የወገን መፈናቀል – ከትግራይ ዴሞክርሲያዊ ትብብር

 

ከትግራይ ዴሞክርሲያዊ ትብብር የተሰጠ መግለጫ

በቅድሚያ አምባገነኖቹ የህወሓት/ኢህአዴግ መሪዎች በጉራ-ፈርዳ ነዋሪ ወገኖቻችን እያደረሱት ያለው ኢ-ሰብአዊ የማፈናቀል እርምጃ በጥብቅ እናወግዛለን። አያይዘንም የተፈናቀሉት ወገኖቻችን ያለምንም ሰባራ ምክንያት ወደ ነበሩበት ቦታ እንዲመለሱና እስካሁን ለደረሰባቸው እንግልትና ኪሳራ ተመጣጣኝ ካሳ እንዲከፈላቸው አበክረን እንጠይቃለን።

ቀጥለን ይህ በወገኖቻችን ላይ እየደረሰ ያለው አሳዛኝ ድርጊት ጠለቅ ብለን እንድናየው የሚያስገድደን አንድ ዓብይ ምክንያት አለ፤ ይኸውም አምባገነኖቹ የህወሓት/ኢህአዴግ መሪዎች ይህ ዓይነት ጨካኝ እርምጃ ለመውሰድ የተነሱበትን መአዝን የሚመለከት ነው። በርግጥ በብዛት አማርኛ ተናጋሪ የሆኑት ኢትዮጵያውያን የጉራ-ፈርዳ ነዋሪ ወገኖቻችን እዛው ቦታ ለበርካታ ዓመታት ሰፍርው ሲኖሩ መንግስት ፈቅዶና አውቆ ለመሆኑ አስረጁ ሰነድ የመንግስት አካል በሆነው የወረዳው ጽ/ቤትና በተፈናቃይዎቹ ወገኖቻችን እጅ ይገኛል። ይህ ባይሆንስ፤ መንግስት አስተዳድረዋለሁ ለሚለው ህዝብ በሃገሩ ውስጥ ሰፈራ መሄድ የተገደደበትን ምክንያት አገናዝቦ አማራጭ መፍትሄ ያቀርብለታል እንጂ እንደጠላት ቆጥሮ የትም እንዲጣል ማስገደድ ነበረበትን ? የቤተ ክርስትያኑ መሪዎችስ ከጨካኙ መንግስት ጋር ወግነው አረሜናዊ ተግባር ላይ መሰማራት ነበረባቸውን ? ይህ አስከፊ ችግር በተናጠል የሚታይ ክስተት ሳይሆን ከአገዛዙ ባህርይና ከሚከተለው የአሰራር ዘይቤ ጋር ተያይዞ መቃኘት ይኖርበታል።

ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ

 

Advertisements
%d bloggers like this:
search previous next tag category expand menu location phone mail time cart zoom edit close