ሻዕቢያ ሰሙኑን ቅሌት አያጣውም

ሻዕቢያ ሰሙኑን ሻዕቢያ ቅሌት አያጣውም click here pdfተድላ ደስታ 03/05/12

ሻዕቢያ ቅሌት አያጣውም። ከያንዳንዱ ቅሌት ጋር ደግሞ ውርደት አይጠፋም። ሰሙኑን ደስ ያላለኝ ብመስል ደግም እውነትም
አይሆንም። ብዙውን ጊዜ ደስ እሚለኝ የልማት ዜናዎች ስሰማ ነው። የገዛ ጀሮዎቼን ያሰለጥንክዋቸው በዚያ መልኩ ስለሆነ።
የጦርነትና የውግያ ዜናዎች ሲሆኑ ደግሞ (የኢትዮጵያ ድል የሚያበሰሩም ቢሆኑ) የሆነ ደስ የማይል ስሜት ያኖሩበኛል። የልማትና
ንግድ ሥራ የወጣ ወጥቶ የተጣራ ትርፍ የሚባል ነገር አለው- ጤናማ ኢንቨስትመንት ከሆነ። ጦርነቶች ሁሉ ግን በዉጤትነት
የሚመዘገብ የተጣራ ትርፍ የሚባል ነገር የላቸውም። የተተኮሰብህ ሁሉ አንተን ወይም ወገንህን ያቆስላል፣ ያጎድላል። የተኮስከው
ሁሉ ጠላትህን ይገድላል እንጂ የጎደለብህን አይመልስም። የተተኮሱ ጥይቶች በሙሉ ሰው ላይ ባያርፉ እንክዋን እንስሳትን ወይም
እጽዋትን ይጎዳሉ። ተረስተው የቀሩ ያልፈነዱ ፈንጂዎችና ተተኩዋሾች ቢኖሩ ከጊዜ በኃላ ፈንድተው ሳር የሚግጥ እንስሳትን ወይ
ደግሞ አገር ሰላም ብሎ የሚጫወት ህጻንን ያጠፋሉ። ለጊዜው በድል የተጠናቀቀ የሚመስል ውግያም ቢሆን ከኃላው ጣጣ
ይከተል ይሆናል የሚል ስጋት ይጫጫነኛል። ይህ ግን በኔ ላይ ብቻ የአብዛኛው ጤናማ ሰው ስሜት እንደሆነ ጥርጥር የለውም;፡
ይሁንና ሰሙኑን ኢትዮጵያ በሻቢያ ላይ በወሰደችው እርምጃ ያ ከላይ የጠቀስኩት ዓይነት ስሜት አልተሰማኝም። ይልቁንም ልክ
ላንድ ብክፉ ደዌ ለተቸገረ ሰው የሚሰጥ እጅግ ምጡንና ፍቱን ፈውስ የተገኘ ያህል ለቀቅ የሚያደርግ ስሜት ያጣጣምኩት።
ከሻዕቢያ ጋርም ቢሆን ጥይትና ፈንጂ እየተወራወሩ መኖር የግድ አልነበረም። ከመረብ ሰሜንና ከመረብ ደቡብ ቢሆንልን
ድልድዮች እየገነባን እየተመላለስንበት፣ ካልሆነም ማዶ-ለማዶ በሰላም በሩቅ እየተያየን መኖር ጥይት ከመወራወር የቀለለና
የተሻለ መንገድ ነበር። ግን ጅብ ከሚበላህ በልተኸው ተቀደስ እንዲሉ ሆነና ኢትዮጵያ የሰሙኑን እርምጃ ለመውሰድ ተገደደች።
ሁሌም መታኮሱ ትርፍ ያለው ሆኖ የሚሰማው ሻዕቢያ መሳሳቱን ለማየት እጅግ በርካታ አጋጣሚዎች ነበሩት። የዛሬውን
የመጨረሻ ያድርግለት።
