ታዳጊው ህጻን ያለአግባብ አንስቴዚያ ተወግቶ አቅመ በሽተኛ (ፓራላይዝድ) ሆነ “ለጉሮሮ ህመም ተብሎ አንስቴዚያ የተወጋውን እጻን እንታደገው” ፣

Share in top social networks!

ታዳጊው እጻን ያለአግባብ አንስቴዚያ ተወግቶ  አቅመ በሽተኛ (ፓራላይዝድ) ሆነ  “ለጉሮሮ ህመም ተብሎ አንስቴዚያ የተወጋውን እጻን እንታደገው” ፣

በዛሬው እለት ይዘንላችሁ የቀረብነው እንግዳችን ከጂዳ ሲሆን  እኝህንም ወ/ሮ ያገኘናቸው በዘመኑ ባፈራው የሶሻል ኔት ዎርክ ግኑኝነት ላይ የቴዎድሮስ ካሳሁንን የቀለበት ሰነ ስርአት ብስራተ ዜና ባቀረብንበት ወቅት ላይ በአስተያየት መስጫ ሳጥናችን ስለ ልጃቸው አሰቃቂ ኑሮ ስለገለጹልን እኛንም ልባችንን እና ቀልባችንን ስቦን ዛሬ በተወሰነ መልኩ ለማቅረብ ሞክረን ሆኖም የልጃቸውን የልጅነት አሰቃቂ ህይወት ወላጆችም ሆኑ ወጣቶች ስሜቱ ሊኖራችሁ እንደሚችል ስለምንረዳ ለማቅረብ ወሰንን ወሳኔአችንንም ከመሬት እንዳይወድቅ ዘንድ አንባብያንንም በጋራ ለፍትህ ለመቆም እንዲሁም ታዳጊውን ህጻን ህይወቱን ለመታደግ ያደርጉ ዘንድ ተማጸንን ! ይህንንም በጥያቄ መልክ እና እንደ ዜናም ስለምናቀርበው  የጥያቄውን እና  ሃሳቡን ይዘት እንዳይለውጥ ለማድረግ እንጥራለን መልካም ንባብ …ማለዳ ታይምስ ።

ሰላም ማለዳ  ይህ የእንግዳችን ሰላምታ ነበር በማለዳው በፌስ ቡክ ላይ የቀረበው ሰላምታ  እባክህን ነጻ ከሆነክ ልታናግረኝ ትችላለህ የምታስታውሰኝ ከሆነ ባለፈው አናግሬህ ነበር እዚህ ፊት ለፊት ላይ የምታየው ልጄ ነው ።

ማለዳ ታይምስ አስታውሳለሁ ምን ልርዳዎት  ?

ሃሊማ ሙዘሚል እባላለሁ ነዋሪነቴ በጂዳ ሲሆን በአሁን ሰአት አንድ ልጄን በህመም ምክንያት ሆስፒታል ገብቶ እየተሰቃየብኝ ይገኛል ። የህክምናው ጊዜ በታም እረጅም ጊዜ ወድሶአል ለስድስት አመታት ልጄ ህክምና ሲገባ ገና የአራት አመት ልጅ ነበር አሁን አስር አመቱ ነው  አልጋ ላይ እያደገ ነው ። ለጉሮሮው የህክምና  አገልግሎት ለማግኘት በገባበት ወቅት አላስፈላጊ የሆነ መርፌ ሰጥተውት  ፓራላይዝድ ሆኖአል ።

ለስድስት አመታት የኢትዮጵያን ኤምባሲ ደጅ፡ጠንቻለሁ ምንም ሊረዱኝ አልቻሉም  ምንም ልንረዳሽ አንችልም ብለውኝ ተስፋ አስቆርጠውኛል ።

ማለዳ ፣ ወይዘሮ ሃሊማ ለልጅጅዎት የተሰጠዎትን የመድሃኒት ስም ያውቁታል?

ወይዘሮ ሃሊማ አንስቴዚያ ይባላል “anesthesia”

ለምን ይህንን መድሃኒት ሊወጉት እንደቻሉ መረጃ አለዎት ?

ወ/ሮ ሃሊማ ምንም የማውቀው ነገር የለኝም

ማለዳ …..በጣም የሚያሳዝን ተግባር  ነው !

ማለዳ እስካሁን ምንም ሊፍጽሙለት አልቻሉም ?

