ዲሞክራሲን ያያችሁ። በዲሞክራሲያዊ ስርዓት የዜጎች መብት        

 (ክፍል 2)   ሉሉ ከበደ

 በዲሞክራሲያዊ ስርዓት የዜጎች መብt click here pdf format Zelalem Gebre

በዲሞክራሲያዊ ስርዓት ውስጥ ዜጎች ማንም የማይነጥቃቸው፤ መንግስት የማይቸራቸው
የማይነሳቸው፤ የአለም አቀፍ ህግ ጥበቃና ዋስትና ያላቸው መብቶች አሏቸው። ማንኛውም ሰው
የኔ የሚለውን የግሉን እምነት የመያዝ የመከተል መብት አለው። የሚያስበውን የመናገር፤
የመጻፍ፤ ሙሉ መብት አለው። ማንም ሰው ማንንም ሰው እንዲህ አስብ፤ እንዲህ እመን፤ እንዲህ
ተናገር፡ እንዲህ አትናገር፤ ብሎ ሊነገረው አይችልም። ሊያዘውም ሊያስገድደውም አይችልም።
የሀይማኖት ነጻነት የተጠበቀ ነው። እያንዳንዱ ሰው የፈለገውን ሀይማኖት የመምረጥ፤
የማምለክና የማስፋፋት መብቱ የተሟላ ይሆናል።  (  እንደህዝቡ ልምድ ባህልና ወግ፤ የህዝብን
መልካም ስነምግባር፤ ደህንነት፤ ባህልና ሞራል፤ የሚጻረሩ ልምዶችን የሚያስፋፉ ሀይማኖቶች
ወይም የቡድን እምነቶች፤ የሀገርን ደህንነት አደጋ ላይ የሚጥሉ፤ የህዝቡን ምርጫና ውሳኔ
መሰረት በማድረግ፤ የህዳጣንንምመብት በእጅጉ ባልተጋፋ ሁኔታ ገደብ ሊጣልባቸው ይችላል።)
እያንዳንዱ ግለሰብ የኔ የሚለውን ባሕሉን መንከባከብ፤ ማንጸባረቅ፤ ተግባር ላይ ማዋል፤ መብቱ
የተሟላ ይሆናል። ከሌሎች መሰል አባላቱ ጋር ህዳጣንም ቢሆኑ በባህላቸው መሰረት መኖር
መብታቸው ነው። ባህላቸው የሚፈቅደውን ማድረግ መብታቸው ነው። የራሳችን በሚሉት

we have owen freedom

ልምድና አሰራርም ላይ የራሳቸው ቁጥጥር ይኖራቸዋል። እያንዳንዱ ወገን ያን ማድረግ
የዲሞክራሲ መብቱ መሆኑን መረዳትም አለበት። ይሁንና በሰው ልጅ አካልና  አእምሮ ላይ ጉዳት
ሊያደርሱ የሚችሉ ጎጂ ልምዶች እንደባህል ተይዘው ከሆነ አስፈላጊው ትምህርትና እርምት
እየተሰጠ እንዲቀሩ ይደረጋል። ለምሳሌ የሴቶች ግርዘት፤ ለውበት ተብሎ አካልን በስለት
መተልተል፤ በእሳት ማቃጠል ወዘተ….