የሻዕቢያን እዩኝ-እዩኝ ደብቁኝ-ደብቁኝ ጨዋታ እንደገና በዚህ ሰሙን አየነው። ከልሳኑ መረር ያለ ቃል፣ ከእጁ ከረር ያለ ቃታ
ጠፍቶ ተውተበተበ። እሚገርመው ታድያ እንዲህ ሊስለመለም ተው ሲባልና ሲለመን፣ አልያዝም አልገነዝም ብሎ ያስቸገረው
ታድያ ለምንድነው? እሚለው ጉዳይ ነው። በጁ የያዘው ይዞ ካልሆነ ታድያ ማንን ተማምኖ ነው ያሁሉ “የኔ አቻና እኩያ አሜሪካ
እንጂ ወያኔን ከቁብ አልቆጥራትም”ቡራከረዩ ፉከራ ታድያ ለምን ነበር፣ ያሰኛል። እንክዋን አጋዥ ለቅሶ ደራሽም አልታየ። በደህና
ጊዜ ያላስቀመጡት ወዳጅ ዘመድ ድንገት ከየት ይመጣል?! ይህ ሻዕቢያ የተባለው ቡድን የወዳጆቹን ስሜት ክፉኛ አበላሽቶ፣
የኤርትራን ተከታታይ ትውልድ አኮላሽቶ፣ እራሱን በአደገኛ ሁኔታ ለመከስከስ ቁልቁለትን በፍጥነት የምትበር ፍሬን የሌላት
ብስክሌት ላይ ተሳፍሮ በመጨረሻ መጀመርያ ጉዞ ላይ ያለ ጠፊ ኃይል ሆኖ ይታየኛል። ሆኖም ግን መዳኛ እንደሌለው ባወቀ ጊዜ፣
አጥፊቼ ልጥፋ በሚል ተስፋ-ቆረጥ መንፈስ ብዙ ክፋት ሊያስብና ሊፈጽም የሚችል እጅግ አደገኛ ኃይል መሆኑን ፈጽሞ
አላጣውም።

http://www.maledatimes.com

ደርግና ቐሺ ገብሩ
የደርግ ጋዜጠኛ፡ “ብትያዙ ወይም ብትማረኩ ምን ትሆናላችሁ እያሉ ነው እሚያስተምርዋቹህ?”
ቐሺ ገብሩ፡ “ደርግ ቢይዛቹህ ይገድላቹኃል፣ ወይም ያሰቅይዋቹኃል እያሉ ነው የሚነግሩን።”የደርግ ጋዜጠኛ፡ “አሁን አንቺ ተማርከሻል፣ በአብዮታዊ መንግስታችን ቁጥጥር ሥር ነው ያለሽው፤ የተባልሽው ነገር ነው ያጋጠመሽ?”
ቐሺ ገብሩ፡ “ እስከ አሁን ምንም የሆነው የለም። ከተባልነው ውስጥ እስከአሁን ያጋጠመን ነገር የለም።”
ይች ድንቅ ታጋይ ከአንድ የሞት ሽረት ውግያ በኃላ የተስጣት ግዳጅ ከሽፎ፡ አብሮዋት የነበሩ ጉዋዶችዋ በጠላት ምርኮና ጥይት ካጣች ካንድ
ቀን በኃላ፣ ገዳይነቱን አስቀድማ በደንብ በምታውቀው ጠላት እጅ ሆና ነበር ተረጋግታና ያለምንም ፍርሃት እነዚህን ጥያቄዎች የምትመልሰው።
የቐሺ ገብሩ ቀጥተኛነት፣ ጽናትና ልብሙሉነት በገዳዮችዋ እጅ ያለች አልመስል ይላል። ጀግናስ ተለይቶ እሚወጣው በንደዚህ ዓይነት ጊዜ
አይደለ?! የቐሺ ገብሩ ግን ልዩ ዓይነት ነው። አ–ይ–ወንድነት! ይህን ግማሽ እውነት ስንት ዘመን ይዘነው እንግዋዛለን?!
