ኢትዮጵያ በዊኪሊክስ ፋይሎች (ክፍል ሁለት)

Ethiopia under wikiliks file list part 2 click here pdf

ኢትዮጵያ በዊኪሊክስ ፋይሎች (ክፍል ሁለት)
በአቢይ አፈወርቅ
የወቅቱ ገናና ቃል ‘ሽብር’ ሆኗል። ሹማምንቱ ሳይጠሩት አያድሩም። ህዝቡም ሲያስበው ውሎ
ያድራል… ያልተሸበረ ማን አለ?” ያሰኛል።
እውነት ነው ህዝቡ ተሸብሯል። እንግዳውን ቤቱ ለማሳረፍ ተሳቋል። መኪናውን ለሰው ማዋስ
የማይታሰብ ነገር ሆኗል።… በዚህ ዘመን ‘ሪፖርት አላደረክም’ በሚል በከባድ ወንጀል ሊያስጠይቅ
የማይችል ነገር ያለ አይመስልም። እድሜ ለ’ጸረ ሽብር’ አዋጁ!...
በሌላ በኩል ደግሞ መንግስትም ሽብር ውስጥ ነው ያለው። ህዝቡ በአገዛዙ ተስፋው ተሟጧል።

የሚነቀል እንጂ የሚቃና ያለመሆኑን ያመነ ይመስላል። በዚያ ላይ የኑሮ ውድነት
አንገብግቦታል።… ይህ ህዝብ ‘በቃ!’ ሊል ይችላል። ይህ ደግሞ ያሸብራል። አዎ- መንግስትም
ተሸብሯል።
ይህ ‘ሽብርና ‘ፀረ ሽብር’ የወቅቱ ትኩሳት እንደመሆኑ የዛሬውን የክፍል ሁለት ቅኝታችን ትኩረት
እንዲሆን ወደድኩ። በዛሬው ምጥን ፍተሻ አራት በተለያዩ ጊዜያት የተላለፉ ኬብሎችን
እንዳስሳለን። ሶስቱ ከቀድሞው የአሜሪካ አምባሳደር ከዶናልድ ያማማቶ የ2009 ዓ.ም መልእክቶች
ሲሆኑ አንዱ ደግሞ አምባሳደር ባልተሰየመበት ወቅት የመንግስታቸው ጉዳይ ፈጻሚ ከነበሩት
ከቪኪ ሁድልስተን የ2006 ዓ.ም መልእክት ላይነው።
(የተከበሩ አንባቢያን በሪፖርቶቹ ላይ የሚጠቀሱ አንዳንድ ሹማምንት የሚነሱት መልእክቶቹ
በተላለፉበት ወቅት በነበራቸው ሚና መሆኑን ልብ እንዲሉ አምናለሁ።)
ሽብር?!.... የምን ሽብር!
የሀሳቡ ጸናሽ አሜሪካ ናት። መነሻዋም ኒው ዮርክና ዋሽንግተን ዲሲ የተፈጸሙት የሽብር
ተግባራት ነበሩ። በወቅቱ ወዳጅ ባለቻቸው ሀገራት ሁሉ የጸረ ሽብር ህግ እንዲወጣ ግፊት ማድረግ
ጀመረች። ይህ ደግሞ ለኢህአዴግ ደስታ ሰጠ። ለተቃዋሚዎቹ ታርጋ እየለጠፈ እንደመኖሩ “የጸረ
ሽብር ህግ” በሚለው አዲሱ ሀሳብ ስር ይበልጥ አፋኝ የሆኑ ህጎችን መንደፍ ጀመረ።… ረቂቁ
ሲወጣም አሜሪካኖቹ ከጠበቁት እጅግ የተለየና ትልሙን የሳተ ሆኖ ተገኘ። እስቲ ከአምባሳደሩ
ቃላት ጥቂት እንይ፦
“ከ2001 ዓ.ም ጀምሮ ስለ ጸረ ሽብር ህጉ አስፈላጊነት ከመንግስት ጋር ስንወያይ የቆየን ቢሆንም
አሁን የወጣውን ረቂቅ ግን እንዲሻሻል ስጋታችንንና ትችታችንን እያቀረብን እንቆያለን።
