያውቅበት ህዝብ አስገብሬ ላሰቃየው የወሰንኩት?
አጼሚኒሊክ ቤተመንግስት ከተቆናጠጥኩ በሗላ የባእዳንን ምክርና መመሪያ እየተቀበልኩ፤ ነጻ ገበያን
አስፋፋለሁ በሚል ፈሊጥ፤ ኢትዮጵያዊ ርህራሄና ግንዛቤ በጎደለው የብቀላ መንፈስ፤ ዜጎችን በግፍና በገፍ
ከየድርጅቱ ከየመስሪያ ቤቱ ከስራ እያፈናፈቀልኩ ፤ እያስወጣሁ፤ የብዙዎችን ትዳር አጨልሜአለሁ።
የብዙዎችን ቤት አፍርሻለሁ። ቤተሰብ በትኛለሁ። የእናቶቻቸውን እቅፍ የልጠገቡ ህጻናት ተርበው
በየመንገዱ ላይ እንዲለምኑ አድርጌአለሁ።
በሌላም አጋጣሚ አእላፍ ኢትዮጵያውያን ጀግኖች ከፍ አድርገው የሚያውለበልቧትን፤ ሀገሪቱን ሊወር የመጣ

ጠላት ፊት ቆመው በጀግንነት የሚዋጉላትን የድል ብርታት የሆነችውን ባንዲራ “ጨርቅ” ብየ ማጣጣሌ፤
የራሴን ዝቅተኝነትና የታሪክ ድህነት፤ የራሴን የሀገር ፍቅር እርዛት መግለጼ መሆኑ የገባኝ አሁን ነው።Page 3 of 4
ሌላም ጊዜ በተናገርኩት አጋጣሚ “የትግራይ ህዝብ ጨርቅ አይደለም” በማለት ስናገር ለቀረው የኢትዮጵያ
ህዝብ በተሳከረ ህሊና ባሳየሁት የንቀት አመለካከት የራሴን ወራዳ በህሪና ትንሽነት፤ የውስጤን ባዶነት
እንዳሳየሁ የተረዳሁት አሁን በድንገት ነው።
ከሁሉም በላይ ይዤ በተነሳሁት መሰሪ እምነት መሰረት፤ ኢትዮጵያውያን ተስማምተው እንዳይኖሩ፤
አንዳቸው ላንዳቸው ጠላት እንዲሆኑ፤ እንዲፈራሩ፤ እንዲጠራጠሩ፤ እንዲጣሉ፤ ለማድረግ የምሸርበውን ደባ
ሁሉ ማቆም ባለመቻሌ፤ ሕሊናዬ ከቁጥጥሬ ውጭ ሁኖ ዛሬ በቃህ ብሎኛል። ያፋጀሁትን የፈጀሁትን ሁሉ
ይቅርታ እለምናለሁ።
የሀገሪቱን ሀብት እየዘረፍኩ፤ እያዘረፍኩ፤ ትግራይን አልምቼና ገንብቹ፤ ሌላውን የሀገሪቱ ክፍል አደህይቹ፤
አጣልቼ፤ ክልሌን በሀብትም በጉልበትም አደርጅቼ፤ አዲስ ባንዲራ ትግራይ ላይ ተክዬ፤ ዙሪያዬን በጦር
ከብቤ፤ አንዲት ሀብታም ደሴት ፈጥሬ፤ ነጻነት አውጄ፤ ዘለዓለማዊ ገዢ እሆናለሁ። የቀረው ኢትዮጵያዊ
በድህነት በጦርነት በረሀብ እየተተራመሰ፤ ለማየት ያለኝን ህልም እውን አደርጋለሁ። ከሽፍትነት ዘመን
ጀምሮ የድርጅትም፤ የሀገርም፤ የግለሰብም ንብረትና ሀብት እየቀማሁ እየዘረፍኩ በሀገርም በውጭም
ደብቄአለሁ። አከማችቻለሁ። የስርቆት ተግባሬ እጅ ከፍንጅ በሚያዝበትም አጋጣሚ ለምሳሌ አስራስድስት
ሚሊዮን ያሜሪካን ዶላር የሚያወጣ የወርቅ ክምችት ከብሄራዊ ባንክ ሳሰርቅ፤ አስር ሺህ ቶን ቡና
ከተቀመጠበት መጋዘን ሳሰርቅ፤ ጉምጉም ያሉትን ሁሉ በማስፈራራት ዝም አሰኝቻለሁ። ለዚህ ሁሉ
የኢትዮጵያ ህዝብ ብቻ ሳይሆን እግዚአብሄርም ይቅር እንዲለኝ እለምነዋለሁ።
የኢትዮጵያን ህዝብ ክብር በመድፈር፤ የሀገሪቱን ሉዓላዊነት በተደጋጋሚ በማስደፈር፤ ግዛቷን ለባእድ
አሳልፎ በመስጠት ረገድ፤ አንድሺህ ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለውን የኢትዮጵያ ግዛት በትግሉ ወቅት