የዚች ብርቅ ታጋይ ፍርሃት የለሽ ጽናት አይተው ብዙ ኢትዮጵያውያን ቢደነቁ የሚጠበቅ እንጂ የሚገርም የለውም። የኔ ትኩረት ግን
የገዳዮችዋ ምክንያት አልባ የጭካኔ ግድያ ላይ ነው። ድርጅትዋ የነገራትን ማስጠንቀቅያ ለጥቂት ጊዜ እንክዋን ውሸት ሆኖ እንዲቆይ
አላስቻላቸውም። የተፈጥሮ ጉዳይ ሆነና ደርግ ራሱ የጀመረው የማስመስል ትያትር ይዞ ለመዝለቅ የሳምንት ትእግስት አጣ። እናም በአንድ
ውግያ በእጁ የገቡለትን ምርኮኛ ታጋዮች ከባድ ማሰቃየት ከፈፀመባቸው በኃላ ጉድጉዋድ አስቆፍሮ ረሸናቸው። ባለፈው ባስነበብክዋቹህ፣
ዛሬም በምታዩዋቸው የደርግ የሚስጥር ዶክመንቶች፡ ታጋዮቹ በጠላት ምርኮኞች ላይ ያሳዩት ሰብአዊ ርህራሄና ዲስፕሊን፡ ደርግ አካባቢ
እየተፈፀመ ከነበረው ተግባር ጋር ማነጻጸር ከነውርም ነውር ይሆናል። ማወዳደሩ ቀርቶ የደርግ ውሳኔዎችና ተግባሮች በራሳቸው በምን አይነት
ሳይንስ ሊተነተኑ ይችላሉ (Are they explainable at all?) የሚለውን ቁምነገር ማሳየት ይቻል እንደሆነም አላውቅም።
መቸም በወንጀሎችና ወንጀለኞች ዙርያ ጥልቅ ሳይንሳዊ ምልከታ የሚያደርጉ ተማራማሪዎች (Criminal Minds
Behavioral Analysts) ፈትሸው እንዲህ ዓይነቱን ድርጊት ከምን እንድሚመነጭ ያስረዱን እንድሆነ እንጂ ደርግና
አርመኔነትን በቅርብ ለምናውቅ ሳይቀር ሊገባን የማይችል እንቆቁልሽ ነው።
ቐሺ ገብሩ የ15 ዓመት ልጅ ሆና ነው ወያኔን የተቀላቀለችው። በደብረታቦር ግንባር ውግያ ስትማረክም የ20 ዓመት ወጣትና የ6 ዓመት
ትግል ልምድ ያላት ልበሙሉ ጉብል ናት። በተማረከች ጊዜ ስትጠይቅና ስትመልስ እንደሰማናት የምታውቀውን በቀጥተኛ አነጋገር ትመልሳለች።
በእርግጥ ደርግ መስማት የፈለገውን ሳይሆን እውነት ነው ብላ የምታውቀውን ነበር የተናገረችው። ለመመለስ ያልፈለገችው ወይም ለመደበቅ
የሞከረችው ነገር ወይም በጥያቄና መልሱ ጊዜ ላለመተባበር ያቅማማችበት ሁኔታ አላየንም። ደርግ ሰለወያኔ ማወቅ የሚፈልገው እውነተኛ
መረጃ ከነበረ፣ ቐሺ ገብሩ ድርጅትዋ ውስጥ ባዳበረችው ቀጥተኛነትና ልብሙሉነት የምታውቀውን ያህል ለማስረዳት ስትሞክር ነበር።
ታድያ ይችን የምታውቀውን ለመናገር ፈቃደኝነት ያላነሳት፣ በቁጥጥሩ ውስጥና ምንም ጉዳት ልታደርስበት በማትችልበት ሁኔታ ውስጥ
የነበረችን፣ በወያኔ ላይ የራሱን ጥናት ለማድረግ ቢፈልግ ደግሞ መረጃ ለማደራጀት ሊጠቅምባት ይችል የነበረውችውን ልብሙሉ ታጋይ፣ ደርግ
ለምን ተቻኩሎ ገደላት? ሰሙኑን ስናወራ ለጥያቄዎች ሁሉ ኣጭር መልስ መስጠት የሚቀናው ጉዋደኛየ “ስማ! ለምን ለምን አትበል። ደርግ
