ከወያኔ በኋላ ለሚመጣው የሽግግር ወቅት መዘጋጀት ጊዜው አሁን ነው::ጋዜጣዊ መግለጫ

13 የካቲት 2004

[pdf]

በወያኔ ሃያ-ዓመት አስከፊ አገዛዝ ምክንያት ኢትዮጵያ ሀገራችን ለከባድ ጥፋትና ውድቀት ተዳርጋልች። በተለይ የወያኔ የጎሳ ፖሊሲ የኢትዮጵያን ህልውና ለከባድ አደጋ አጋልጧል። በትንሳኤ ኢትዮጵያ አርበኞች ህብረት እምነት ሀገራችንን ማዳን፥ አንድነቷን ማስጠበቅ የሚቻልበት መንገድ አለ፤ ይሄውም እንደተጠባባቂ መንግስት የሚያገለግል የሽግግር ወቅት ምክር ቤት በስደት ማቋቋም ነው።

የስደት መንግስት አዲስ ነገር አይደለም። ፋሽስት ኢጣሊያ ኢትዮጵያን ተቆጣጥራ በነበረበት ወቅት በአፄ ሃይለስላሴ የሚመራ የስደት መንግስት ነበር። ባለፉት አመታት የተለያዩ ምሁራን፥ ጋዜጠኞችና የፖለቲካ ድርጅቶች የሽግግር መንግስት በስደት እንዲቋቋም ሃሳብ ሲያቀርቡ ቆይተዋል። በቅርቡ የሶርያ ተቃዋሚ ድርጅቶች ቱርክ ውስጥ የሽግግር ምክር ቤት አቋቁምዋል።

ለሽግግር ወቅት መዘጋጀት የትንሳኤ ኢትዮጵያ ፖለቲካ ፕሮግራም ካካተታቸው ዋና ዋና ነጥቦች አንዱ ነው።

ትንሳኤ ኢትዮጵያ ከላይ የተጠቀሱትን መሰረት በማድረግ በቅርቡ የዩኒቲ ዩኒቨርሲቲ መስራች ዶ\ር ፍሰሃ እሸቴ ያቀረቡትን ብሄራዊ የሽግግር ምክርቤት ሃሳብ በግንባር ቀደምትነት ከሚደግፉ የፖለቲካ ድርጅቶች አንዱ መሆኑን ማሳወቅ ይሻል።

ኢትዮጵያንና ህዝቧን ካጋጠሟት አደጋዎች ለመከላከል በዶ\ር ፍሰሃ የቀረበው የሽግግር ምክርቤት ሃሳብ ወሳኝነት አለው ብሎ ትንሳኤ ኢትዮጵያ ያምናል። ስለዚህም ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን ሁሉ ሃሳቡን እንዲደግፉትና አስፈላጊውን ትብብር እንድናደርግ ጥሪ ያቀርባል።

ትንሳኤ ኢትዮጵያ አርበኞች ህብረት
ኢሜይል: tinsae.ethiopia@gmail.com

========================================

Preparing for transition from the Woyanne era is long overdue

February 21st, 2012

PRESS STATEMENT
20 February 2012

[pdf]

Ethiopia is currently exposed to extreme danger as a result of 20 years of misrule by the Woyanne/EPRDF regime. Woyanne’s ethnic policy in particular is an existential threat to our country. However, there is a way we can protect and preserve Ethiopia’s freedom and unity. Tinsae Ethiopia Patriotic Union believes that we must setup a transitional council in exile that will act as a caretaker government once we overthrow Meles Zenawi’s junta.

Government in exile is not a new concept. During the Fascist Italy’s occupation of Ethiopia, there was an Ethiopian government in exile led by Emperor HaileSelassie. Over the past decade, several Ethiopian scholars, writers, and organizations have proposed such an idea. Recently, Syria’s opposition has setup a transitional council in exile. Preparing for transition from the Woyanne rule is a major component of Tinsae Ethiopia’s political program.

The Ethiopian National Transition Council that is now proposed by the founder of Unity University, Dr Fisseha Eshetu, is a workable idea and Tinsae Ethiopia would like to be one of the first political parties to fully support it.

We believe that forming a transitional arrangement such as proposed by Dr Fisseha is imperative if we want to thwart the grave danger that our country is currently facing. We call on all patriotic Ethiopians around the world to rally behind the idea of forming a transitional council.

Tinsae Ethiopia Executive Committee
Email: tinsae.ethiopia@gmail.com

 

Advertisements
%d bloggers like this:
search previous next tag category expand menu location phone mail time cart zoom edit close