“የሚያሳዝነው ግን የኢትዮጵያ መንግስት በቅርቡ እንዳወጣቸው የሲቪል ማህበረሰብን፣ የፕሬስንና
የፖለቲካ ፓርቲዎችን እንደሚመለከቱት ህጎች ሁሉ ይህንንም አፋኝ ህግ ባለበት መልኩ
ለመተግበር ፀንቶ መቆሙ ነው።”
አምባሳደር ያማማቶ ይህ የፀረ ሽብር ህግ አፋኝና ከቆመለት አላማ ጋር ግንኙነት የሌለው
ስለመሆኑ እየደጋገሙ ነው የከሰሱት። ገና ከመጽደቁ በፊት በማርች 2009 ዓ.ም ባስተላለፉት
መልእክት ላይ እንዲህ ይላሉ፦Page 2 of 6
“ባለበት ቅርጹ ከጸደቀ ለኢትዮጵያ መንግስት ባለስልጣናት የፖሊስ ስቴት ያህል ስልጣን
ይሰጣቸዋል። ምክንያቱም ረቂቁ በህገ-መንግስቱ የተረጋገጡትን አብዛኞቹን የህዝብ መብቶች
ስለሚገፍ ነው።
“ሰፊና ተለጣጭ ትርጉም ሲሰጠው መጭው ህግ በቀላሉ የተቃዋሚ ቡድኖችን ለይቶ ለማጥቃት
መዋል ይችላል። መንግስት ተቀናቃኞቼ ናቸው የሚላቸውን በጸረ ሽብር ስም ነጥሎ ለማጥፋት ህጉ
ወሰን የለሽ ኃይል ይሰጠዋል። ይህ መንግስት ደግሞ ተቃዋሚዎቹ ላይ መሰረተ ቢስ ውንጀላዎች
የመለጠፍ ፍላጎቱን ደጋግሞ ያሳየ ነው።”
ያማማቶ በሪፖርታቸው ላይ የህጉን አስፈላጊነት ሲያነሱ የሚከተሉትን ነጥቦች ነቅሰው
አጣቅሰዋል።
“በዚህ ህግ ስር የደህንነት መስሪያ ቤቱና የፌደራል ፖሊስ ልዩ የፀረ-ሽብር ግብረ ኃይል ያለምንም
የፍርድ ቤት ትእዛዝ የጠረጠሩትን ሰው ሁሉ የመከታተል፤ ስልኩን የመጥለፍም ሆነ ቤቱን
የመፈተሽ መብት ተሰጥቷቸዋል። ዜጎች መንግስት ሽብርተኛ ስላላቸው ሰዎች መጻፍ፣ ማተምም
ሆነ ማሳተም ተከልክለዋል። ሌላው ቀርቶ ቤትም ሆነ መኪና ያከራየ ወይም ጸጉረ ልውጥ ቤቱ
ያስጠጋ እንኳን በ24 ሰዓት ውስጥ ሪፖርት የማድረግ ግዴታ ተጥሎበታል።…
“ክስ ከተመሰረተ ደግሞ ሂደቱ በዝግ ችሎት ሊታይ ይችላል። በዚያ ላይ ማንነታቸው ያልተገለጹ
ሰዎችን ምስክር ብሎ መቁጠርና የ’ስማ በለው’ ቃልም እንደ መረጃ ተቀባይነት እንዲኖረው
ተደርጓል።…”
ባጭሩ አምባሳደሩ የዳሰሷቸው አንቀጾች እንደሚያሳዩት ከሆነ ማናቸውም ሰው ያለ አንዳች በቂ
ምክንያት ክትትል ሊደረግበት፣ ሊፈተሽ፤ ሊታሰርና ሊከሰስ እንዲሁም ባልታወቁ ሰዎች በወሬ ወሬ
ተመስክሮበታል ተብሎ ሊፈረድበት ሁሉ ይችላል ማለት ነው።
ይህንን አፋኝና አስፈሪ ረቂቅ አምባሳደሩ “ግፊት ብናደርግም ሊያጸድቁት ጸንተዋል።” እንዳሉት
ሁሉ በጁላይ ወር ላይ ጸድቋል።
“ሕጉን እርሱ፤ እኛን እመኑ”
የኢትዮጵያ ፓርላማ አፀደኩት ከማለቱ ከ3 ቀናት በፊት ደግሞ ረቂቁን አስመልክቶ አምባሳደር