ስለሆነ ነዋ” ነበር ያለኝ። ግን ደርግም ቢሆን በኢትዮጵያ ምድር የነበረ የሰዎች ስብስብ ነው። ሌሎች እንሰሳትን እየገደሉ መመገብና መኖር
የተፈጥሮ ግዳጅ የሆነባቸው አንበሳና ጅብ የመሳሰሉ አራዊቶች አንክዋን ስለቻሉ ብቻ ከአስፈላጊያቸው በላይ አይገድሉም።
እንዲያም ሆኖ እንዲህ ያለ ከፋት ፈጻሚዎቹን ሲጠቅም ወይንም አሸናፊ ሲያደርግ በታሪክ ተመዝግቦ አልታየም። አሸናፊዎቹ ሁሌም ጀግኖቹና
እውነተኞቹ እነ ቐሺ ገብሩ ናቸው። ቐሺ ገብሩ ለመጨረሻ ጊዜ በውግያ የተፋለመችበት 1982 የበጋ ወቅትና፣ የነበረችበት ግንባር ጎንደር-
ደብረታቦር በብዙ ወሳኝ ድርጊቶች የተሞላ የውጊያ ትርኢቶች ቅጽበት ለቅጽበት የሚተወኑበት መድረክ ነበር። የነዛ ወሳኝ ድርጊቶች ቀጥተና
ውጤትም እነቐሺ ገብሩ አሽናፊ ሆኖው ስማቸው ከመቃብር በላይ በመልካም ዝና ከአጥናፍ አጥናፍ፤ ከትውልድ ትውልድ የናኘበት፣ ደርጎች
ከነእኩይ ሃሳባቸውና ምግባራቸው ላይመለሱ ጥልቅ መቃብር ውስጥ የተጣሉበት ወቅት ላይ እንገኛለን። ገናም ነፍስወከፍ ትውልድና ዘመን
አፈርና ድንጋይ፣ እሾህና አረም እያለበሳቸው ይቀጥላል።

ደርግና ሓየሎምና ሳሞራ
የካቲት ወር 1982 ደርግ ደብረታቦርን ጨምሮ የዚያ አካባቢና የሰሜን ሸዋ ገዢ ቦታዎች በሙሉ ለታጋዮች አስረክቦ ባህርዳርና ጎንደር፣
ደሴና ጣርማበር ተከርክሞ መጪ እጣፈንታውን የሚጠባበቅብት ሆኖ ተገባደደ። ከዚያ በኃላ ዘመቻ የማድረግ አቅሙ ሙሉ ለሙሉ
ተቀምቶ ስለነበር ሊያደርገው የሚችለው ነገር አልነበረም። ሆነም ቀረም የቐሺ ገብሩ ጉዋደኞች በፈለጉትና በተዘጋጁበት ጊዜ ለሚከፍቱት
ዘመቻ ምላሽ መስጠት ነው። ያም ቢሆን በየውግያው እየተበለጠና እጅ-እግሩ እየተከረከመ ጉልበቱ እያዛለበት በያንዳንድዋ ግጭት እያነሰና
ጉልበቱም እየዛለበት ነበር። ሲፈጠር ጀምሮ እንደነበረች የዘለቅችው የግብረ-እከይ ሃሳቡ ነች።
የዛሬዎቹ ሚስጥራዊ ሰነዶች ደርግ ስለወያኔ ምን ያህል ያውቅ ነበር፤ የሚለውን ጥያቄ ይመልሳሉ። እነ ኃየሎም የመሰሉ ታዋቂ የኢህአዴግ
አዋጊዎቹን በመረጃም በዝናም ደርጎች በደንብ ያውቃቸዋል። በዚህ የደብረታቦር ግንባር ተስልፎ በወያኔ ተማርኮ በኃላ የለየለት ወያኔ፣ አሁን
ደግሞ የለየለት አሉባልተኛ ሆኖ የቀረው ተስፋዬ ገብረአብ በቡርቃ ዝምታ መፅሃፉ የደርግ አዛዦች ኃየሎምን እንዴት እንደሚያስቡት ሲያሳይ
እንደ ብርሃን ፈጣን፣ እንደ ኃይለኛ የጎርፍ ማእበል ፋታ ነሺ፣ እንደ ብርቱ ፀሀይ አንዳጅ፣ እንደ ነፋስ አይጨበጤ…እያለ በፈጠራቸው ገጸ-ባህርያት በኩል ይስልልናል። መቸም የተስፋዬን የማጋነን ልክፍት አስታውሰን አገላለጹን ችላ ብንለው እንክዋን፣ ተስፋዬ ከደርግ ከፍተኛ