ወ/ሮ ሃሊማ አዎ ሆስፒታሉ ሚንም ማድረግ አልቻሉም እንዲያውም በልጄ ላይ ያደረጉት አንሶአቸው እንደገና ጭካኔ በተሞላበት አንደበት ልጅሽ ከአሁን በሁዋላ ምንም አይሰራልሽም  ስለዚህ እሱን እንግደለው እና ለአንቺ ብር እንስጥሽ እና  ሁሉንም ነገር ተይው እና በሰላም ተቀመጪ አሉኝ ምንም ቢሆን ፈጣርኢ የፈጠረውን ልጄን ጨክኜ ልገድለው አልፈልም ብዬ ልጄን ለገዘብ ብዬ ልሸጥ አልፈልግም ። በዚያም ላይ ክስ ብዬ ፍርድ ቤት ብሄድ ተዘግቶ ዬኔም መንገዱ ሁሉ ተዘጋብኝ ፣የምነግረው ጠፋኝ የምጮህበት እና ብሶቴን የማሰማው አጣሁ እባካጭሁ አንድ በሉልኝ እናንተ ወገኖቼ ጩኸቴን አሰሙልኝ !

ማለዳ   በጣም እናዝናለን ! ለመሆኑ አሁን እርስዎ ያሉት የት ነው

ወ/ሮ    ሃሊማ  አሁን ሳኡዲ አረቢያ ጂዳ ነው ያለሁት

ማለዳ   እግዚአብሄር ከእርስዎ ጋር ይሁን!

ወ/ሮ ሃሊማ ሰለሁሉም ነገር ከልብ አመሰግናለሁ !

ማለዳ  በጂዳ የሚገኘው የኢትዪጵያ ኢምባሲ ለማናገር አልሞከራችሁም ? ከሞከራችሁስ የኢምባሲው መልስ ምን ነበር እኛስ በምንችለው አቅም መጠየቅ ያስችለን ዘንድ ለእናንተ የተሰጠው አሉታዊ ወይንም አወንታዊ ምላሽ ምን ነበር?

ወ/ሮ  ሃሊማ ኢትዮጵያ ኢምባሲ በየጊዜው እየሄድኩ ለስድስት አመታት ባለቅስ ምንም መፍትሄ ሊሰጡኝ አልቻሉም ።ከዚህ አገር መንግስት ጋር አንጋፋምም ብለውኝ ነበር አዲስ ቆንጽል መጥቶ ፣ስብሰባ በተሰበሰቡበት ገብቼ አልቅሼ ፎቶውን ለአዲሱ ቆንጽላ አሳይቼው እሱ መጥቶ አሳይቼው ነበር እሱም ሆስፒታል ድረስ መጥቶ አየው ከዚያም የሆስፒታል ሰራተኞቹንም ሄደው አናገሩአቸው ባለቤቱንም ሄደው አናገሩ ከዚያም ምንም ሳይሉኝ ሳያናግሩኝም በዚያው ጥለውኝ ሄዱ ።እኔም ሆስፒታል ድረስ ሄጄ ምን አሉ ብዬ ስጠይቃቸው አስቀጥረሽ ጠብቂ አሉ።

ማለዳ    ማን ይባላሉ አምባሳደሩ ?

ወ/ሮ ሃሊማ  አምባሳደር መሪዋን በድሪ ይባላሉ ! በአካል ሄጄ አምባሳደሪንም ሳናግራቸው ያሉት እራስሽ ጠበቃ ቀጥረሽ ተከራከሪ ብለው ነው ያሉት እኔ ደግሞ አቅሙም የለኝ እናንተም ባላችሁ አቅም ተባበሩኝ ስላቸው ምንም ማድረግም የምንችለው የለም ይሄ ከአቅማችን በላይ ነው ከዚህ አገር ባለ ሃብት ጋር ምንግስታሽን ጥምረትን እንጂ ወዳጅነትን ማጣት አይችልም በአንዲት ተራ ነገር ብለው ነው ያዋደቁት ጉዳዩን ።

  • ማለዳ እኛም እስኪ ከኢምባሲ ለመነጋገር እንሞክራለን እንደምንም አነጋግረን የሚሉንን ለመሰማት እንሞክራለን ፣በተለይ በእርዎ በኩል ለመድሃኒት እና ለህክምና እስከዛሬ ድረስ ያወጡትን ወጭ ደምረው አጠቃላይ  የልጅዎትንም የጉዳት ሁኔታ የሚያመለክቱ መረጃዎችን በzelalem@maledatimes.com  ኢሜል አድራሻችን ይላኩልን ።
  • ማለዳ እስኪ ስለ ልጅዎት ጥቂት ይበሉን ልጁ በአሁን ሰአት በምን አይነት ሁኔታ ላይ ነው ያለው ?
  •  ወ/ሮ ሃሊማ  በአሁን ሰአት ልጁ እዚያው ሆስፒታል ነው ያለው ባዶ ቤት ዉስጥ አስቀምጠውት ይገኛል ፣እኔንም ፈርሚና እንግደለው ለአንቺም ካሳ ክፍያ እንስጥሽ ብለውኝ እንቢ ብዬ ነው እስከዛሬ ያለሁት  እሱም እዚያ ባዶ ቤት ውስጥ ነው እየተሰቃየ ያለው ቤራሱ ጊዚእ እንዲሞት ያለጠባቂ ብቻዉን አስቀምጠውት በስቃይ ላይ ነው እኔም የስደት ህይወት ስቃይ አንሶኝ በእሡ የህመም ስቃይ አብሬው እየተሰቃየሁ ነው …የልጄ ስቃይ የከፋ የህይወት ደረጃ ላይ ደርሶአል እንሱም ጨክነዋል ዶ/ሩ እንኳን የሚያየው በሳምን አንድ ቀን እኔ ሄጄ እይልኝ በዬ ካልጨቀጨኩት ለማየትም ፍቃደኛ አይደለም ።

