“እኛ የአንድም ኢትዮጵያዊ ገበሬ መሬትን አልነጠቅንም” የሰውዲ የግብርና ሚ/ር “መንግስት ከቀያችን ያፈናቀለን ሊገድልን አስቦ ነው” ተፈናቃይ አርሶ አደር

የሰውዲ አረቢያ መንግስት “ከኢትዮጵያዊያን አርሶ አደሮች ላይ ቅንጣት መሬት በሃይል አልወስደንም” ይልቁንም በአህጉሪቱ ውስጥ ላደረግነው የልማት ተሳትፎ ከመንግስት ባለስልጣናት የማበረታቻ ሙገሳዎችን አግኝተናል የላል፡፡ ተፈናቃይ አርሶ አድሮች በበኩላቸው ዛሬም ድረስ የገዢው መንግስትን ማማረራቸው ተዘገበ፡፡
በታዳጊ አገሮች በተለይ ደግሞ በኢትዮጵያ ውስጥ አየተካሄደ ነው በተባለው የመሬት መቀራመት ዘመቻ (Land Grab) በተመለከተ ከተቆርቋሪ ወገኖች ከፍተኛ ወቀሳ ከሚቀረብባቸው ባእዳን ከበረቴ አገሮች መካከል አንዱ የሆነው የሪያድ (ሰውዲ አረቢያ) መንግስት የግብርና ሚኒስትር የሆኑት ዶክተር ፋሃድ ቤን አብዱላርሃም “በልማት ስም ከመሬቱ ላይ አላግባብ የተፈናቀለ አንድም ኢትዮጵያዊ አርሶ አደር የለም፡ ወቀሳውም ቢሆን መሰረተ ቢስ ነው፡፡” በማለት የመንግስታቸውን አቋም ሰሞኑን ገልጸዋል፡፡ በምድረ አሜሪካ ከላስቭጋስ ከተማ የሚሰራጨው የህበር ራዲዮ “ዚስ ኢዝ አፍሪካ” የተሰኘውን ድህረ ገጽን በመጥቀስ በሳምንቱ ማብቂያ ላይ አንደዘገበው ከሆነ በምግብ እና በመስኖ ውሃ አቅርቦት እጦት የሚቸገረው ከ ሃያ አምስት ሚሊዮን በላይ የሚገመተውን ህዝቡን ለመታደግ ሲል የሰውዲ መንግስት የንጉስ አብደላ ማበረታቻ በተባለ ፕሮግራም ጥላ ስር ከስምንት መቶ ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር በላይ ወጭ በማደርግ ኢትዮጵያን ጨምሮ በሰላሳ የተለያዩ የአለም ታዳጊ አገሮች ውስጥ ኢንቭስት ለሚያደርጉ የሃገሪቱ ባለሃብቶች የምክር ፡በመንግስታት ደረጃ ውይይት( ስምምነት) እና የሃሳብ አገልግሎት የሚሰጥ “ገለልተኛ” የተባለ ማእከል ያቋቋመ ሲሆን ኢትዮጵያን በተመለከተ በ 2009 እኤአ የመጀመሪያውን ለሩዝ፡ለስንዴ እና ለገብስ ምርቶች የሚውል መሬት በ አንድ መቶ ሚሊዮን ዶላር ኢትዮጵያ ውስጥ በሊዝ መልክ ገዝቶ የርክብክብ ሰነስርአቱ ሲካሄድ የአገሪቱ ንጉስ በስነስረአቱ ላይ መገኘታቸውን ያወሳው ዜና ዘገባው ከደሃው የጋምቤላ አርሶ አደር በግዴታ እና በሃይል ትነጥቆ ለስውዲ ባለሃብቶች ተሰጥቷል ስለተባለው ሰፊ እና ለም የእርሻ መሬት በተመለከተ ለዶክተር ፋሃድ ላቀረበላቸው ጥያቄ ” በእውነቱ ከሆነ የተባለውን ስሞታ በተመለከተ ከምእራባዊያን ተቆርቋሪዎች ወይም የዜና ሰዎች ካልሆነ በቀር ከአፍሪካዊያኑ ዘንድ ከአንዳቸውም የቀረበልን ስሞታ የለም ፡እኛም ብንሆን የተባለውን አቤቱታ በአይናችን አላየንም ፡የፈለገውን ታማኝ ሆነ ተነባቢ የዜና ምንጭ ይሁን ከተባለው ቦታ ሄዶ በአይን ከማየት የበለጠ ሊሆን አይችልም” ያሉት የሰውዲው የግብርና ሚኒስቲር ” በተቃራኒው በአፍሪካ ውስጥ ለምናደርጋቸው የተለያዩ የኢንቭስትመንት ስራዎች ከመሪዎቹ የማበረታቻ ድጋፎች እየተሰጠን ነው ” ብለዋል፡፡
ዶ/ር ፋሃድ ቢን