መኮንኖች እንደነበረው ቅርበት የሰማውና ያየው ነገር ቢኖር ነው በሚል ከጥርጣሬያችን ጋር እንቀጥል።
የደርግ 3ኛ ክፍለ-ጦር አዛዥ ኮሌነል ሰረቀብርሃን ይባላሉ። ይህ ክፍለ-ጦር ከኢህአዴግ ሰራዊት ጋር በሰሜን ሸዋ በተለይም መራኛ አካባቢ
ብርቱ ውግያ ያካሄደ እጅግ መካናይዝድ የነበረ ደርግ የሚመካበት ኃይል ነው የነበረው። ደርግ ይህንን ክፍለጦር አውድሶና አሞግሶ
አይጠግብም። “አብዮታዊውና ጀግናው…” የሚሉ ቅጽሎችን ይደረድርለታል። አዛዡ ኮ/ል ሰረቀብርሃን በየትናንሽ የውግያ አጋጣሚዎች
በእጃቸው የወደቁትን ታጋዮች በታንክ እስከመርገጥ የደረሰ ብዙ ግፍ ፈጽመዋል። መጽሃፋቸው ያው የደርጉ ነው፤ የነውረኞችና ከይሲዎች
መጽሃፍ። ይህንን ምግባራቸውን የሚያውቁት የኢህአዴግ ሰራዊት አባላት በ3ኛ ክ/ጦር ላይ ይህ ነው የማይባል ቂምና ቁጭት ይዘዋል። በዚህ
ሁኔታ እያሉ ኃየሎምና ሳሞራ በተሳተፉበት ውግያ 3ኛ ክ/ጦር መራኛ አካባቢ ሙሉ ለሙሉ ይደመሰሳል። አዛዡ ኮ/ል ሰረቀብርሃንም
ይማረካሉ። ታጋዮቹ ብርቱ ቂም ይዘውባቸው ስለነበረ በእጃቸው ሊበቀሉ አስበው አዛዡ መማረካቸውን በአግባቡ ሪፖርት ሳያደርጉ ይቀራሉ።
ኃየሎም ትክሻው ይንገረው ሰው ሹክ ይበለው፣ ራሱ እየከነፈ ቦታው ድረስ በአካል ሄዶ ኮ/ል ሰረቀብርሃንና በከፍተኛ ቁጣ ምርኮኛውን ከበው
የሚጠብቁ ታጋዮች ያገኛል። የሆነ ክፋት ያሰቡ መሰለውና ክታጋዮች ጋር ተፋጠጠ። “ጉዋዶች ኮለኔሉን እምትነኩት መጀመርያ እኔን
ገድላቹህ ነው። በእጃቹህ መፋረድ ጀመራቹህ እንዴ?” አላቸው። ታጋዮቹ ቀዝቀዝ አሉ። ማንም ታጋይ በኃየሎም እሚጨክን አንጀት
አልነበረውም። በዚህ መልክ የሰረቀበርሃን እስትንፋስ ሰነበተች። ለነገሩ ኮ/ል ሰረቀብርሃን ከዚያ በኃላ የመካናይዝድ ውግያ ስልትን
የኢህአዴግን ሠራዊት በማስልጠን ገንቢ ሚና እንደተጫወቱ የሚመሰክሩ አሉ። እዚህም ላይ በሁለቱም ተፈላሚዎች የነበረውን ጭካኔና
ሰብአዊነት ብቻ ሳይሆን ድንቁርናንና አስተዋይነትንም ማለትም፤ የማረከውን ጠላት ለመግደል የሚጣደፈው ደርግንና፣ የማረከውን ጠላት
ለራስ ጥቅም እሚያውል ወያኔን መለየትና ማነጻጸር ይቻላል።ደርግ ኃየሎምን ወያኔ አሉኝ ከሚላቸው ምርጥ አዋጊዎች ውስጥ ከፊተኞቹ
ረድፍ እንደሚጠቀስ ከዚህ ጽሁፍ ቀጥሎ በምታዩት ሰነድ ላይ ያስነብበናል።
“The master of trench warfare’ የምትለዋን የቅርብ ጊዜ አባባል በአዲስ አበባና የክልል ከተሞች በመኪኖች፣ በቁልፍ