ዶናልድ ያማማቶ የጠ/ሚ/ሩ ቢሮ ኃላፊና የካቢኔ ጉዳዮች ሚኒስትር ከሆኑት ከአቶ ብርሃኑ አዴሎ
ጋር ተወያይተው ነበር።
አቶ ብርሃኑ በአምባሳደሩ የተለያዩ ሪፖርቶች ላይ የተነሱ፣ ከ2005 ዓ.ም በኋላ በወጡ ህጎች ላይ
ሁሉ በዋናነት ያጋፈሩና የአቶ መለስን አመኔታ ማግኘታቸው የተጠቀሰላቸው ሰው ናቸው። እኚህ
የህግ ባለሙያ የጸረ ሽብር ህጉ መንግስትን ከችግር ለማዳን ሳይሆን ሕዝቡን ከጥቃት ለመጠበቅ
ብቻ የተቋቋመ ነው የሚል አስገራሚ ክርክር ያቀርባሉ።
“የጸረ ሽብር ህጉ” ህዝብ ላይ ያነጣጠረ የሽብር ተግባር ስለመኖሩ በተጨባጭ መረጃ ካልተረጋገጠ
በቀር በተግባር አይውልም። ሌላው ቀርቶ መንግስት ለመገልበጥ ወይንም ባለስልጣናትን ለመግደል
የሚደረግ ሙከራ እንኳን በተራ የወንጀል ህግ እንጂ በዚህ ህግ አይታይም” ባይ ናቸው። እንደ
ምሳሌ ያጣቀሱት ደግሞ (ዛሬ በዚሁ ህግ የተወነጀሉትን) የግንቦት ሰባቱን ዶ/ር ብርሃኑ ነጋን ነበር።Page 3 of 6
“ለምሳሌ ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ መንግስት ስለመገልበጥ ያለውን ሀሳብ ፍንጭ ሰጥቷል። በተጨባጭ
ለግልበጣ ኃይል እያስተባበረ መሆኑ ቢረጋገጥ እንኳን በወንጀለኛ መቅጫ እንጅ በፀረ ሽብር ህጉ
አይከሰስም።” እንዳሏቸው አምባሳደሩ ጽፈዋል።
ያማማቶ የሂዩማን ራይትስ ዎችን ሪፖርት መሰረት አድርገው ‘የተቃዋሚ መሪዎችን ለመጥለፍና
ነጻ ፕሬስን ለማጥፋት የረቀቀ ህግ ነው’ ስለተባለው ክስ አንስተው ነበር። የአቶ መለስ ዋና አማካሪ
ግን በፍጹም ተዋሚዎችም ሆኑ ነጻው ፕሬስ አይነኩም ባይ ሆኑ።
ምንም እንኳን ህጉ ተለጣጭና አፋኝ መስሎ ቢቀረጽም የአቶ መለስ መንግስት ግን ከማረምና
ከማሻሻል ይልቅ “እመኑኝ አልጠቀምበትም” የሚል ሽንገላ ነበር ለማቅረብ የወደደው።
“በቅርቡ እንደወጡት ሌሎች ህጎች ሁሉ መንግስት የሽብር ህጉንም ለማሻሻል ፍቃደኛ አይደለም”
የሚሉት ያማማቶ “ይልቅስ በአንቀጾቹ የተቀመጡትን ነጥቦች በተግባር አንተረጉማቸውም፣
ከተጻፈው ነገር ይልቅ በመንግስት በጎ አላማ ላይ እምነታችሁን ጣሉ እያሉ ሊያሳምኑን ይሞክራሉ”
በማለት የአስተዳደሩን አስገራሚ ድርቅና ያጋልጣሉ።
እንደ አምባሳደር ያማማቶ እምነት ግን የጸረ ሽብር ህጉ ሽብርን ሳይሆን ተቃዋሚዎችን ለመዋጋት
ነበር የተቀረጸው።
“የሽብር ህጉ” ይላሉ ያማማቶ ግምገማቸውን ሲያቀርቡ “ከ2005 ዓ.ም ወዲህ ከወጡት በርካታ ህጎች
