ሉሲዎች የግብፅ አቻቸውን 4-0 አሸነፉ

Ethio football:ለአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ዛሬ በአዲስ አበባ ስታዲየም የመልስ ጨዋታውን ያደረገው የኢትዩጵያ የሴቶች ብሄራዊ ቡድን የግብፅ አቻቸውን 4-0 በማሸነፍ ወደ ቀጣዩ ዙር ማለፈን አረጋገጠ፡፡

ብሄራዊ ቡደኑ በሰፊ የግብ ልዩነት ማሸነፍ የቻለው በ37 አና 53 ደቂቃ ራሂማ ዘርጋው ፤70ኛው ሄለን ሰይፉ ፤ 83ኛው ብርቱካን ገ/ክርስቶስ ባስቆጠሯቸው ጎሎች ነው፡፡

በተመልካቹ ከፍተኛ የሞራል ድጋፍ እየታገዙ የተጫወቱት ሉሲዎች በጨዋታ የበላይነት አንፀባራቂ ድል ለማስመዝገብ ችለዋል፡፡ የቡድኑ ስብስብ አንድም የወዳጅነት ጨዋታ ሳያደርግና የረጀም ጊዜ ዝግጅት ሳይኖረው፤ በዱባይና በባህሬን የወዳጅነት ጨዋታዎች በማድረግ ከሶስት ወር በላይ የተዘጋጀውን የግብፅ ቡድን በጨዋታ ብልጫ ማሸነፉ አስፈላጊው ድጋፍ ቢደረግለት የተሻለ ውጤት ማስመዝገብ እንደሚችል አሳይቷል፡፡ ፌዴሬሽኑ ቡድኑ ከፊቱ ለሚጠብቁት ጨዋታዎች የአቋም መለኪያ ጨዋታዎች አንዲያደረግ ሁኔታዎችን ማመቻቸት ይጠበቅበታል፡፡

Advertisements
%d bloggers like this:
search previous next tag category expand menu location phone mail time cart zoom edit close