የአቤ ቶክቻው ወንድም ወንደሰን ጌታነህ በሆቴል ውስጥ ተገድሎ መገኘቱ ተሰማ

የጸሀፊና ሀያሲ አቤ ቶኪቻው የሶስት ጊዜ ታናሽ ወንድም የሆነው ወንደሰን ጌታነህ ሰሜን መዘጋጃ አካባቢ ከሚገኝ አንድ ሆቴል ውስጥ ሞቶ ተገኘ፡፡
ተመስገን ደሳለኝ በፌስ ቡኩ ላይ ባስቀመጠው ዘገባ እንዲህ ብሎአል “ይህ ልጅ ገና ታዳጊ ነው፡፡ በአንድ ገራዥ ውስጥም በብየዳ ሙያ ተሰማረቶ ይሰራል፡፡ ገነት ሆቴል አካባቢም ብቻውን ተከራይቶ ይኖር ነበር፡፡ ስለድንገተኛ አሟሟቱ ፖሊስ መረጃ ለመስጠት ጊዜው ገና ነው እያለ ነው፡፡ የተቀበረው ሽሮሜዳ ስላሴ ነው፡፡ በተቀበረ በማግስቱ የአዲስ አበባ የወንጀል ምርመራ መረጃ ክፍል ሃላፊን ከቤሮአቸው ሄጄ ስለአሟሟቱ እና በምርመራ ስለደረሱበት ነገር መረጃ እንዲሰጡኝ ጠይቄ ነበር፡፡ ኢንስፔክተር ናቸው፡፡ ነገር ግን ኢንስፔክተሩ እንዲህ አሉኝ ‹‹እኔ በቀጥታ ለአንተ መረጃ መስጠት አልችልም፤ 22 ማዞሪያ አካባቢ የሚገኘው ትራፊክ ጽ/ቤት ሂድና አናግራቸው፤ እዛ መረጃ ለመስጠት የተመደቡትን ኮማንደር ግርማ ታደሰን ታገኛለህ›› አሉኝ፤ እናም ሄድኩኝ ኮማንደሩን ላገኛቸው አልቻልኩም፡፡
እንግዲህ ስለወንደሰን አሟሟት ከፖሊስ ብዙ እንጠብቃለን የሚለው ተመስገን የገና ማግስትም እንዲሁ ካልታወቁ ሰዎች ክፉኛ የመደብደብ አደጋ ደርሶበት እንደነበርና ከአሟማቱ ጀርባ አንድ ወንጀል እንዳለ የሚጠቁሙ ወይም ፍንጭ የሚሰጡ ነገሮች እንዳ ገልጧል፡፡
አቤ ቶክቾው እጅግ ማዘኑን እና በአሁኑ ገዜ መግለጫ ለመስጠት በማይችልበት ደረጃ ላይ እንደሚገኝ ለማወቅ ተችሎአል። አቤ ቶክቻው ወደ ስደት ከመውታቱ በፊት በመንግስት ክትትል ትልቅ ችግር ውስጥ መጋፈጡን እና ወደፊትም ሊደርስበት እንደሚችል ገልጸውለት እንደነበር የሚታወስ ሲሆን እና የስደቱ ዋነና ምክንያት መሆኑን ከዚህ በፊት መዘገባችን ይታወቃል።

Advertisements
%d bloggers like this:
search previous next tag category expand menu location phone mail time cart zoom edit close