ጋር ነው መታየት ያለበት። በጥቅሉ ሲወሰዱ በሀገሪቱ የተቃዋሚ ፓርቲዎች መደራጀት
እንዲያቅታቸው፤ በወጉ ተንቀሳቅሰውም ለገዥው ፓርቲ ብቁ አማራጭ ሆነው ለመቅረብ
እንዳይችሉ የሚያደርጉ ናቸው።”
አምባሳደሩ ደጋግመውና አጠንክረው ገዥው መንግስት ተቃዋሚዎቹን ባገኘው መንገድ ሁሉ
የመወንጀል ልምድ እንዳለው ጠቅሰዋል። ይህ ህግም አላማው ከዚህ ውጭ እንደማይሆን
ያደረባቸውን ስጋት ለውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤታቸው አስተላልፈዋል። እነሆም ዛሬ ያሉት ሁሉ
ተፈጽሟል።
ያማማቶ የኢትዮጵያ መንግስት ተቃዋሚዎቹን ያለ አግባብ ይወነጅላል ብለው የሰጉት
ያለምክንያት አልነበረም። ተደጋጋሚ ሪኮርዱን በቅርቡ ያለው ኢምባሲያቸው ሲከታተለው የቆየ
ጉዳይ ስለነበር እንጂ። ለአስረጅ ያህል አንድ ሁለቱን እንመልከት፦
“ኤፕሪል 25 ቀን የኢትዮጵያ መንግስት ከግንቦት ሰባት ጋር ግንኙነት ያለቸውንና የሽብር ተግባር
ለመፈጸም በእቅድ የተንቀሳቀሱ 35 ሰዎችን አስሬያለሁ አለ። በአንዳንድ መገናኛ ብዙሃን
የተጠቀሱ የተለዩ ምክንያቶችን ፈጥኖ በማስተባበልም በሽብርተኝነት እንዳሰራቸው ለማስረዳት
ሞከረ።
“ይሁንና ክሱን የሚደግፍ አንድም አይነት መረጃና ማስረጃ ሳይኖር እኛ እና ያነጋገርናቸው ሌሎች
ዲፕሎማቶች የወሰድነው ግንዛቤ - ክሱ ተቃዋሚዎችን ለማፈን የተወሰደ የተለመደ እርምጃ
ስለመሆኑ ነው። ባለፉት አመታት በተደጋጋሚ እንዳደረገው ሁሉ አሁንም የኢትዮጵያ መንግስት
በጦሩም ሆነ በሲቪል ሰርቪሱ ውስጥ ያሉ ተቃዋሚዎቹን የሚደግፉ ግለሰቦችን እየለየ ለመክሰስ
ማቀዱን ነው ያመንነው።” ይላል መግለጫው በወጣ በሶስተኛው ቀን ወደ ስቴት ዲፓርትመንት
የተላከው የአምባሳደር ያማማቶ መልእክት።
“የስቴት ኮሚኒኬሽን ሚኒስትር የሆኑት ኤርሚያስ ለገሰ በፍርድ ቤት ትእዛዝ የተጠርጣሪዎችን ቤት
ስንፈትሽ የጦር መሳሪያዎችንና ፈንጅዎችን ጨምሮ የሽብር እቅዱንም የሚያሳዩ ደኩመንቶች
አግኝተናል ብለው ነበር። መንግስትም በይፋ የእቅዱ ማስተር ማይንድ ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ ናቸው
ብሏል።
“እኛም ሆንን በብሪቲሽ ኢምባሲ ያሉ አቻዎቻችን ግን የክሱን መሰረተ ቢስነት በተመለከተ
ተመሳሳይ እምነት ነው ያለን።
“ዶ/ር ብርሃኑም ቢሆን ‘በማናቸውም የትግል ስልት መታገል ያስፈልጋል’ ከሚለው አባባሉ ውጭ