መያዣዎችና በቲ-ሸርቶች ተዘውትራ እንደነበር የሚያስታውስ ያስታውሳል። በሻዕቢያ ወረራ ጊዜ ጠላት የሰራውን ምሽግ ተማምኖ “ፀሀይ
ትሞት እንደሆነ እንጂ ከባድመ መውጣት አይታሰብም”እያለ ሲፎክርብን እንዳልከረመ ራሱ የሰራው ምሽግ በልቶት እንዲቀር ያደረጉትን
የውግያ አመራሮችን፣ እነ ጀነራል ሳሞራን እምትመለከት አባባል ድንቅ ነች። የደርግ የመረጃ ተንታኞች ስለሳሞራም የሚሉትን ብለዋል።
በርስዎ ግምት በደርግ ዓይንና ሚዛን በአዋጊነት ብቃትና ችሎታ በቁጥር አንድ ደረጃ የሚጠቀስ የህወሓት ወታደራዊ መሪ ማን ይመስልዎታል?
በሁለተኛ ደረጃ የተቀመጠውስ? በአጠቃላይ የደርግ ወታደራዊ መረጃ ኃላፊዎች ስለአብዛኛዎቹ የህወሓት አመራር አባላት ማንነት፣
ምድብና ብቃት ምን ይጽፉና ምን ያህል ያውቁ እንደነበር የማወቅ ጉጉት ካለዎት ለጥቂት ደቂቃዎች አብረውኝ ይቆዩ። “ብርቱ ሚስጥር፣
እጅግ አስቸክዋይ” ተሰኝተው ከ603 ኮር መምርያ ለደርግ ምድር ጦር የበላይ ኃላፊዎች የተላኩትን ሚስጥራዊ ሰነዶች እንዳሉ
እዘከዝክልዎታለሁ።
ይህ በጥር 22፣ 1982 ሪፖርት የተደረገው ወታደራዊ የመረጃ ጥንቅር ስለ በርካታ የህወሓት አመራር ግለሰቦች የቤተሰብና የት/ቤት
ታሪክ፤ ስለቤትና የበረሃ ስሞቻቸው፤ የስራ ኃላፊነትና የተመደቡባቸው ግንባሮች መጠነኛ መረጃ ያስቀምጣል። ለምሳሌ የያኔው ታጋይ አዋጊ
ሳሞራ የኑስን (አሁን ኤታ መዦር ሹም- ጀነራል) እንዲህ ሲል ይገልጻቸዋል፡ “…ሳሞራ በሚል የጫካ ስም የሚጠራው መሓመድ
የኑስ…በአዋጊነቱ በአንደኛ ደረጃ ያደንቁታል።” ስለ ስመ ገናናው ጀግና አዋጊ ታጋይ (ጀነራል) ኃይሎም አርአያ ደግሞ “…ግለሰቡ በውግያ
ችሎታው በሁለተኛ ደረጃ መሆኑ ይነገርለታል” ይላል። በማዋጋት ችሎታ በ3ኛ ደረጃ እንደሚደነቁ የተናገረላቸው ደግሞ ታጋይ ወዲወረደን
(ጀነራል ታደሰ ወረደን) ነው። በዚህ ሚስጥራዊ ሰነድ አቶ መለስ ዜናዊን (ደርጎች ወዲዜናዊ በሚልም ይጠራቸዋል፤ አቶ ስዬ (ሳህለ)
አብርሃን ጨምሮ በርከት ያሉ የኢህአዴግ አመራሮችና አዋጊዎች ተገምግመዋል።
ከዶክመንቱ ከራሱ እንደምትመለከቱት የህወሓት አዋጊዎች እጅግ ውጤታማ የስልት እንቅስቃሴዎች እንደሚያደርጉና መሪዎቻቸውም
በየግንባሩ ከተዋጊዎቹ መሃል እየተገኙ ሞራል እንደሚሰጡ ሰነዱ ይገልጻል። በዚህ መልኩ ብዙ እውነተኛ መረጃ እንዳሰባሰቡ የሚገመቱት
የደርግ የመረጃ ባለሙያዎች- አይጥ ወርዳ ወርዳ እንዲሉ- በወሳኞቹ ነጥቦች ላይ ምክንያታዊ ትንታኔ ላይ መድረስ ሲያቅታቸው አለያም ሆን
ብለው ሲለግሙና የተወናበዱ አስተያየቶች ሲያቀብሉ ይታያሉ። ለምሳሌ “የህውሓት ተዋጊዎች ድፍረትና ጀግንነት ከምን ይመነጫል?”
