የአወሊያ ኮሌጅ ተቃዉሞ ዛሬም ቀጥሏል

አዲስ አበባ: ሬዲዮ ቢላል ጥር 02/2004 ከ11 በላይ ተማሪዎች ታስረዋል በአወሊያ ኮሌጅ ተማሪዎች ትናንት ያገረሸው የተቃዉሞ ሠልፍ ዛሬም እንደቀጠሉ መሆኑን የሬዲዮ ቢላል ምንጮች አስታወቁ፡፡ በሥፍራው የሚገኘው የሬዲዮ ቢላል ዘጋቢ ከምንጮቻችን መረዳት እንደቻለው በዛሬው ዕለት ብቻ ከ11 በላይ የኮሌጁ ተማሪዎች በፀጥታ ኃይሎች ተወስደዋል፡፡ የተማሪዎቹ ጥያቄ ጠንከር ብሎ መጅሊሱ አይወክለንም አይመራንም ወደሚል መሸጋገሩም ተጠቁሟል፡፡ ተማሪዎቹ ወላጆች ትናንት በግቢዉ ዉስጥ በሚገኘው መስጂድ ሹራ ሲያደርጉና ችግሮች እንዲወገዱ ለፈጣሪያቸው ፀሎት ሲያደርሱ ማደራቸውንም ለማወቅ ተችሏል፡፡ በኮሌጁ ግቢ ዉስጥ በርካታ የፌዴራልና የከተማ ፖሊስ አባላት ፈሰው እንደሚገኙ የሬዲዮ ቢላል ዘጋቢ ተመልክቷል፡፡ ከተወሰዱት የኮሌጁ ተማሪዎች በተጨማሪ ሌሎች ቁጥራቸው በውል ያልታወቀ ተማሪዎችም እየታሰሩ መሆኑን ለመታዘብ ችለናል፡፡ የተማሪ ወላጆች ተማሪዎችን በማረጋጋት ሥራ ላይ የዋሉ ሲሆን ከሚመለከታው የመንግሥት አካላት ጋር በመወያየት መፍትሔ ለማምጣት ያስችለናል ያሉትን አንድ ኮሚቴም አቋቁመዋል፡፡

Advertisements
%d bloggers like this:
search previous next tag category expand menu location phone mail time cart zoom edit close