እንደተጠቀሰው ከሽብር ተግባር ጋር ግንኙነት አለው ብለን የምንቀበልበት አንድም ምክንያት
አላገኘንም።” የሚሉት ያማማቶ ይልቅስ የኢትዮጵያ መንግስት ተቃዋሚዎቹን ለማጥቃት
ተመሳሳይ ዘዴ እንደሚጠቀም ካለፉት ልምዶቹ እያጣቀሱ አስታውሰዋል።
“ከዲሴምበር 2006 ዓ.ም ጀምሮ የኢትዮጵያ መንግስት በጦሩም ሆነ በሲቪል ሰርቪሱ ውስጥ ያሉ
ይቃወሙኛል የሚላቸውን ሰዎች የመወንጀል ልምድ አለው። ሌላው ቀርቶ በግልጽ ድጋፍ
ነፍገውኛል ያላቸውን ሳይቀር ነው የሚከሰው።” ይላል የአምባሳደሩ ረፖርት።
በኦክቶበር 2008 ዓ.ም “ለሽብር ተግባር የተዘጋጁ የኦነግ አባላትን ይዣለሁ” በሚል በርከታ የኦሮሞ
ተወላጆችን በሰበብ ማሰሩንም አስታውሰዋል።
መንግስት ሽብር ለመፈጸም በተጨባጭ ሲንቀሳቀሱ ያዝኳቸው በሚል 35 ሰዎችን ቢያስርም
እንኳን በገቢር ግን አንዳችም አይነት የሽብር እንቅስቃሴ መኖሩን የሚያሳይ ርምጃ አለመወሰዱም
የክሱን ከንቱነት ካጋለጡ ጠቋሚ ክስተቶች መሀል አንዱ ነበር።
“ምንም እንኳን” ይላሉ ያህንን የታዘቡት የአሜሪካው አምባሳደር “መንግስት በመዲናዋ ትልቅ
የሽብር ተግባር አከሸፍኩ ቢልም አዲስ አበባ ላይ ከወትሮው የተለየ አንዳችም አይነት ተጨማሪ
የደህንነት ጥበቃ አላየንም።”
አምባሳደር ያማማቶ ይህንን ሪፖርታቸውን ያጠናቀቁት ከበባው ተቃዋሚዎችን ለማዳከም
ስለመሆኑ ያላቸውን እምነት በሚያረጋግጥ መልኩ ነው።Page 5 of 6
“ጉዳዩን መከታተል ብንቀጥልም ተቃዋሚዎችን ለማዳከም ያነጣጠረ የፖለቲካ ማጥቃት ከመሆን
ውጭ የሚያረጋግጠው ነገር ይኖራል ብለን አናምንም።”
ይህ ምስክርነት የሚፈነጥቀው ሀቅ ቢኖር ዛሬ ከሽብር ጋር በተያያዘ ወንጀል ተከሰው በሽብርተኛው
መንግስት እስር ቤቶች የታጎሩ ወንድምና እህቶቻችን እንዴት በሸፍጥ በተቀረጸ ህግና በሰበብ
በተለጠፈባቸው ውንጀላ እየተጎሳቆሉ መሆኑን ነው። መሰረታዊ እውነቱን ደግሞ ቢያንስ የአሜሪካን
መንግስት ጠንቅቆ እንደሚረዳው ሾልከው የወጡት መልእክቶች ቁልጭ አድርገው ያሳዩናል።
የአቶ መለስ መንግስት ይህንን የመሰለውን ውንጀላ ለማቅረብ በተፈላጊዎቹ መኖሪያ ቤት የጦር
መሳሪያ እያስቀመጠ ፎቶ በማንሳት ብቻም አያቆምም። ሲያሻው ራሱ ገድሎ ራሱ
የሚወነጅልበትም ጊዜ አለ። ለዚህ ደግሞ በኦክቶበር 2006 ዓ.ም የዚያኔዋ የአሜሪካ ጉዳይ ፈጻሚ
ቪኪ ሁድልስተን ያስተላለፉትን ሪፖርት በመቃኘት የክፍል ሁለት ምጥን ፍተሻችንን እንቋጭ።
“ራሱ በድሎ - ራሱ አለቀሰ!”