መገናኛ ብዙሀን ፈርጀ ብዙና ነጻ ናቸው። ዜጎች ከጋዜጣ የሚያነቡትን፤ ከሬዲዮ
የሚያዳምጡትን፤ ከቴሌቪዢን የሚያዩትን የመምረጥመብት አላቸው።
ዜጎች ከመረጡት የሙያ ቡድን፤ የሰዎች ስብስብ ጋር የመደራጀት፤ የመተባበር መብታቸው
የተጠበቀ ነው።
ዜጎች በሀገራቸው ውስጥ ያለ ምንም ገደብና ጥያቄ፤ ከቦታ ቦታመዘዋወር፤ ከክልል ክልል አማርጦ
መኖር፤መስራት፤መብታቸው ነው። ከፈለጉም ከሀገርመውጣት።
የመሰብሰብ ነጻነት፤መንግስትን በድርጊቱ የመቃወምመብትሙሉ የዜጎች ነው።2
ዜጎች እነዚህን መብቶቻቸውን እየተጠቀሙ በለትተለት ኑሮአቸው ውስጥ በሚያደርጓቸው
እንቅስቃሴዎች ሁሉ፤ የሕግን የበላይነት መጠበቅና የሌሎችን መብት መጠበቅ ከመብታቸው
ጋር የተቆራኘ ግዴታቸውመሆኑን ማወቅ ይጠበቅባቸዋል።
በህግ ስለመገዛት
ዲሞክራሲ ማለት በህግ መገዛት እንጂ በግለሰብ መገዛት ማለት አይደለም። ዲሞክራሲ ባለበት
አገር ውስጥ ህግ የዜጎችን መብት ያስከብራል። ደንብና ስርዓትን ያስጠብቃል። የመንግስትን
ስልጣን ይገድባል። ዜጎች ሁሉ በህግ ፊት እኩል ናቸው። ዘሩን፤ ሀይማኖቱን፤ ጎሳውን፤ ጾታውንና
ቀለሙንመሰረት በማድረግ በሰብዓዊ ፍጡር ላይ አንዳችም አድሎና ልዩነት አይደረግም።
ማንም ሰው በዘፈቀደ አይታሰርም። ወህኒ አይገባም። አገርጥሎ እንዲሰደድ አይደረግም።
አንድሰው በፖሊስ ሲታሰር የተከሰሰበትን ጉዳይ የማወቅ መብት አለው። የግለሰቡ ወንጀል፤
በህግ፤ በፍርድቤት ውሳኔ እስካልተረጋገጠ ድረስ እንደንጹህ ዜጋ ይቆጠራል።
ማናቸውም በወንጀል ድርጊት የተከሰሰ፤ ወገንተኛ ባልሆነ ችሎት፤ ከአድሎ የጸዳ፤ ለህዝብ ይፋ
የሆነና ፈጣን ፍርድ የማግኘት መብት አለው። ህግ በሚፈቅደው አኳሗን ካልሆነ በስተቀር ማንም
ሰው አይከሰስም አይታሰርም።
በወያኔ ዲሞክራሲ አንድ ዜጋ ኦነግ ነህ ወይም ግንቦት ሰባት ነህ ተብሎ ከመንገድ ላይ ተጎትቶ
አስር አመትም ሊታሰር ይችላል።
በዲሞክራሲ አገር ውስጥ አንድም ዜጋ ከህግ በላይ አይደለም። ንጉስም፤ የተመረጠ
ፕሬዚዳንትም፤ ጠቅላይሚኒስትርም፤ ሁሉም ከህግ በታች ናቸው።
በወያኔው ዲሞክራሲ የህውሀት ባለስልጣናት ከመለስ ዜናዊ ጀምሮ በተለይም የተወሰኑቱ
የማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት ከሕግ በላይ ናቸው። እነመለስዜናዊ የሚከሰሱበት ችሎት ሄግ ካልሆነ
ኢትዮጵያ ውስጥ የለም። በኢትዮጵያ ውስጥ ያለው የፍትህ ስርዓት የተሰራው ሰፊው ህዝብ እናም