ለተደረገልን እገዛና ድጋፍ፤ እንደክፍያ ለሱዳን መንግስት ቃል በገባሁት መሰረት በስልጣኔ ሰጥቻለሁ።
ይህንንም ሳደርግ፤ የኢትዮጵያ ህዝብ ቢቃወም በመግደል እንደማንበረክከው በመተማመን ነው። ሕዝቡ
የጦር መሳሪያ ቢኖረው ኖሮ ይሕን ያሕል ድፍፈረት አይኖረኝም ነበር ። ጠመንጃ ያለው በጄ ነው። ሕዝብ
ባዶ አጁን ስላለና ለመቃወም ስላልተደራጀ እንደፈለኩ ሳደርግ ኖሬአለሁ።
የሀገሪቱን ለም የእርሻ መሬት በራሴ ፍላጎትና ውሳኔ፤ በተጥደፈደፈ ሁኔታ በርካሽ ከሀምሳ አስከ መቶ ዓመት
በሚደርስ ኮንትራት እየተዋዋልኩ፤ ከህዝቡ ሳልማከር የምሸጠው፤ በውስጤ ያለው፤ ሴጣናዊ መንፈስ
እየመራኝ፤ “ሀገራቸውንም ለባእዳን ሽጥባቸው፤ እነሱንም ከፋፍላቸው፤ አባላቸው፤ ባእዳኑን ቶሎ ቶሎ ብለህ
አቆናጣቸው፤ መንግስታቶቻው ያንተው አጋርና ደጋፊ ይሆናሉ። በጦርም በገንዘብም በዲፕሎማሲም ከጎንህ
ይቆማሉ። ዜጎቻቸውን እያመጡ ስለሚያሰፍሩ ፤ መሬቱን ስለሚያርሱ ፤ ያንተን ሰዎች የጉልበት ባሪያ
አድርገው ሕዝባቸውን ስለሚመግቡ፤ የራሳቸውን ዜጎች እያመጡ ጥሩ ጥሩውን ስራ ለነሱ ስለሚሰጧቸው
ያንተን ውለታ ለመመለስ ህዝቡን አብረውህ በመርገጥ ይረዱሀል። ብትፈልግ ሀገሪቱን እስከመጨረሻው
ትገዛለህ። ከፈለክም የትግራይን መንግስት አቋቁመህ እነዚህን አባልተህ ባእዳኑ እራሳቸውን እንዲከላከሉ
መክረህ ትሄዳለህ” የሚለኝ እርኩስ መንፈስ መሆኑን የተረዳሁት አሁን ነው።
ሀገራቸውንና ህዝባቸውን ከልብ የሚወዱ፤ መልካም ራእይ መልካም መኞት ያላቸው ዜጎች በፖለቲካ
ድርጅቶች ተሰባስበው፤ በሀገራቸው የፖለቲካ ህይወት ያስተዳደር ስርዓት፤ ለመሪነት እድል የሚሹ፤
በህዝቡም ዘንድ ከኔ ድርጅት፡ ከኔ ቡድን የበለጠ፤ እጅግ እጅግ የመጠቀ ቅቡልነትና ተአማኒነት፤ ከበሬታ፤
ፍቅር ያላቸውን ግለሰቦችና ድርጅቶች፤ ካሁን በፊት በምርጫ የጣሉኝንም ሆነ ሊጥሉኝ የሚችሉትን ሁሉ፤
አፋጃቸዋለሁ። ሕሊናቸውን ለጥቅም የሚሸጡ ከንቱ ወንድሞቻቸውን በገንዘብ እየገዛሁ፤ እያደራጀሁ፤
የሚፈልጉትን እያደረኩላቸው፤ የምፈልገውን እያደረጉልኝ እዚህ ደርሰናል። ሰርገው እየገቧቸው አገር
ወዳዶችን እንዲበጠብጡልኝ አደርጋለሁ። ለሀገራቸው ጥሩ ራእይ ያላቸውን፤ ያወቁ የበቁ የተማሩ
የተመራመሩ ዜጎች የተሰባሰቡባቸውን የፖለቲካ ድርጅቶች በንዘብ በምገዛቸው መሆዶ ወንድሞቻቸው
ትርምስምሳቸውን ሳወጣ ኖሬአለሁ። ይህች አገር ስንዴና እንክርዳዱ እኩል የበቀሉባት ምድር ነች። እራሴን
ከእንክርዳዱ ቆጥሬ። የሚመኙትን ነገር ካገኙ ማናቸውንም ወንጀል በሀገርና በህዝብ ላይ መፈጸም የሚችሉ
ልበ ድንጋይ ሰዎች ኢትዮጵያ ሞልቷቷል። እራሳቸውን በእሳት አቃጥለው የሚሞቱላት ጀግኖች እንዳሏትPage 4 of 4
ሁሉ። ኢትዮጵያ አጥፊዋንም አልሚዋንም በማህጸኗ የተሸከመች ሀገር ነች። አዝንላታለሁ። ፋሺሽት ኢጣሊያ
ሀገሪቱን በወረረ ዘመን ፤ ከጠላት ሹመትና ድርጎ ስላገኙ ብቻ! “የጣሊያን መንግስት ደግ ነው። ልማት