የሚለውን ጥያቄ ለመመለስ በዙ መዳከር የሚጠይቅ አልነበረም። ስውርና ውስብስብ ጉዳይ አይደለማ። ከደርግ ሰላዮችና የመረጃ ተንታኞች
የተደበቀ መረጃ ካለመሆኑም በላይ እነ አሞራው የመሳሰሉ ታጋዮችም ፊትለፊት ቀርበው የተናገሩትን ማዳመጥ በራሱ በቂ ነበር።
አሞራው ያለውን ብናስታውስ፡ “የተቆጣ ህዝብ አለ፤ እኛ ደግሞ የዛ የተቆጣ ህዝብ ልጆች ነን” የሚል ነበር። ጀግንነቱ የሚመነጨው ከዚህ
እውነታና ስሜት ነው። ይሁንና በዛሬው ሚስጥራዊ ሰነድ የምንታዘባቸው የደርግ መረጃ አጠናቃሪዎች የመረጡት ተልካሻ ምክንያት ፍለጋ ሩቅ
መሄድን ነው። የህወሓት ታጋዮች የውግያ ድፍረትና ሞራል የሚያገኙት ከምንድነው፣ ለሚለው ጥያቄ ደርጎች እንዴት መልስ ሊሰጡ
እንደሞኮሩ አይተን በማዘን ጭንቅላታችንን እንነቀንቃለን። “ለውግያ ድፍረቱ አደንዛዥ ዕጽ እንደሚጠቀሙ ጠቅዋሚ መረጃዎች [አሉ]”
ይላል። ይህ እስከ አሁን ከደርግና ከልጆቹ ከሰማናቸው ስም የማጥፋት ተግባሮች በላይ በጣም የሚያበሳጨው ጸያፍ ማወናብጃ ነው።
ባለፈው ያየናቸው የደርግ ሰነዶች ታጋዮቹ በዚያ አይነት ፈታኝ የውግያ ወቅት በከፍተኛ ሰብአዊነትና ዲስፕሊን ይንቀሳቀሱ እንደነበር ራሱ
ደርግ በማያሻማ ሁኔታ የመሰከረው ነው። ደርግ እውነትና ውሸት ቀላቅሎ እያወራ ከነበልሹ ታሪኩ ከመቃብር በታች ወርደዋል። እውነተኞቹና
አሸናፊዎቹ ታጋዮች በህይወት ያሉቱ በህያው እንቅስቃሴያቸው፤ ሰማእታቱ ደግሞ መልካም ስማቸውና በቅብብሎሽ ሂደት ላይ ባለው
ሰንደቃቸው ምክንያት ዛሬም ሁሌም ከመቃብር በላይ ናቸው።ከዚህ ቀጥሎ ተያይዘው በቀረቡላችሁ ገጾች፣ እስከአሁን የጠቀስናቸውን ብቻ ሳይሆን ሌላ ይዘት ያላቸው ኦሪጅናል ቅጅ የደርግ ሚስጥራዊ
ሰነዶችንም ያገኛሉ። ሰነዶችን ያለምንም/ማንም ጣልቃ-ገብነት መርምረው የራስዎን ግንዛቤ ያዳብሩ። በደርግና በህወሓት/ኢህአዴግ
መካከል ስለነበረው የዓላማ ልዩነት በያዙት ዕውቀት ላይ በአሰራራቸውና የዕለተዕለት ምግባሮቻቸው ላይ ፈጽመው የማይመሳሰሉ ኃይሎች
እንደነበሩ በደንብ ይገነዘቡብታል። ለምሳሌ ከነዚህ የሚስጥር ሰነዶች አንድዋ፣ “ወንበዴዎች” የየካቲት በአላቸውን በድግስ ለማክበር