በተለይ ደግሞ መንግስቱ ሰስልጣኔ ያሰጋሉ ይቃወሙኛል የሚላቸው ወገኖች ሁሉ እንዲቀጡበት
ተደርጎ ነው።
ሕግ ሚዛናዊ በሆነ መልኩ ፍጹም ከወገንተኝነት በጸዳ ሁኔታ ከሌላው የመንግስት አካል ንክኪ
በሌላቸው ፍጹም ነጻነት ባላቸው ፍርድቤቶች ተግባር ላይ ይውላል። ተፈጻሚም ይሆናል።
ቁም ስቅል ማሳየት (ቶርች)፤ጭካኔ የተሞላበት ድርጊት በዜጎች ላይመፈጸም፤ ኢሰብዓዊ አያያዝ
ፍጹም የተከለከለ ነው።
በወያኔ ዲሞክራሲ ዜጎችን ገልብጦ መግረፍ፤ ብልት ላይ ኮዳ ውሀ ማንጠልጠል፤ አሰቃቂ
ግርፋት፤ እናም በድብደባ አሰቃይቶመግደል፤ ወይም ደግሞ ያላደረጉትን እንዳደደረጉ እያናዘዙ
ፊልም ማንሳትና በቴሌቪዢን ለህዝብ ማሳየት የተፈቀደ ነው።3
ሕግ በመንግስት ስልጣን ላይ ገደብ ይጥላል። አንድም የመንግስት ባለስልጣን በህግ የተሰጠውን
ስልጣን ተላልፎ አንዳች ነገር አያደርግም።
በወያኔ ዲሞክራሲ የወያኔ ባለስልጣናት ስልጣን የህግ ገደብ የለውም። አንድ የወያኔ ሹም
የፈለገውን ያደርጋል።
የሀገር መሪ፤ ሚኒስቴር ወይም የፖለቲካ ፓርቲ መሪ ለአንድ ፍርድ ቤት የቀረቡለትን የክስ
ጉዳዮች እንዴት እንደሚመለከት ለችሎቱመመሪያ ሊሰጥ አይችልም።
በወያኔው ዲሞክራሲ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሬዲዮና በቴሌቪዥን እነ እከሌ ወንጀለኞች ናቸው
በማለት ዳኞች ስለሚሰጡት ፍርድመመሪያመስጠት ይችላል።
ባለስልጣናት የተሰጣቸውን ስልጣንና ሀላፊነት ለግል መበልጸጊያ ሊጠቀሙበት አይችሉም።
ማንም ይሁን ማን ከሕዝብ የተሰጠውን ስልጣን ተጠቅሞ ለግሉ ከበለጸገ፤ ነጻ ፍርድ ቤቶችና
ድርጊቱን ለመመርመር የሚቋቋሙኮሚሽኖች አስፈላጊውን ቅጣት ይሰጡታል።
በወያኔ ዲሞክራሲ እያንዳንዱ ባለስልጣን የሚፈልገውን ያህል ሀብት መስረቅ በውጭ ባንክ
መደበቅ ይችላል። እስካሁን ባጠቃላይ ከ  11  ቢሊዮን ያሜሪካን ዶላር በላይ በውጭ ባንኮች
መደበቃቸው ተረጋግጧል። ወያኔ ጸረ ሙስና ኮሚሽን አቋቋመ። ያኮሚሽን ታች ወለሉ ላይ
ያሉት ትናንሽ ሌቦች እንደተምች ስለበዙና ዋና ዋናዎቹ ትልልቅ ሌቦች የሚሰርቁትን
የሚቀንሱት መስሎ ስለታየ፤ የጸረሙስናው ኮሚሽን ተልኮ ትንንሾቹን ማጥፋት ነው የሚሆነው።
ትልልቆቹ ሌቦች የመንግስት ጥበቃ ይደረግላቸዋል። በቅርቡ ለተሰረቀ አስር ሺ ቶን ቡና መለስ
ዜናዊ እጃችን አለበት ብሏል።
ዲሞክራሲን ስለሚገድቡ ግዴታዎች