ያውቃል። የሸፈታችሁ ግቡ።” እያሉ ይሰብኩ፤ አርበኞችን ይወጉ የነበሩ ሰዎች መኖራቸውን ማስታወስ
ያስፈልጋል። የነዚያ ሰዎች ልጆችና የልጅ ልጆች አሁንም ካያቶቻቸው ተፈጥሮ ጋር መኖራቸውን መዘንጋት
አያሻም። አካሏን ለሽያጭ እንዳዘጋጀች ሴትኛ አዳሪ፤ ክብራቸውን ህሊናቸውን ለችርቻሮ የሚያቀርቡ፤
ከምሁር እስከ ለፍቶ አደር፤ ከልጅ እስከ አዋቂ፤ በገፍ አግኝቻቸዋለሁ። ርካሽ ዜጎች ናቸው። ለጊዜያዊ
ጥቅምና ጉርሻ ሀገርና ወገን ያስጠቃሉ። እንደውሻ የምጥልላቸውን ትርፍራፊ እየለቃቀሙ፡ እኔ የምለውን
እያሉ ሲከተሉኝ የከረሙ ዶክተሮች፤ ፕሮፌሰሮች፤ ምሁር ተብዬዎች ሁሉ አብረውኝ ሲዋሹ፤ ሲሰርቁ ኖረው
ኖረው አሁን እኔ ወደ እውነቱ ስመለስ እነሱ ወደየት ይሆን የሚሄዱት? የኢትዮጵያ ህዝብ እነዚህን
የትውልድ እብቆች እያነፈሰ እያንገዋለለ ወደ ዳር ማስቀመጥ አለበት። እኔን ጨምሮ።
ለጊዜው ይህን ካልኩ ይብቃኛና ከዚህ በመቀጠል አሁን ያለው አቋሜን ባጭሩ አስቀምጣለሁ።
ባንድ ወር ጊዜ ውስጥ ጊዜያዊ የሽግግር መንግስት ባስቸኳይ እንዲዋቀርና ስልጣኑን እ

ንዲረከበኝ
እጠይቃለሁ።
ካንድ ወር በሗላ ይህ አሁን ያለው ምክር ቤትና መንግስት ይፈርሳል። የኢትዮጵያ ህዝብ ያልፈቀዳቸው
ተቋማት ሁሉ ከመከላከያው ጀምሮ ፈርሰው እንደ ህዝቡ ውሳኔና ፍላጎት ተተኪው በህዝብ የሚመረጥ
መንግስት ባዲስ ሊያደራጃቸው ይችላል። እያንዳንዳችን እንደየጥፋታችን ክብደትና እንደሀላፊነታችን መጠን
ለፍርድ ለመቅረብ እንድንዘጋጅ አሳስባለሁ።
የኢትዮጵያ ህዝብ ከፈቀደልኝ እስካሁን ያሳለፍናቸውን የኢትዮጵያን ህዝብ ጥቅምና ደህንነት የሚጻረሩ
ውሳኔዎችን በመቀልበስ፤ በዘር ያዋቀርናቸውን ክልሎች ከማፍረስ፤ እስከ የተዘረፈ የግለሰብ ፤ የህዝብ፤ የሀገር
ሀብቶችን መመለስ፤ በትግራይ ልማት ድርጅት ስም በሀገር ውስጥም ሆነ በውጭ የተደበቁ፤ ከጥሬ ገንዘብ
እስከ ተንቀሳቃሽና ቋሚ ንብረት የመመለሱን ተግባር ባራት ወራት ውስጥ አከናውናለሁ። እስካሁን የተበላሹ
ነገሮችን ሁሉ የማስተካከሉን ስራ ከህዝቡና ህዝቡ ከወከለው መንግስት ጋር በመተባበር የማስተካከሉን ስራ
እመራለሁ። ባለፉት ሀያ ዓመታት ውስጥ በሰራሁት ስራ እየተጸጸትኩ አባሪዎቼ በሙሉ አብረን ለፍርድ
እንድንቀርብ በኢትዮጵያ ሕዝብ ፊት ቃል እገባለሁ። እስካሁን ለበደልኩት በደልና በሀገር ላይ ላደረስኩት
ጥፋት የኢትዮጵያን ህዝብ ይቅርታ እጠይቃለሁ።
ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!
መለስ ዜናዊ

ለትችትና ለእርምት lkebede10@gmail.com

Advertisements
%d bloggers like this:
search previous next tag category expand menu location phone mail time cart zoom edit close