“ሴፕቴምበር 16 ቀን በካራቆሬ አካባቢ ሶስት የቦምብ ፍንዳታዎች ተሰሙ። 3 ሰዎች
ስለመገደላቸውም ሪፖርት ተደረገ። መንግስት ሟቾቹ የኦነግ አባላት መሆናቸውንና ከኦሮሞ
ብሔራዊ ኮንግረስ ጋርም ግንኙነት ያላቸው ስለመሆናቸው ገለጸ። አደጋው የደረሰውም ሟቾቹ
የሽብር ተግባር ለመፈጸም በዝግጅት ላይ እያሉ ቦምቦቹን ሲገጣጠሙ በፈጸሙት ስህተት
በመፈንዳቱ ነው አለ።
“ይሁንና የኢምባሲ ምንጮቻችንና ሚስጢራዊ ሪፖርቶች የሚያሳዩት ፍንዳታዎቹ ሆን ተብለው
በራሱ በመንግስት የደህንነት ኃይሎች መፈጸማቸውን ነው።” ይላሉ ሁድልስተን።
በወቅቱ ብሄራዊ የደህንነት መስሪያ ቤቱ ከፖሊስ የጸረ ሽብር ግብረኃይል ጋር በመሆን በሰጠው
መግለጫ የአገሪቱን የዲሞክራሲና እድገት ጉዞ ለመግታት በኦነግና በሻእቢያ የተቀነባበረው የሽብር
ሴራ ከሽፏል አለ። ተጠርጣሪዎቹ በህገ ወጥ መንገድ በተገነባ ቤት ውስጥ ተደብቀው ቦምቡን
እያዘጋጁ እንዳሉ እንደፈነዳባቸውና ሁለቱ ወዲያውኑ አንዱ ደግሞ ወደ ሆስፒታል ሲወሰድ
በመንገድ እንደሞተ ነበር የዘረዘረው።
የፖሊስ የጸረ ሽብር ግብር ኃይልም ሌሎች ከሽብር ፕላኑ ጋር ግንኙነት የነበራቸውን ሰዎች አስሮ
ባደረገው ምርመራ ከሜጫና ቱለማ እና ከኦብኮ ጋር ግንኙነት ያላቸው መሆናቸውን ማረጋገጡን
አትቷል። ቦምቦቹ ምንጫቸው ኤርትራ ስለመሆኑና ከአሁን ቀደም በተፈጸሙ የሽብር ተግባራት
ላይ ጥቅም ላይ ከዋሉ ቦምቦች ጋር ስሬታቸው ተመሳሳይ ሆኖ ስለመገኘቱም ገልጿል።Page 6 of 6
የአሜሪካ ኤምባሲ ያደረገው ምርመራ ግን የተለየ እውነት ነበረው። የኢምባሲው ታማኝ
ምንጮችም የሚያስረዱት ነበራቸው። እምነት ከሚጣልባቸው አይነተኛ ምንጮች አንዱ
እንደሚከተለው ምስክርነታቸውን ሰጥተው ነበር።
“ሟቾቹ ቦምብ ሲያዘጋጁ እንዳልሞቱ እኒህ ታማኝ ምንጫችን ነገሩን። ፖሊስ ሰዎቹን ይዞ
ያሰራቸው ከሳምንት በፊት ነበር። ቶርችም አድርገዋቸዋል። በኋላም በተጠቀሰው ቤት ውስጥ ወስዶ
አስቀመጣቸውና በአቅራቢያቸው ቦምቡን አፈነዳ። - በዚህ መልኩም ሶስቱንም ሰዎች ገደላቸው።
ብለውናል።
“ሌሎች ምስጢራዊ መረጃዎች የሚያሳዩትም ቦምቦቹ እንደተባለው ቤቱ ውስጥ ሲገጣጠሙ
ያለመፈንዳታቸውን ነው። ይልቅስ ቤቱ አጠገብ ከውጭ ነው እንዲፈነዱ የተደረጉት።” ይላል
የሁድልስተን ሪፖርት።Ethiopia under wikiliks file list ( part 2 click here PDf Zelalem Gebre
Maleda news your community


Advertisements
%d bloggers like this:
search previous next tag category expand menu location phone mail time cart zoom edit close