በጎንደር፣ ወገራ አውራጃ አርባወዳ በተባለው መንደር ብዙ ኩንታል እህል ሸምተው አቶ ንጋቱ ገብረስላሴ በተሰኘ አርሶአደር ቤት
ማስቀመጣቸው ጥቆማ ደርሶናል የሚል መረጃ ለበላይ የደርግ ጦር መሪዎች ሪፖርት መላኩን ተመልክቶ ይነበባል። ተቀባዩም ኃላፊ ሳይውል
ሳያድር ድሮ በምናውቃት የባለስልጣኖች መመርያ አፃፃፍ በአግድሞሽ “አስፈላጊውን ክትትልና እርምጃ ወስዳችሁ ውጤቱን አስታውቁን”
የሚል ቀጭን ትእዛዝ አስፍሮ ይታያል። ከዚህ በኃላ የአርሶአደሩና የቤተሰቡ እጣፈንታ ምን ሊሆን እንደሚችል እያሰላሰልን እናስበው።
ጥቆማው ከክፉ ምቀኛ የተገኘም ቢሆን፡ አቶ ንጋቱ ታጋዮቹን “ሌላ ቦታ ፈልጉ” ለማለት ድፍረት አጥቶ አርጎትም ቢሆን በደርግ ቤት
“በለው-ግደለው” ነው።
ለደርግና ሻዕቢያ ደጋፊዎች
Try again, Fail again, Fail better. እንተርጉመው ብንል በመጀመርያው ባይሳካልህ ደግመህ ሞክር፣ እንደገና
መውድቅ የግድ ቢሆንብህ እንኩዋ የተሻለ አወዳደቅ እንጂ የመጀመርያው አይነት አወዳደቅ አትውደቅ እንደማለት ነው። ይህን አስተማሪ ቃል
የተናገረው ሳሙኤል ቤኼት ነው። እስቲ የተሻለ አወዳደቅ አሳዩን። እስቲ የተሻለ ዓሊ አብዱ፣ የተሻለ ታማኝ በየን አሳዩን። የታደሉት በገንቢ
ሂስ ተሞራርደው፣ አቅሞቻቸውን አዋድደው በመደጋገፍና በመተራረም አገርንና ትውልድን ይገነባሉ። ታሪክ ይሰራሉ። እናንት የኛዎቹ የደርግ
ናፋቂዎችና የሻዕቢያ ሹምባሾች ደግሞ የመተባበር ቁምነገር ቀርቶ የተሻለ አወዳደቅ እንኩዋን ማሳየት ተሳናቹህ። መላልሳቹህ እስዋኑ
አወዳደቅ ታሳዩናላቹህ። ቐሺ ገብሩ አስተማረች፣ አሞራው አስተማረ፤ ኃየሎም አስተማረ…የተቀበለ የለም። ሳሞራ አሁንም ድረስ ሻዕቢያን
ያስተምራል። ፀሐይቱም የምስራቅና ምዕራብ የተፈጥሮ ዑደትዋን፣ ነብር ዥንጉርጉሩነቱን ባድመ ኢትዮጵያዊነትዋን እንደነበሩ ይቀጥላሉ።
ከዚህ በታች የደርግ ሚስጥራዊ ሰነዶችን ይመርም 

Advertisements
%d bloggers like this:
search previous next tag category expand menu location phone mail time cart zoom edit close