ማለዳ ምን ያህል እንክፈልዎት አሉዎት በልጅዎት ነፍስ ላይ ?

ወ/ሮ ሃሊማ እነሱ ያሉት ፈርሚና የፈለግሽውን እናደርግልሻለን ነው ያሉት እኒእ ደግሞ በልጄ ህይወት ፈርሜ ግንዘብ አልበላም ፣የምፈርመው እኮ በልጄ ህይወት ላይ ነው ።

ማለዳ ታይምስ ህይወት እንደ ቀላል እንዲህ የምናያትን ያህል ከባድ ፈተና ወስጥ ትከተናለች ሁላችንም የዚህ አለም ነዋሪዎች ሆነን ሳለን ለሰው ልጆች ህይወት ከፍተኛውን ሰበአዊነት እና ርህራሄ እንዲሁም ለህጻናት ተገቢውን እንክብካቤ ማድረግ ሲገባን በአለማችን ላይ ግን በተለይም በስደተኞች ኢትዮጵያውያኖች ላይ እየተደረገ ያለው ግፍ እና መከራ ዛሬም አልበቃ ብሎ በከፍተኛ ደረጃ እየተባባሰ እና እየበረታ መጥቶ ይገናል ሆኖም ግን ሁላችንም ተባብረን ይህንን ነገር አንድ ልንለው ይገባል ፣መንግስታችንም ይህንን ለማስቆም ሃይሉን እና ጉልበቱን አጠናክሮ ከህብረተሰቡ ጋር ጠንክሮ በሰራ የተገባ ነበር ግን ማን ዘርን ከዘር ያለያይለት ሁላችንንም በአንድ ሃሳብ እንዳንሰማማ እንዲህ አይነት መሰናክል ከፊታችን ደቅኖብን ዛሬ ላይ ደረስን ወገናችን ሜዳ ላይ ወድቆ ስናየው ልንረዳው አይደለም ልናየው እንድጸየፋለን ከንፈር መጠን እናልፋለን ይህንን ከማደርግ ይልቅ ዛሬ ላጠፋነው ጥፋት በአምላካችን ፊት ይቅርታ ገብተን በይቅርታ ምህረቱ ተዳሰን የነገን ይህወት ለመታደግ በጋራ እንነሳ  የዘር መከፋፈል እና ዘር መቁጠሩን ትተን ከአንድ ምንጭ መቀዳታችንን ልብ እንበለው …..ኢትዮጵያችንን እናስታውሳት ከመልከአምድራችን አቀማመጥ ጀምሮ የአፈጣጠራችን ስህበት የ እኛነታችንን የሚለውጠው አይደለም እና አሁንም በጋራ ለመልካም ነገር እንዝመት ይህንንምታዳጊ ህጻን ለመታደግ ዛሬ ነገ ሳንል ሁላችንም የተቻለንን ያህል እንረባረብ ።ወላጅ እናቱንም ሆነ በጂዳ የሚገኙትን የኢትዮጵያ አምባሳደር ለማግኘት ከፈለጋችሁ በስልክ ቁጥራቸው ማነጋገር የምትችሉ መሆኑን ስንገልጽ በሰሜን አሜሪካ የምትገኙ ወላጅ እናቱን ለማግኘት ካልቻላችሁ በስልክ ቁጥር 312566 6280 በማግኘት መርዳት የምትፈልጉትን ሁሉ ለመቀበል እና ለወ/ሮ ሃሊማ ሙዘሚል የምናስተላልፍ ሲሆን እርሳቸውን ለማግኘት ደግሞ በስልክ ቁጥር             00966502509571       ወይንም             00966593113823       የአምባሳደር መሪዋን በድሩን ለማነጋገር 9660505681794 የሚያገኙአቸው መሆኑን እንገልጻለን .።ከምስጋና ጋር ማለዳ ታይምስ እና ዘሃበሻ ዝግጅት ክፍል

http://www.maledatimes.com

Advertisements
%d bloggers like this:
search previous next tag category expand menu location phone mail time cart zoom edit close