ዲሞክራሲ እንሻለን በምንልበት ጊዜ የዲሞክራሲ መብታችንን እየተጠቀምን ስንኖር
የምናከብረውም ግዴታ መኖሩን መዘንጋት አያሻም። ዜጎች መብታቸውን   መጠቀም ላይ ብቻ
ካተኮሩ የሚከበሩ መርሆዎች፤ ህጎችና ዲሞክራሲያዊ ባህሪያት ሊዘነጉ ይችላሉ። በመጀመሪያ
ደረጃ ከሁሉም የበላይ የሆነውን ታላቁን ህግ ማክበር ነው። በሁለተኛ ደረጃ የራስን መብት
እንደሚፈልጉ ሁሉ የሌላውንምመብትመጠበቅ።
በፖለቲካ ባላንጣ አንጻር ወይም ደግሞ መንግስትን ጥያቄ በመጠየቅ አንጻር አመጽና ሁከትን
ሀይልመጠቀምን ማስወገድ የዲሞክራሲ ባህልና ወግ ነው።
የፖለቲካ አስተሳሰብ ልዩነት ስላለ ብቻ በተቃራኒ የቆመውን ተቃዋሚ ፓርቲ እንደ ጠላት ቆጥሮ
ማሳደድ ማሰርናመግደል የሚፈቀደው በወያኔ ዲሞክራሲ ብቻ ነው።
እያንዳንዱ ዜጋ የሌሎች ዜጎችን መብት መጠበቅና መንከባከብ አለበት። እያንዳንዱ ዜጋ
የሌሎች ዜጎችን ክብርና ሰብዓዊ ሰውነት መጠበቅ መንከባከብ አለበት። ይህ የዲሞክራሲ ግዴታ
ነው።4
የወያኔው ዲሞክራሲያዊ መሪ መለስ ዜናዊ ባማራው ሕዝብ ላይ የጠለቀ ጥላቻ አለው። ዜጎችን
ያለፍትህ ይገላል። ያስራል። ያሰቃያል።
የአቋምና ያመለካከት ልዩነት ሰላለ ብቻ ማንም ዜጋ የሚቃወመውን የፖለቲካ ድርጅት ስም
ማጥፋትመጥፎ ቅጽልመስጠት አይችልም።
በወያኔ ዲሞክራሲ መለስ ዜናዊ የፖለቲካ ድርጅቶችን  (ተቃዋሚዎችን) አሸባሪዎች ናቸው እያለ
ይናገራል። ባዋጅ ያስነግራል። ይህ የፖለቲካ ስድነት ነው። ጋዜጠኞችንም ጨምሮ ስም
ያጠፋል። ይከሳል። ያስራል። ካገር እንዲሰደዱ ያደርጋል። ይህ የጤናማ መንግስት ባህሪ ሳይሆን
በሆነ አጋጣሚ ያንድን አገር ሕዝብ የመቆጣጠር እድል ያገኘ የአሸባሪዎች ቡድን ውለኛ ባህሪ
ነው።መለስና ጉዋደኞቹ ፍጹም አሸባሪዎች ናቸው።
ዜጎች በዲሞክራሲያዊ ምርጫ በህዝብ ለተሰየመ መንግስት የተሰጠውን ስልጣን እውቅና መንፈግ
አይችሉም። ነገርግን ስለሚያወጣቸው ፖሊሲዎችና ስለሚወስናቸው ውሳኔዎች ጥያቄ መጠየቅ
ይችላሉ።
ሰዎች ባንድ ጉዳይ ላይ የሚሰማቸውን ሲገልጹ ሌሎችንም የማዳመጥ ሀላፊነት አለባቸው። ምንም
እንኳ የማይስማሙበት ሀሳብ ቢሆንም። እያንዳንዱ ሰው ቅሬታውን ሲናገር የመደመጥ መብት
አለው። ልዩ ልዩ ፍላጎቶችና አመለካከቶች አስተሳሰቦች በተለያዩ ሰዎች ዘንድ መኖራቸውን
መገንዘብ ግድ ይላል። እኔ ብቻ ነኝ ትክክለኛና አዋቂ ብሎ ማመንን ዲሞክራሲ አይፈቅድም።
የመለስ ዲሞክራሲ ሊፈቅድ ይችላል።
