በኖርወይ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች በግዳጅ ወደ ሃገራቸው ሊጠረዙ ነው::


በአቢ ገብረሃና Abby Gebrehanna/ኖርወይ/

ከሰሞኑ የአፍሪካ ህብረት ባደረገው ሰብሰባ ከያዛቸው የመወያያ አጀንዳዎች አንዱ በአፍሪካ አህጉር የሰብአዊ መብት ረገጣ ለተደረገባቸው መታወሻ የሚሆን ኢንስቲቲዩት ማቋቋም መሆኑን ስሰማ በጣም ነበር የገረመኝ:: ይባስ ብለው የፕሮጀክቱ የበላይ ጠባቂ ሆነው የተሾሙት ፕሮፊሰር አንድሪያስ እሽቴ  አላማውን ሲዘረዝሩ “…መታሰቢያነቱ በአፍሪቃ መንግስታት በእኛው በኢሰብአዊ አያያዝ የተረገጡትን ማስታወሻ ነው” ካሉ በሗላ የአፓርታይድንንና የደርግን  የቀይ ሽብር ሰለባዎች ለአብነት ጠቃቅሰው ራሳቸውም የታሪኩ ተቁዋዳሽ የሆኑበትን የትናንቱን የጋምቢላ ፥የጂማ ፥የአዲሳ አበባ የበደኖውን  ኦጋዲኑ፥ እረ ስንቱ… የወያኔ  ኢሰብአዊ የመብት ረገጣ ውሃ ሲቸለሱበት ሳስተውል “ተምሮ መና! አለ ያገሬ ሰው አሁን ኢኚህ ሰው ፐሬዚዳንት በነበሩብት ትምሀርት ቤት  ነበር የተማርኩት” ስል ራሴንም ሳልታዘበው አልቀረሁም ።

በዚህ ሁኔታ ስብሰለሰል ሳለ በትናንትናው እለት አንድ ወዳጀ  “በእግር በፈረስ ሳፈላልግህ ነበር…” አለኝ ፊቱ በድነጋጤ  ቡን እነዳለ ነበር “የወያኔንና የኖርወይን ጉድ ስማህ? ሲል ጠየቀኝ ፧ “ጆሮ አይሰማው የለ፡ እረ አልሰማሁም፤ ምን ተፈጠረ ደሞ?” ብየ መጠየቅ

“እረ ጉድ ነው! የኛው ሆዳም ጥቂት ጉርሻ ኖርዊጅያኖች ጣሉለት መሰል… ሰደተኞችን እንደፊስታል አንጥልጥላችሁ መልሱልኝ ኢትዮጵያዊ እንደዚህ መጠጊያ ይጣ? አለኝ::” ትክዝ እንዳለ ። “ይህ ነገር የተለመደው የወያኔዎች የማወናበድ ወሬ እንዳይሆን” ስል ወሬውን ላጣጥልበት በሞክርም ከነማስረጃው ይሕው አለኝ:: እኔም ይህንኑ  የወያኔዎች ባህር ተሻጋሪ ተቅበዝባዥነት ላወጋችሁ ወደድኩ።

በአሁን ሰአት በሃገር ውስጥ ያለውን  የሰብአዊ እና ዲሞክራሲያዊ መብት ጥሰት የኢኮኖሚ ጭቆናና አፈና በመሽሽ ባገኙት ቀዳዳ በመጠቀም ከሃገር ወጥተው ከጎረበት ሃገራት እስከባህር ማዶ በመሰደድ አስከፊውን የስደት ህይወት እየገፉ የሉ ኢትዮጵያውያን ቁጥር ከእለት ወደ እለት እየጨመረ ይገኛል::

የኖርወይ ውጭ ጉዳይ ሚኒስተር ሴክሪታር ቱርጌይር ላርሰን እና ከኢትዮጵያ በኩል ደግሞ አምባሳደር ብርሃነ ገብረክርስቶስ ጋር  ስምምነቱን በተፈራረሙበት ወቅት ፎቶ በኖርወይ ፍትህና ኢመርጀንሲ ዲፓርትመንት