ተቀማጭነቱ በአሜሪካ ያደረገው መንግስታዊ ያልሆነው የኦክላንድ የጥናት ኢንስቲዩት በበኩሉ ባለፈው አመት “በጋምቤላ ክልላዊ መንግስት ወስጥ ዜጎች ከመኖሪያ ቀያቸው በሃይል ይፈናቀላሉ፡አካባቢውም ለእርሻ ጥቅም ከመዋሉ በፊት ተገቢው የቅድመ አካባቢያዊ ጥናት(Environmental Impact ) አልተደረገበትም” ሲል ሰውዲ ስታር በተባለው ኩባንያ ላይ ወቀሳ ማቅረቡ አይዘነጋም፡፡ ይህንኑ እና መሰል ወቀሳዎችን በተመለከተ የሰውዲው የግብርና ሚኒስተር ስሞታውን ያስተባብሉ? ወይም
ይቀበላሉ? ተብለው ሲጠየቁ “ተፈናቀልኩ የሚል አንድ ተራ ግለስብ እንኳን አላየሁም፡እናንተም ሆናችሁ ሌሎች ታማኝ ዘጋቢዎች ተፈናቅልን የሚሉ ወገኖች ካጋጠሟችሁ ለእኛ አሳውቁን ፡፡እኔ እስከ ማውቀው ድረስ የሰውዲ ባለሃብቶች መሬት በሊዝ ለሚሸጡት አገሮች ህግ ተገዤዎች ናቸው ፡እኛ በጋራ ( በፓርትነርነት) የምንሰራው እንጂ ነጣቂዎች አይደለንም፡፡ ያለ አካባቢው ህዝብ ድጋፍ ዘላቂ የሆነ ልማት ማደረግ አይቻልም ” በማለት የአገራቸውን አና የሰውዲ ባለሃብቶችን “አቋም” ለማንጸባርቅ ሞክረዋል፡፡
በሌላ ተመሳሳይ ዜና አለርት ኔት የተሰኝው ድህር ገጽ ሰሞኑን እንደገለጸው ከሆነ ከአሰር ሰዎች አንዱ የምግብ እጥረት ችግር ይገጥመዋል፡በድርቅ ወራት ከአምስቱ አንዱ ኢትዮጵያዊ መራቡን ጠቅሶ ኢትዮጵያ ከ2008 እኤአ ጀምሮ በሚሊዮኖች ሄክታር የሚቆጠር ለም መሬትን ለቻይና፡ ለህንድ፡ለሰውዲ እና ተመሳሳይ ባለሃብቶች መስጠቷን ጠቅሶ ለባለሃብቶች ሲባል በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ በደቡብ ምእራብ (ጋምቤላ አካባቢ ) የሚኖሩ አርሶ አደሮች ከመሬታቸው በሃይል አንደተፈናቀሉ የሰባዊ መብት ተቆርቋሪዎች ሪፖርትን ጠቅሶ የገለጸ ሲሆን ከተፈናቃይ አርሶ አደሮች መካከል አንዱ አባወራ ሰለደረሰባቸው በደል ሲናገሩ “ገዤው መንግስት መሬታችንን ነጥቆ ለባለሃብቶች በመስጠት ወደዚህ ስፍራ ያመጣን በረሃብ እንድን ሞት አስቦ ነው፡ ሌላው ቀረቶ ወደ ቅድሞው ቀያችን መመለስ እንኳን እንችልም” በማለት ደረሰብኝ ያሉትን የመፈናቀል አደጋ ገልጸዋል ፡፡
የሂው ድህረ ገጽ በሰተመጨረሻም ኢትዮጵያ በአለም ፈጣን የህዝብ ቁጥር ከሚታይባቸው አገሮች ውስጥ በአምስተኛ ደርጃ መገኘቷን የጠቀሰ ሲሆን ይህ የህዝብ ቁጥር በኢኮኖሚው ላይ ሰለሚኖረው አሉታዊ ተጽእኖ በተመለከተ ወ/ሮ ተወዳጅ ሞገስ የተባሉ እና በአለም የምግብ ጥናት ማእከል ሰራተኛ በኢሜል ለድህረ ገጹ አንደገለጹለት “የወቅቱ የኢትዮጵያ መንግስት የሞከራቸው በርካታ የግብርና ማሻሻያ ፖሊሲዎች በፈጣን ሁኔታ እየገሰገሰ ከመጣው የህዝብ ቁጥር ጋር የሚጣጣም ባለመሆኑ ፖሊሲው ውጤት አልባ ሆኗል ፡፡” ማለታቸው በዘገባው ላይ ተካትቷል፡፡
(ዘገባውን ያጠናቀረው ታምሩ ገዳን ለተጨማሪ ጥያቄዎች እና መረጃዎች በtamgeda@gmail.com ማግኘት ይችላሉ፡፡ )
Advertisements
%d bloggers like this:
search previous next tag category expand menu location phone mail time cart zoom edit close