ማንኛውም ዜጋ የዲሞክራሲ መብቱን ተጠቅሞ አንድ ነገር ሲጠይቅ ቀድሞ መረዳት ያለበት ነገር
እያንዳንዱ ሰው የሚሻውን ነገር ሁሉ ሊያገኝ የማይችል መሆኑን ነው። ዲሞክራሲ ስምምነትን
ይጠይቃል። አንተም ይህን ተው እኔም ይህን ልተው ማለትን። የተለያየ አመለካከትና አስተሳሰብ
ያላቸው ወገኖች በጠረጴዛ ዙሪያ ተገናኝተው በመነጋገር ልዩነቶቻቸውን ማጥበብ አለባቸው።
በዲሞክራሲያዊ አሰራር ውስጥ አንድ ቡድን ሁል ጊዜ እሱ የሚፈልገውን ብቻ የሚያሳካበት
አጋጣሚ ሊኖር አይችልም። የተለያዩ ቡድኖች በተለያዩ ግዳዮች ላይ አሸናፊዎች የሚሆኑበት
ጊዜ ይኖራቸዋል። የሗላ ሗላ ሁሉም ወገን የተሳካለት ነገር ወይም ነገሮች    ይኖሩታል ማለት
ነው።
አንድ ወገን ሁል ጊዜ ከተገለለና ተደማጭነትን ካጣ እንደወያኔ ፖለቲካና ዲሞክራሲ ሁል ጊዜ
አንድ ወገን ብልጥ ሆኖ የራሱን ጥቅምና ፍላጎት ብቻ ለማሳካት ሲል ሌሎችን ሁሉ ወደ ገደል
እየገፋ አይኑን ጨፍኖ የሚሮጥ ከሆነ፤ የዲሞክራሲ ባህልና ወግ ይጠፋና አመጽ ይተካል። እዚህ
ላይ ዲሞክራሲ የኛን የይሉኝታ ባህልም ይፈልጋል ማለት ነው። አሁን በወያኔ ዲሞክራሲ
የይሉኝታ ባህል የለም። እየቀጣን እናስተምራቸዋለን። ወይንም እያስተማርን እንቀጣቸዋለን።
በዚህ ጽሁፍ አቅራቢ ግምት ከስድስት ሚሊዮን የማያንስ ኢትዮጵያዊ ባለም ላ ይ ተበትኖ ይገኛል
። ቢያንስ ቢያንስ አንድ ሚሊዮን ሀገሩን የሚወድ ኢትዮጵያዊ ይጠፋ ይሆን? ይ ህ አንድ ሚሊዮን
ሰ ው በየወሩ አስር አስር ብ ር ብ ቻ ቢያዋጣ የወያኔን አፈና ተቋቁሞ ሀ ያ አራት ሰ ዓ ት ለኢትዮጵያ
ህዝብ አውነትን የሚያስተላልፍ ቴሌቭዢን ይኖራል። አስር ብ ር ማለት ደ ግ ሞ አን ድ ቅዳሜ
መሸታ ቤ ት ጎ ራ ብለን ከምናቀልጠው ገንዘብ ጋ ር ሲነጻጸር ምንም ማለት አይደለም። እባካችሁ
እባካችሁ ይህን ጽሁፍ አንብባችሁ እንደጨረሳችሁ  ESAT  የሚለውን በማውስ ጠቁሙና አንድ
ነገር አድርጉ። እንደ አኬልዳማ አይነቶቹን የወያኔ ውሸቶች ፤ እውነቱን በማቅረብ ነ ው ህዝቡን
መታደግ የሚቻለው። ጸሀፍትም ሁ ሉ በየጽሁፎቻችሁ መጨረሻ ላ ይ ይህንን ልመና አቅርቡ ።
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር

Advertisements
%d bloggers like this:
search previous next tag category expand menu location phone mail time cart zoom edit close