ታሪካዊ እውነታ

ኣጠቃላይ የኖርወይ የህዝብ ብዛት ወደ 4.99 ሚሊዮን ገደማ ይደርሳል:: ኖርወይ በአለም ላይ የሰብአዊ መብትን በማስከበር በግንባር ቀደምነት ከሚጠቀሱት ሃገሮች አንዷ ብትሆንም ቅሉ ግን በተግባር እየተደረገ ያለው  ሃቅ  የተገላቢጦሽ  ነው::

ሜይ ፍላወር በሚል ሃይማኖታዊ ምክንያት በ1825 ወደ ታላቂቱ አሜሪካ መትመም ከጀመሩበት ግዜ አንስቶ በአጠቃላይ  በአሁኑ ሰአት በሃገር ወስጥ ማለትም በኖርወይ ካለው አጠቃላይ የህዝብ ብዛት እኩል የሚሆን ቁጥር ያለው  ማለትም 4.6 ሚሊዮን ገደማ ያህሉ ኖርዊጅያዊ ስደተኛ  በሃገረ አሜሪካን ቤት ንብረት አፍርተው በሰላም ኑሮአቸውን እንደሚመሩ የታወቃል::

ይሁን እንጂ በቁጥር በጣም አነስተኛ የሆነ ኢትዮጵያዊ ሰደተኛ ያላት ኖርወይ ኢትዮጵያውያንን አይናችሁን ላፈር ካለች ውላ አደራለች::

አድራለች:: ለረጂም ጊዘ ያህል የስራ ፈቃድ ተሰጥቱአቸው አስፈላጊውን የመንግስት ግብር እየከፍሉ ቤት ንብረት አፍርተው አግብተው ወልደው የስደት ህይወታቸውን የሚመሩ ኢትዮጵያውያን ግን ኖርውጅያውያኑ በአሜሪካን ሀገር ያላቸውን አይነት የጥገኝነት ነጻነት ኖሯቸው ሊኖሩ አልቻሉም::

ለዚህም እንደ አብነት የሚጥቀሰው አምና በ 2011በየካቲት ወር በአስሎ ካቴድራል ቤተክርስትያን ቁጥራቸው ወደ 100 ገደማ የሚሆኑት ህጻናት እና አዋቂዎች ጭምር የረሃብ አድማ ማድረጋቸው የታወሳል:: ውጤት አልባ የነበረው የረሃብ አድማ ካበቃ በሃላም ገሚሶቹ በተለያየ መንገድ ኖርወይን ለቀው ቢወጡም የኖርወይ መንግስት በቅርብ የፍልስጤም መንግስት ጋር ያደረገውን አይነት ስምምነትን በ26/2012 በአዲስ አበባ የኖርወይ ውጭ ጉዳይ ሚኒስተር ሴክሪታር ቱርጌይር ላርሰን እና ከኢትዮጵያ በኩል ደግሞ አምባሳደር ብርሃነ ገብረክርስቶስ ጋር ተፈራርመዋል::

የኖርወይ መንግስት ድርድሩን ካለፈው ጁላይ ወር 2011 ጀምሮ ሲያደርግ ከቆየ በሁላ  የስደት ጥያቂያቸው ተቀባይነት ያላገኙ ኢትዮጵያውያንን  ፍቃደኛ ከሆኑ እስከ 15 ማርች ወር 2012 ድረስ እንዲመዘገቡ ካልሆነ ደግም በግዳጅ- forced return     እንዲደሚደረጉ የሰደተኞችን ጉዳይ የሚያየው ቢሮ ይፋ አድርጋል::

ይህ የኢትዮጵያና የኖርወይ መንግስት ስምምነት በሌሎች ሃገራት ላሉ ኢትዮጵያውያን ሊያሳድር የሚችለው ተጽ እኖ በቀጣይ የሚታይ ቢሆንም ውጤቱ ግን የከፋ ሊሆን እንድሚችል መገመት ያስችላል:: ስለሆነም በስደት ላይ የምንገኝ አኢትዮጵያያን በሙሉ  ስምምነቱን ልንቃወምው ይገባል እላለሁ::

እግዚአብሄር ኢትዮጵያን ይባርክ!

Advertisements

1 thought on “በኖርወይ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች በግዳጅ ወደ ሃገራቸው ሊጠረዙ ነው::

Comments are closed.

%d bloggers like this:
search previous next tag category expand menu location phone mail time cart zoom edit close